ከእርቅ ማዕድ ፕሮግራም አዘጋጅና ከሥነ ልቦና ባለሞያ ትዕግሥት ዋልታንጉስ ጋር የተደረገ ቃለምልልስ።
- የኢሬቻ መታሰቢያ ሐውልት ተቃውሞ ገጥሞታል
በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር፣ሰሜን ጎንደርና ደቡብ ወሎ አጣታዳፊ ትውከትና ተቅማጥ ወይም (አተት) መስፋፋቱን የተ.መ.ድ የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ /ኦቻ/ አስታወቀ።
በኦሮሚያ ክልል ከሐረር 16 ኪሎሜትር ርቃ በምትገኘው ኮምቦልቻ ከተማ የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ከገባ አምስት ቀናት መቆጠሩን የከተማው አስተዳደር አስታወቀ።
የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ዳንኤል ሺበሺና በጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ሥር ከታሰሩ ከዘጠኝ ወራት በኋላ በ50 ሺሕ ብር ዋስትና ከእስር ተለቀዋል። ጽዮን ግርማ የእስር ቤት ቆይታቸውና ከእስር በኋላ ያለው ሁኔታ ምን እንደሚመስል ጠይቃቸዋለች።
ወደ የመን በመጓዝ ላይ እያሉ ቀይባህር ላይ በአሸጋጋሪዎቻቸው ተገፍትረው ከተጣሉት መካከል የተረፉት ስደተኞች ወደ ባህር የተወረወሩት በአሸጋጋሪዎቻቸው ከተደቀነባቸው መሳሪያ ጭምር ለማምለጥ እንደሆነ ለአሜሪካ ድምጽ ገልፀዋል።
በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የንግድ ቤቶችና የሕዝብ ትራንስፖርት ተቋማት አገልግሎት ማቋረጣቸውን ነዋሪዎች እየገለፁ ነው። ለዚህም በምክንያትነት የሚያስቀምጡት በባሕርዳር ከተማ የዛሬ ዓመት በተቃውሞ ወቅት በፀጥታ አካላት የተገደሉ ወጣቶችን ለማስታወስና አሁን በአማራ ክልል ተግባራዊ መደረግ የጀመረውን የቀን ገቢ ግምት በመቃወም ነው። በኦሮሚያ ደግሞ የታሰሩ የፖሊተካ አመራሮች ይፈቱ የሚል እና በቀን ገቢ ግምቱ ላይ መፍትሔ አልተሰጠንም የሚል ይገኝበታል።
ዛሬ ነሐሴ 2/2009 ዓ.ም የሚካሄደው አምስተኛው ፕሬዝዳንታዊ የኬንያ ምርጫ ውጥረት ናይሮቢ ለሚገኙ ስደተኞች ከፍተኛ የስጋት ምንጭ እንደሆነባቸው ተናገሩ። የተጋጋለው የቅድመ ምርጫ ሂደት እርስ በእርስ ግጭት ያመጣል እንዲህ ያለ ነገር ደግሞ ለዝርፊያ፣ለመታሰር እና ለአካል ጥቃት ያጋልጣል የሚል ከፍተኛ ስጋት እንዳሳደረባቸው ወደ ሦስተኛ ሀገር ለመሻገር በመጠባበቅ ላይ ያሉ ስደተኞች ገለጹ።
የሕፃናቱን ወላጆች አነጋግረናል ቤተሰቦቹ እንደሚሉት የመደፈር አደጋው የደረሰባቸው የአንድ መንደር ወንድ ሕፃናቱ ሰባት እንደነበሩና ፖሊስ ወደ ፍርድ ቤት ጉዳያቸውን የወሰደው ሕፃናት ቁጥር አምስት መሆኑን ነው።
ችግሩ የተከሰተው በድንበር ማካለልና ማስፋፋት እንቅስቃሴ ምክንያት መሆኑን በመጥቀስ ለዚህ ችግር መንግሥት ኃላፊነት ወስዶ በአፋጣኝ ሁኔታውን ወደነበረበት እንዲመልስ ፓርቲው በመግለጫው ጠይቋል።
•የአካባቢው ነዋሪዎች ከዚህ በፊት እንዲህ ያለ ግጭት አጋጥሞን አያውቅም ብለዋል። በደቡብ ክልል አማሮ ሕዝብ (ኮሬ ጎሳ)ና በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን አጎራባች ወረዳ ነዋሪዎች መካከል የመጀመሪያው ግጭት የተጀመረው እሁድ ሐምሌ 16/2009 ዓ.ም መሆኑን ተናግረዋል።
መንግሥት የተመነባቸውን የቀን ገቢ ግምት ተቃውመው ቅሬታ ያቀረቡ ነጋዴዎች ቅሬታቸው እየታየ እንደሚገኝ ቢያስታውቅም ነጋዴዎች ግን ቅሬታቸውን የሚፈታ አካል እንዳጡ ይናገራሉ።
“በዚህ በኩል ግብር እየሰበሰቡ በሌላ በኩል ጎደለ ማለት በሀገሪቱ ተጠያቂነት ያለበት አሠራር አለመኖሩን ማሳያ ነው” ብለዋል።
አዲሱን የቀን ገቢ ግምት በተመለከተ ደረጃ “ሐ” አነስተኛ ቁርጥ ግብር ከፋዮችም ሆነ ማንኛውም ግብር ከፋዮችን በተመለከተ የተቀየረ ነገር እንደሌለ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ።
አዲሱ የቀን ገቢ ግምት በነጋዴዎችና በግብር ሰብሳቢው መካከል የፈጠረው አለመግባባት አሁንም እንደቀጠለ ነው። የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ነጋዴዎች በተደረገው ግምት ላይ ተቃውሞና አቤቱታ እያቀረቡ ሲሆን በአቤቱታዎቹ ዙሪያ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋን አነጋግረናቸዋል።
የፌደራል ዐቃቤ ሕግ በአማራ ክልል ዓመፅ አነሳስተዋል በሚል በእነ ንግሥት ይርጋ መዝገብ ክስ በመሰረተባቸው ስድስት ሰዎች ላይ፤ “ቀሪ ምስክሮቹን ለማቅረብ አንድ ዓይነት ምክንያት እየሰጠ ተደጋጋሚ ቀጠሮ በመጠየቁ ምስክሮቹን የማሰማት መብቱ ታልፏል” ሲል ፍርድ ቤቱ በዛሬው ዕለት ትዕዛዝ ሰጠ።
በአዲስ አበባ የሚገኙ ነጋዴዎች ቅሬታቸውን አቅርበው ምላሽ እየጠበቁ እንደሆነ ገልፀውልናል።
በዛሬ ዕለት በእነ ንግሥት ይርጋ መዝገብ የተከሰሱ ስድስት ሰዎችን ወክለው በችሎት የተገኙትን ጠበቃ አቶ ሄኖክ አክሊሉ አነጋግረናቸዋል።
"ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ ያላቸውን ቅሬታ በዚህ አግባብ ቢገልጹ ምንም ክፋት የለውም"የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ።
የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና በጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በ50 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰጠ። የፍርድ ቤቱ ሂደት እስኪጠናቀቅ ከሀገር እንዳይወጡ የተሰጠው ትዕዛዝ ለፍርድ ቤት መድረሱ ሲረጋጥም እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰቷል።
ተጨማሪ ይጫኑ