ከስድስት ዓመት በኋላ በነጋዴዎች ላይ የወጣው አዲሱ የገቢ ግብር ትመና በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች የንግድ ቤቶችን የመዝጋት አድማ አስነስቷል።
የፕሮግራሙ ተወያዮች በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ የሚገኘው የአሜሪካን የተፈጠሮ ሙዚየም የጥናት ቡድን አባል የሆኑት ዶ/ር ዩሃንስ ዘለቀና በዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪው የሕግ የፖሊሲና የቢስነስ አማካሪው ዶ/ር ብርሃን መስቀል አበበ ሰኚ ናቸው።
በገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግና 16 ተቀዋሚ ፓርቲዎች ሊጀምሩት የተወሰነው “ድርድር” የመስጠትና የመቀበል መርህን የማያሟላ በመሆኑ “ድርድር” ሊባል አይችልም ሲሉ ሁለት ምሑራን ተችተውታል።
ከሁለት ወራት በፊት ከሆቴሎች የሚገኙ የተራረፉ ምግቦችን እየተመገቡ ስለሚማሩ የሐረር ከተማ 40 ተማሪዎች ያቀረብነው ዘገባ ሰምተው ለልጆቹ በተለያየ መንገድ ዕርዳታ እንደተሰጣቸውና ያገኙት 231 ሺሕ ብርም ተስፋን እንደሆናቸው አሰባሳቢያቸው ነግሮናል። ልጆቹም ለተደረገላቸው እርዳታ ከልብ አመስግነዋል።
ወደ ዩናይትድ ስቴይትስ በመጓዝ ልጅ መውለድ ቢፈቀድም፤ “በቪዛ ቃለመጠይቅ ወቅት ሁኔታውን አለመግለጽ ግን ማጭበርበር ነው” ሲል በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ አስታወቀ። የተጠቀሙበትን የሕክምና አገልግሎት ወጭውን መክፈል እንዳለባቸውም ኢምባሲም ጨምሮ ገልጿል። በጉብኝትና በንግድ ቪዛ መጥተው በሆስፒታሎቹ ውስጥ ልጅ ከወለዱ በኋላ ለተጠቀሙበት አገልግሎት ክፍያን ሳይፈጽሙ የሚመለሱ አሉ ተብሏል።
በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን እና በአፋር ክልል የሚገኙ ሁለት ተጎራባች ቀበሌ ነዋሪዎች በየጊዜው በሚቀሰቀስ ግጭት ሲጋጩና ሲታረቁ ቢቆዩም አሁን ግን የ12 ሰዎች ሕይወትን ያጠፋ የከረረ ግጭት መፈጠሩን የሁለቱ አካባቢ ነዋሪዎች ይናገራሉ።
የምንሰማው ሳይሆን የሚሰማን ነው የምንፈልገው"- ነጋዴዎች
ባለፈው ሳምንት ቀዳሚ ርእስ ሆኖ የሰነበተው በአዲስ አበባ ከተማ ነጋዴዎች ላይ የተደረገው አዲሱ አማካኝ የቀን ገቢ ትመና አሁንም ነጋዴዎችንና የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣንን አላግባባም። ገቢዎች የገቢ ግምት ትመናው የቀን ገቢን እንጂ ተከፋይ ግብርን አያሳይም ሲል የነጋዴው ማኅበረሰብ አባላት በበኩላቸው ግምቱ ወደፊት ሊመጣ የሚችለውን ከፍተኛ የገቢ ግብር ማሳያ በመኾኑ ሊቀበሉት እንደማይችሉ ይናገራሉ። ተከታዩ የጽዮን ግርማ ዘገባ ይህንን ሁኔታ ያስቃኘናል።
አዲሱን የገቢ ግብር ግምት ነጋዴዎች አልተቀበሉትም። “ከገቢያችን ጋር ፍፁም ተመጣጥኝነት የሌለውና ከሥራ ውጭ የሚያደርገን ነው” ብለውታል። በኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉሙሩክ ባለሥልጣን የአዲስ አበባ የታክስ ፕሮግራም እና ልማት ሥራዎች ዘፍር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ነጻነት አበራ ትመናው የተከናወነው ሰፊ ጥናት ተደርጎ እንደሆነ ከገለጹ በኋላ ቅሬታ አለኝ የሚል ማንኛውም ነጋዴ ያለ ምንም ክፍያ በተጨባጭ ማስረጃ አያይዞ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል ብለዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ በዝቅተኛ ግብር ከፋዮች ላይ የተጣለው አዲሱ የቀን ገቢ ግብር ትመና “ከገቢያችን ጋር በፍጹም የማይገናኝና ከሥራ ውጭ የሚያደርገን ነው” ሲሉ ያነጋገርናቸው ነጋዴዎች አማረሩ።“ምሬታችንንም የሚሰማን አጥተናል” ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ ያላት ሕገ መንግሥታዊ ጥቅምና አሁን ያለበት ደረጃና ወደፊት በሚል የመመረቂያ ትናት የሠሩት የሕግ ባለሞያ አስተያየት ሰተዋል።
የኦፌኮና የሰማያዊው ፓርቲ አመራሮች ይናገራሉ
በውሃናና የአካባቢ ጥበቃ የሲቪል ምህንድስና ባለሞያ የሆኑትንና በበዩናይትድ ስቴትስ በደቡባዊ ካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት ንጹህ የመጠጥ ውሃ ለሚያቀርብ ተቋም በማገልገል ላይ የሚገኙትን ዶ/ር ስዩም ያሚ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ይሰጣሉ።
ከመደበኛው ተምች የተለየና ከዚህ ቀደም በአፍሪካ ተከስቶ የማያውቅ የበቆሎና የማሽላ ሰብል እየመረጠ የሚያጠቃ “ተምች” በኢትዮጵያ በስድስት ክልሎች መከሰቱን የእርሻና የተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው የሚኖሩ ዜጎች ያለ ምንም እንግልት ከሀገር እንዲወጡ የሰጠችው የጊዜ ገደብ ዛሬ ወይም ነገ ይጠናቀቃል። ሁኔታውን ከሥፍራው ሲዘግቡ የቆዩ ሁለት ጋዜጠኞች ከማስታወሻ ደብተራቸው እየገለጡ የዐይን እማኝ የኾኑበትን ውሎ ያስረዱናል
የኢንደስትሪ ፓርኩ አመራሮች ለአሜሪካ ድምጽ እንደተናገሩት ፓርኩ እጅግ ዘመናዊ በሆነ መልኩ ከፍሳሽ ነፃ ተደርጎ መገንባቱን ገልፀው የፍሳሽ ማስወጃ መስመሩ ለዝናብ ውሃ መውረጃ የተሠራ ነው ብለዋል።
በብሪታንያ መዲና ለንደን ውስጥ በሚገኘው ግሬንፌል በተባለው ግዙፍ የመኖሪያ ሕንጻ ላይ ባለፈው ሣምንት በደረሰው ቃጠሎ የሞቱት ሰዎች 79 ሳይደርሱ እንዳልቀሩ የለንደን ፖሊስ አስታውቋል።
ተጨማሪ ይጫኑ