በኢትዮጵያ በድርቁ ምክኒያት በተከሰተው የተመጣጠነ ምግብና የውሃ እጥረት እንዲሁም ይህን ተክለትሎ በገባው የአተት ወረርሽኝ በሶማሌ ክልል 68 ሕፃናት መሞታቸውን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አስታወቀ። የተመጣጠነ የአስቸኳይ ምግብ ዕርዳታ ፈላጊ ሕፃናት ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በዐሥር እጥፍ መጨመሩን ይፋ አድርጓል።
ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ በ13ኛውና በፒባዲ መንገዶች መገናኛ ላይ በደረሰው የመኖሪያ ሕንፃ ቃጠሎ በሕይወትም ሆነ በአካል ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ አንድ የከተማዪቱ ባለሥልጣን ለቪኦኤ አስታውቀዋል፡፡
በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ታዛቢዎች ፊት በድርድር አጀንዳዎች ላይ መነጋገር የጀመሩት ገዢው ኢሕአዲግና 16 ተቃዋሚ ፓርቲዎች "ለሕዝብ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥና የሀገሪቱን ችግር የሚያስተካክል ምንም የሚያመጡት ለውጥ የለም" ሲሉ ኦፌኮና ሰማያዊ ፓርቲ ተቹ።
በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የሚከሰተው የኢንተርኔት መዘጋትና መከፈት የማኅበራዊና ፖለቲካዊ መስተጋብሮችን እያሰናከለና እያስተጓጎለ እንደሆነ ይሰማል። ይህን በተመለከተ ጽዮን ግርማ ሦስት የኢንተርኔት አምደኞችን አወይታለች።
የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላትና ሴናተሮች የኢትዮጵያ መንግሥት ዓለም አቀፍ የሕጻናትን ጉዲፈቻ እንዲቆም የሚያስገድደውን ውሳኔ በድጋሚ እንዲያጤነውና በሕጋዊ መንገድ የጉዲፈቻ አሠራር ጀምረው በሂደት ላይ ያሉ ቤተሰቦች ጉዳያቸውን እንዲጨርሱ እንዲደረግ ለኢትዮጵያ መንግስት ደብዳቤ ጻፉ።
በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ከተቋረጠ አራት ቀናት ኾኖቷል። መንግሥት አገልግሎቱ መዘጋቱን አምኖ ይህ የተደርገው ከዚህ ቀደም ያጋጠመው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልቀቂያ ፈተና ሾልኮ እንዳይወጣና ተማሪዎች ከስጋት እና ከመረበሽ ነፃ ሆነው እንዲፈተኑ ለማስቻል እንደሆነ አስታወቋል። የዩኒቨርስቲ መምሕራን እና የድረገጽ አምደኞች ድርጊቱን ይቃወሙታል። ለተነሱ ፖለቲካዊ ችግሮች መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ ቴክኖሎጂውን ማፈን መፍትሔ አይሆንም ይላሉ።
የእስሩ ምክኒያት የኮከብ አርማ የሌለው ባንዲራ እንዲሰቀል አድርገዋል የሚል ነበር ተብሏል።
በዚህ እለት የድምፅ ማጉያ ማይክራፎን ይዞ “Down Down Woyane” በሚል ተቃውሞ ሲያሰማ የነበረው ወጣት “በዕለቱ ከእኔ በስተቀር ማይክ ይዞ የተቃወመ የለም እኔ የምገኘውም በስደት ነው ብሏል”
ቀድሞውኑ እንደወንጀለኛ ሊቆጠር በማይገባው ተከሳሽ ላይ ስድስት ዓመት ከስድስት ወር እስር መፍረድ ተገቢ ያልሆነና አሳፋሪ ጭምር መሆኑን ሰማያዊው ፓርቲና ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጹ። እንዲህ ያሉ አፈናዎች በበዙ ቁጥር የሚፈራውን ዐመጽ እንዳይቀሰቅሱ የኢትዮጵያ መንግሥት አፈናውን አሁኑኑ ማቆምና ከዚህ ቀደም የፈፀመውን የመብት ጥሰት ማረም ይገባዋል ብለዋል።
ከሙዚቃ ሥራዎቹ በተጨማሪ በኢትዮጵያዊ ማንነት፣ በአንድነትና በፍቅር ዙሪያ አተኩሮ ስለሚሠራ በርካቶች ከዘፋኝነት በላይ አልቀው ይመለከቱታል። ቴዲ አፍሮ “ኢትዮጵያ” የተሰኘውን አዲሱን አልበሙን በተመለከተ ከጽዮን ግርማ ጋር ቆይታ አድርጓል።
ቤተክርስቲያን ደጅ ላይ ለልመና ላስቲክ አንጥፈው በሚያገኙት ትርፍራፊ ምግብ ለሚያሳድጓት ማየት የተሳናቸው ወላጆቿ በቶሎ ለመድረስ ጠንክራ ከምትማር የ10ኛ ክፍል የደረጃ ተማሪ ጀምሮ፤ ቤተሰቦቻቸውን ከነመፈጠራቸው የማያውቁ በልጅነት ጊዜያቸው ብዙ መከራን የገፉ ተማሪዎች ሕይወት በዚህ ዘገባ ውስጥ ተካተዋል።
ቤተክርስቲያን ደጅ ላይ ለልመና ላስቲክ አንጥፈው በሚያገኙት ትርፍራፊ ምግብ ለሚያሳድጓት ማየት የተሳናቸው ወላጆቿ በቶሎ ለመድረስ ጠንክራ ከምትማር የ10ኛ ክፍል የደረጃ ተማሪ ጀምሮ፤ ቤተሰቦቻቸውን ከነመፈጠራቸው የማያውቁ በልጅነት ጊዜያቸው ብዙ መከራን የገፉ ተማሪዎች ሕይወት በዚህ ዘገባ ውስጥ ተካቷል።
የብሔራዊ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን በኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅ ወደ ረሃብ ሳይቀየር መቋቋም መቻሉን እየገለፀ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ፤ “ከ5.6 ሕዝብ ወደ 7.8 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይፈልጋል ለዚህም 742 ሚሊዮን ዶላር ከለጋሾች ይጠበቃል።” ይላል።
ወ/ሮ ፀጋ ስዩም መድሕን ትውልደ ኤርትራ አሜሪካዊት ናት።
ኮሌጅ ገብተው መማር የማይችሉ አምስት አፍሪካ ዲያስፖራ ተማሪዎችን ለመርዳትና በሐሳብ ለመደገፍ ሥራ መጀመሯን ትናገራለች።
በነጆ ከተማ የ11ኛ ክፍል የመሰናዶ ትምሕርቱን በመከታተል ላይ እያለ የሠራው ባለ አራት ጎማ መኪና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተመዝግቦ የፈጠራ ባለቤትነት መብት እንደተሰጠው ይናገራል።
ዘካሪያስ ጥበቡ መስፍን ይባላል። አስቸጋሪውንና ሕይወት አስከፋዩን የስደት ጉዞ በእግር ከኢትዮጵያ ጀምሮ ከሦስት ዓመት የስደት መከራ በኋላ ካናዳ የደረሰ ወጣት ነው። ይህንን ታሪኩን ከ18 ዓመት በኋላ ወደኋላ ተመለሶ “ዕውር አሞራ ቀላቢ” በሚል የዘጋቢ ፊልም ዘውግ ታሪኩን አስቀርቶታል። ፊልሙም በኒዩርክ የአፍሪካ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ከጠንካራ ፊልሞች አንዱ ወይም “Centerpiece ” ሆኖ ለመታየት ተመርጧል።
ዘነበ ጫቅሌ ዩሃንስ የተባለ የሁለት ልጆች አባትና የ32 ዓመት ወጣት ዳንሻ ከብት ገበያ ውስጥ ከብት በመነገድ ላይ እያለ መጋቢት 23 ቀን 2009 ዓ.ም በፖሊሶች ተይዞ ከተወሰደ ከሁለት ሳምንት በኋላ በእስር ቤት መሞቱን ቤተሰቡና በቅርብ የሚያውቁት ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ገልጸዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ