ዘካሪያስ ጥበቡ መስፍን ይባላል። አስቸጋሪውንና ሕይወት አስከፋዩን የስደት ጉዞ በእግር ከኢትዮጵያ ጀምሮ ከሦስት ዓመት የስደት መከራ በኋላ ካናዳ የደረሰ ወጣት ነው። ይህንን ታሪኩን ከ18 ዓመት በኋላ ወደኋላ ተመለሶ “ዕውር አሞራ ቀላቢ” በሚል የዘጋቢ ፊልም ዘውግ ታሪኩን አስቀርቶታል። ፊልሙም በኒዩርክ የአፍሪካ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ከጠንካራ ፊልሞች አንዱ ወይም “Centerpiece ” ሆኖ ለመታየት ተመርጧል።
ዘካሪያስ ጥበቡ መስፍን አስቸጋሪውንና ሕይወት አስከፋዩን የስደት ጉዞ በእግሩ ከኢትዮጵያ ጀምሮ ከሦስት ዓመት የስደት መከራ በኋላ ካናዳ የደረሰ ወጣት ነው። ይህንን ታሪኩን ከ18 ዓመት በኋላ ወደኋላ ተመለሶ በፊልም “ዕውር አሞራ ቀላቢ” ሲል በፊልም ቀርፆ አስቀርቶታል። ፊልሙም በኒዩርክ የአፍሪካ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ከጠንካራ ፊልሞች አንዱ ወይም “Centerpiece Night Film” ሆኖ ለመታየት ተመርጧል።
አቅም ተመጣጣኝ የሆነ የኢንተርኔት አገለግሎት አቅርቦት ጥምረት (A4AI)የተባለ ዓለም አቀፍ ድርጅት ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራትን የኢንተርኔት አቅርቦት ባወዳደረበት ጥናቱ ከ58 ሀገራት ኢትዮጵያን 55ኛ ደርጃ ላይ አስቀምጧታል። ለቪኦኤ ቃለምልልስ የሰጡ የተቋሙ አጥኒ አንድ ሰው 1GB የኢንተርኔት አገልግሎት ለማግኘት ከገቢው ከሁለት በመቶ በላይ ማውጣት እንደሌለበት ገልጸው "በኢትዮጵያ ግን ከወር ገቢው ከ20 በመቶ በላይ" ወጪ ማድረግ ይጠይቃል" ብለዋል።
በኢትዮጵያ ድርቅ መከሰቱ በይፋ ከተገለፀ አራት ወራት አስቆጥሯል። እስካሁን የሞተ ሰው ሪፖርት ባይደረግም ድርቁ ግን ከፍተኛ በመሆኑ 7.8 ሚሊዮን ሕዝብ ለምግብ እጥረት መጋለጡና እንስሳት መጨረሱ ይፋ ተደርጓል። መንግሥት ድርቁን ለመቋቋምና ርዳታውን በአግባቡ ለማዳረስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን በመግለጽ “ረሃብ” የለም ይላል። የነገሌ ቦረና ነዋሪ በበኩላቸው“ሌሎች እንዴት እንደሚታያቸው አላውቅም እንጂ እኛ አካባቢ ድርቁም ከፍተኛ ነው ረሀብም አለ” ይላሉ።
አስቸኳይ የምግብ ርዳታ የሚያስፈለጋቸው ተረጂዎች ቁጥር በአራት ወር ጊዜ ውስጥ ከ5.6 ወደ 7. 7.8 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል።
በፓሪስ መሰረቱን ያደረገው ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን በዛሬው ዕለት ባወጣው ዓመታዊ ዓለም አቀፍ “የሚዲያ ነፃነት” መለኪያ የደረጃ ሰንጠረዥ።ኢትዮጵያ በዚህ በማያስመሰግነው ደርጃ ላይ ከመቶ 180 ሀገሮች 150 ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። በተያያዘም በዓለም አቀፉ ፕሬስ ኢንስቲትዩት “የዓለም የፕሬስ ነፃነት ጀግና” የሚል ስያሜ ያገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲልን አነጋግረናታል።
“የአፍጋኒስታን ጋዜጠኞች ደህንነት ኮሚቴም” ሁለተኛው “የዓለም የፕሬስ ነፃነት ጀግና” ተብሏል።
“ባለወርቃማው ድምፅ” የማሊው ዘፋኝ ሳሊፍ ኬታ ከቪኦኤ ጋር #SalifKeita #MaliMusic #Africa #AfricanMusic #GabinaVOA ሳሊፍ የቆዳና የፀጉር ንጠረ ነገር እጥረት በሚያስከትለው “አልባይኖ” ተይዞ በመወለዱ ምክኒያት እንዲህ ያሉ የአፍሪካ ሕፃናት የሚገጥማቸው መገለል ሁሉ እርሱንም አጋጥሞት እንደነበር ይናገራል።
ድርቁ ከብቶቻቸውን እየጨረሰ መሆኑን የቦረና አርብቶ አደሮች ተናገሩ። ከሦስት ወራት በፊት ስናነጋግራቸው ከ30 ከብት ሃያ እንደቀራቸው ነግረውን የነበሩት አርብቶ አደር አሁን ሁለት ብቻ እንደቀራቸው ነግረውናል።
በኦሮሚያ፣ በአማራና በደቡብ ክልል ተቀስቅሶ በነበረው ተቃውሞ ምክኒያት በኢትዮጵያ የተከሰተውን የሰው ሞት፣ አካል መጉደልና ንብረት መጥፋት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዛሬ ያወጣው የምርመራ ሪፖርት "ተቋሙ ገለልተኛ ባለመሆኑ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም" ሲሉ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና የብዙሃን መገናኛ ኃላፊዎች ገለፁ።
በኅብርቱ ልዩ ልዑክ ስታቭሮስ ላምብሪኒዲስ መሪነት በአዲስ አበባ በቅርቡ የተካሄዱት ውይይቶች የሕግ የበላይነት መከበር፣ የእስረኞች ይዞታና መንግሥቱ በያዘው የልማታዊ መንግሥት አቅጣጫ የዜጎች የምጣኔ ሀብት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ የሚነቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችና በሰብዓዊ መብት ጉዳይ ላይ አስተያየት የሚሰጡ ጸሐፊዎች "ኢዮጵያ ውስጥ ያለውን የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ችግር አስረድተናቸዋል" ብለዋል።
በቂሊንጥ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ተከሰው የሚገኙ እስረኛ ተከሳሾች "እኛ በምስክርነት ልንቆጠር ሲገባ ድርጊቱ ፈፅማችኋል ተብለን መከሰሳችን ይሳዝናል" በማለት ድርጊቱን አለመፈፀማቸውን ገልፀው የእምነት ክሀደት ቃላቸውን ለፍርድ ቤት መስጠታቸውን ጠበቆቻቸው ተናግረዋል።
በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በተነሰሳው የእሳት ቃጠሎ ወቅት የማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎች በእስረኛው ላይ ከውጭ ወደ ውስጥ ተኩሰው እንደነበርና አስለቃሽ ጭስም ወርውረው እንደነበር የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ሪፖርት አቀረበ። በዚሁ መሰረት ድርጊቱን የፈፀሙት የማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎችና ትዕዛዙን የሰጡት ኃላፊዎች በሕግ ሊጠየቁ ይገባል ብሏል።
ዶ/ር መረራ በቀረቡበት በአንደኛው ችሎት የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጃዋር መሐመድ እንዲቀርቡ ጥሪ የሚያደረገው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ለችሎት ቀርቧል። ጥሪ የተደረገላቸው ተከሳሾች ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ በሰላሳ ቀን ውስጥ እንዲቀርቡ ተብሏል።
በአዲስ አበባ ከተማ "ቆሼ" ተበሎ በሚጠራው ቦታ ከደረሰው የመደርመስ አደጋ የተረፉ ቤተሰቦች አንዳንዶቹ ተገቢው እርዳታ አልተደረገልንም “ወሬውን እንጂ በተግባር ያየነው ነገር የለም” ሲሉ አማረሩ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በ24 ሚሊዮን ብር ወጪ የተሰሩ 110 የመኖሪያ ቤቶች ለተጎጂዎች ማስረከቡን እና ሁሉንም በአንድ ማዕቀፍ አካቶ እንደሚያቋቁም በሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ይፋ አድርጓል።
በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ታውጆ የነበረውና ለስድስት ወራት የዘለቀው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ለአራት ወራት ተራዝሟል። የመጀመሪያው ዐዋጅ ተግባራዊ መደረግ በጀመረበት የመጀመሪያ ወራት ታስረው የተፈቱ ሁለት ወጣቶችና የሕግ ባለሞያ አነጋግረናል።
ደቡብ ክልል፥ በጋሞ ጋፋ ዞን፥ የደምባ ጎፋ ወረዳ የሱካና የጉራደ ቀበሌ የሚኖሩ 38 አርሶ አደሮች በመሬት ግንባታ ምክኒያት የእርሻ መሬታቸው ካመረቱት ሰብል ጋር መውደሙን፣ መሬቱ ላይ አሸዋና ጠጠር ተቆልሎ አራት ዓመታት መቆጠሩን አርሶ አደሮቾ ይናገራሉ። ከዚህ በኋላ ማረስ እንዳልቻሉ፣ ልጆቻቸውን ማስተማርና ቤተሰቦቻቸውን መመገብ እንደተሳናቸውም በምሬት ይናገራሉ።
በደቡብ ክልል፥ በጋሞ ጋፋ ዞን፥ የደምባ ጎፋ ወረዳ የሱካና የጉራደ ቀበሌ የሚኖሩ 38 አርሶ አደሮች በመሬት ግንባታ ምክኒያት የእርሻ መሬታቸው ካመረቱት ሰብል ጋር መውደሙን፣ መሬቱ ላይ አሸዋና ጠጠር ተቆልሎ አራት ዓመታት መቆጠሩን አርሶ አደሮቾ ይናገራሉ። ከዚህ በኋላ ማረስ እንዳልቻሉ፣ ልጆቻቸውን ማስተማርና ቤተሰቦቻቸውን መመገብ እንደተሳናቸውም በምሬት ይናገራሉ።
በምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሀገሮችን በመጉዳት ላይ ያለውን ድርቅ “ድምጽ አልባው ቅስፈት” ሲሉ የዩናይትድ ስቴይትስ ኮንግረስ አባላት የምስክር ሰሚ ሸንጎ አስችለዋል።
በዛሬው ዕለት በአካባቢው የነበሩ እማኞች ዛሬ ቦታው እየተቆፈረ እንደሆነ ገልፀዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ