የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ እና የፓርቲው ፀሐፊ አቶ ደጀኔ ጣፋ ቤተሰቦች እስረኛ ቤተሰቦቻቸው በማርሚያ ቤቱ ውስጥ ለእስረኛ የሚሰጥ መብት ለእነሱ ስለተነፈጋቸው ማረሚያ ቤቱ መብታቸውን እስኪያከብርና ውሳኔ እስኪሰጣቸው ምግብ እንደማይቀበሉ እንደነገሯቸው ተናገሩ።
ለምስክር ሰሚ ሸንጎ ቀርበው ምስክርነታቸውን የሰጡት ስድስት ሰዎች የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎቹን "ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብት ይጥሳል። ከአሜሪካ በእርዳታ የወሰድውን ገንዘብ ለፖለቲካ ፍጆታው መጠቀሚያ ያውለዋል” ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
እናቱና ወንድሙ ሕይወታቸው አልፎ መቀበራቸውን ያላወቀ የሰባት ዓመት ታዳጊ አነጋግረነዋል
የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚንስትር ዶ/ር ነገሪ ከዚህ አደጋ በህይወት ተርፈው በተለያየ ቦታ የሚገኙ ሰዎችን ለመርዳት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንደሆነና በዘላቂነት መልሶ እንዲቋቋሙ እንደሚደረግ ገልፀውልናል።
እናት ከሦስት ልጆቿ ጋር በቤት ውስጥ ተቀብራለች
ጉዳዩን በውጭ ሆነው የሚከታተሉ የሟቾቹን ቁጥር 13 ያድርሱታል። ታፍነው የተወሰዱት 27 እንደሆኑ ሲናገሩ። በርካታ ቤቶች ተቃጥለዋል ይላሉ።
የአናኒያ ሶሪ ባለቤትና የኤልያስ ገብሩ እህት ጋዜጠኞቹ በጹሑፍ ሐሳባቸውን ከመግለጽ ውጭ የሠሩት ወንጀል የለም ብለዋል። መንግሥት በበኩሉ የታሰሩ ካሉ ወይ ሞያው የሚጠይቀውን የጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ባለማክበራቸው ነው ወይም ጋዜጠኞች ባለመሆናቸው ነው ብሏል።
የተጠየቀው ገንዘብ ካልተገኘ መንግስትት፣ የግል ባለሃብቱና ሕብረተሰቡ በጋራ ይሸፍኑታል ተብሏል። ለሶማሌላንድ የተሰጠው እርዳታም አጋርነታችንን ለማሳየት ነው ብለዋል።
በደቡብ አፍሪካ ከሁለት ዓመት በኋላ በድጋሚ ባገረሸው በመጤዎች ጥላቻ ላይ ያነጣጠረ ዝርፊያ ፕሪቶሪያ "አትረጅቪል" በተባለች መንደር ውስጥ ሙሉ የሱቅ ንብረታቸውን እንደተሰረቁ ሁለት ኢትዮጵያውያን ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ። በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ሱቃችን ሲዘረፍ ይሄ ሁለተኛ ጊዜያቸው እንደሆነ የተናገሩት ነጋዴዎች “ሱቆቹን ያሟላነው ተበድረን ነበር። ዕዳውን ሳንከፍል ከነቤተሰቦቻችን ቧዶ እጃችንን ቀረን ብለዋል።”
በኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ባገረሸው ድርቅ 5.7 ሚሊዮን ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ ይፈልጋል። ድርቁ ባለፉት ዐስርት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከታዩት የከፋ መሆኑ አሳሳቢ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገልፆ ሕዝቡን ከረሃብ ለመታደግ የሚያስችለውን ሥራ ለማከናወን 1 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ያስፈልጋል ብሏል።
የታሰሩ ጋዜጠኞች ቤተሰቦችን አነጋግረናል።
የአውሮፓውያን ባሕልና ባዕል የሆነው የሆነው ቫላንታይንስ ዴይ ወይም የፍቅር ቀንን ጨምሮ ሌሎች የምዕራባውያን ወግና ልማዶችን ኢትዮጵያውያን እንዳለ እየተቀበሉ ወይም ደግሞ አሳስተውና አጋነው እየወሰዱ ከባሕልና ማንነታችን ጋር እንዲቃረን ያደርጉታል ሲሉ በርካቶች ትችት ያቀርቡበታል። ከትችት አቅራቢዎች ውስጥ ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን እና በምህንድስና ሞያ ላይ የተሰማራውና የዩኒቨርስቲ መምሕሩ አቶ ረደኤት አባተን ጽዮን ግርማ አወያይታቸዋለች።
የካቲት 3/2009 ዓ.ም የፈረንሳይ መንግሥት የባሕል እና ኮሚኒኬሽን ሚኒስቴር ኢትዮጵያ በሚገኘው ፈረንሳይ ኢምባሲ አማካኝነት ለሦስት ኢትዮጵያውያን የኪነጥበብ ባለሞያዎች የክብር ኒሻን ሸልሟል።(ተሸላሚዎቹ የእሁድ ምሽት ፕሮግራማችን እንግዶች ናቸው።)
በኦሮሚያ እና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ድንበሮች የተቀሰቀሰው ግጭት መቀጠሉንና በዚህም በሁለት ቀናት ውስጥ የ18 ሰዎች ሕይወት ማለፉን በደቡብ ኦሮሚያ በነገሌ ቦረና አቅራቢያ የሚኖሩ ነዋሪዎች ገለጹ። የጉጂ ዞን የፀጥታ ኃላፊ ችግሩን በመንግሥትና በባህላዊ መንገድ ለመፍታት እየሞከሩ መሆኑን ተናግረዋል።
በሪዮ ኦሊምፒክስ ሁለት እጆቹን አጣምሮ ከግንባሩ በላይ በማሳየት በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የመብት ጥሰቶችን ለዓለም ግንዛቤ ያስጨበጠው ኢትዮጵያዊ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ከቤተሰቦቹ ጋር ተቀላቀለ።
ትምሕርቴን ለመጨረስ 50 ሺሕ ብር ያስፈልገኛል ትላለች - አንድ ላፕቶፕና የድምጽ መቅጃ ሪከርደር ባገኝ ጥናታዊ ጹሑፌን ማጠናቀቅ እችላለሁ ብላናለች
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመማር ዕድል አግኝተው ነገር ግን ከጥቃቅን መሰረታዊ ችግራቸው ጀምሮ እስከ ትምሕርት መርጃ መሳሪያዎች ማሟላት የማይችሉ ተማሪዎችን ለመርዳት የቢጫው ንቅናቄ በሚል የተደራጁ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በዚህ ሳምንት ዕርዳታ በማሰባሰብ ሥራ ተጠምደዋል። በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የአማርኛ ቋንቋ ሥነ-ጽሑፍና የፎክሎር ትምሕርት ክፍል የአምስተኛ ዓመት የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪ ሆና ትምሕርቷን ለመጨረስ በመንገዳገድ ላይ ያለች ወጣት ታሪክም በዘገባው ተካቷል።
ተጨማሪ ይጫኑ