ከምስራቅ ሀረርጌ የተለያዩ ቦታዎች ተይዘው ታስረው የነበሩ አንድ የ45 ዓመት ጎልማሳና አንድ የዩኒቨርስቱ ተማሪ ስለ "ጦላይ የእስረኞች ማቆያ ማዕከል" ቆይታቸው አጫውተውናል። ክፍል አንድ በትናንትናው ምሽት ቀርቦ ነበር ክፍል ሁለት በዛሬው ምሽት ይቀርባል።
ንጉሤ መንገሻ ስለ አማርኛ፣ ስለ አፋን ኦሮሞና ስለ ትግርኛ ሥርጭቶች አጀማመርና ዕድገት፣ የአሜሪካ ድምፅ ለኢትዮጵያዊያን አድማጮቹ ስለሸፈነው ክፍተት እና ስላሉበት ችግሮች ተናግሯል።
ከምስራቅ ሀረርጌ የተለያዩ ቦታዎች ተይዘው ታስረው የነበሩ አንድ የ45 ዓመት አዛውንት እና አንድ የዩኒቨርስቱ ተማሪ ስለ "ጦላይ የእስረኞች ማቆያ ማዕከል" ቆይታቸው አጫውተውናል። በዚህ ዘገባም የመጀመሪያ ቆይታቸው ምን እንደሚመስል የተናገሩትን ይዘናል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በጦርነት በተበጠበጠችው የመን ውስጥ ለሚኖሩ 12 ሚሊዮን ሕዝብ ነፍስ አድን የሚሆን የ2.1 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ጠየቀ።
ከሊቢያ ተነስተው በሜዲተራኒያን ባህር አቋረጠው ወደ ጣሊያን ለመግባት በጉዞ ላይ የነበሩና ባጋጠማቸው አደጋ የድረሱልኝ ጥሪ ያሰሙ 1500 ስደተኞች በጣሊያን የባህር ላይ ጠባቂዎች አማካኝነት ሕይወታቸው ተርፏል።
በአዲግራት ዩኒቨርስቲ ጥር 17 ለሊት ለጥር 18/2009 አጥቢያ ሕይወቱ ያለፈው የአንደኛ ዓመት ተማሪ ሹሚ አስክሬን ለቤተሰቦቹ ሲሰጥ ታማሚ እንደነበር እንደተነገራቸው ወላጅ አባቱ ገልፀው “ልጄ ከሦስት ወር በፊት ከእኔ ጋር ሲሄድ ጤነኛ ነበር” ብለዋል።
ድብደባ ደረሰብን ያሉት አነጋግረናል።
ኢትዮጵያ ለ5.6 ሚሊዮን ሕዝብ የዕለት ደራሽ ምግብ ለማቅረብ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣት ጠይቃለች።
የዩናይትድ ስቴይትስ መንግሥት ከፍተኛው የሕዝብ ቁጥራቸው የእልምና ሃይማኖት ተከታይ የሆኑባቸው ሰባት ሃገሮች ዜጎች ወደ አሜሪካ የሚያደርጉትን ጉዞ በጊዚያዊነት ከገደበ ወዲህ በዓለም ደረጃ ውዝግብ አስነስቷል።
ቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን በማቃጠል እና ለ23 ሰዎች ሞት ተጠያቂ ናችሁ በሚል የተከሰሱ 38 እስረኛ ተከሳሾች ጨለማ ቤት መታሰራቸውንና ከቤተሰብ መገናኘት እንዳልቻሉ በመግለፅ ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረቡ።
በዘንድሮ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ከ54ቱ አባል ሀገሮች 39ኙ ሞሮኮ ተመለሳ ሕብረቱን እንድትቀላቀል ድጋፍ በመስጠታቸው አሸናፊው "አንድነት" ሆኗል።
ቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን በማቃጠል 121 ተጨማሪ እስረኞች ተከሰሱ። ተከሳሾቹ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ከሳቸው እየተነበበላቸው ይገኛል። በዛሬው ዕለትም ቀኑን ሙሉ ክስ የመስማት ሂደት ተከናውኗል። በክስ መስማቱ ሂደት ተከሳሾቹ ባሰሙት አቤቱታ በችሎቱ መረባበሽ ነበር ተብሏል።
በኢትዮጵያ በአምስት የተለያዩ ክልሎች ከደረሰው ድርቅ የቦረና ዞኑ የከፋ በመሆኑ ከብቶች መሞት መጀመራቸውን ነዋሪዎች ገለጹ። በጥቂት ቀናት ውስጥ ዝናብ መጣል ካልጀመረ ደግሞ ለከፋ አደጋ እንደሚጋለጡ በመግልጽ አሁን ያለውን የግጦሽ መሬት መድረቅ በ1977 ዓ.ም ከደረሰው አስከፊ ድርቅ ጋር ያያይዙታል።
የዓለም ባንክ አስተርጓሚና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ቄስ ኦሞት አግዋ የቀረበባቸው የሽብር ሕግ ወደ መደበኛ የወንጀል ሕግ ተቀይሮ በይግባኝ በ50 ሺህ ብር ዋስ ከእስር ተለቀቁ። ከሀገር እንዳይወጡም ታግደዋል።
ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ማለት ምን ማለት ነው? ለአፍሪካ ምን ትርጉም አለው?በኒዩርክ አዮና ኮሌጅ በማኅበረሰብ ጥናት ረዳት ፕሮፌሰር ለሆኑትን ዶ/ር ደረሰ ጌታቸው የቀረበ ጥያቄ ነው።
የምክትል ፕሬዚዳንቱ ማይክ ፔንስ የህይወት ታሪክ እንደ ፕሬዚዳንቱ ዶናልድ ትራምፕ የኋላ ታሪክ አይደለም። ማይክ ፔን፡ ረዥም የሕዝብ አገልግሎት ሪኮርድ አላቸው። በአጭር ዘገባ ታሪካቸውን እንዳስሳለን።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቃለ መሃላ ፈጽመው 45ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከሆኑ አራት ቀናት አስቆጥረዋል። ለመሆኑ ዶናልድ ትራምፕ ማናቸው?
በሌላ በኩል የጥምቀት በዓል አከባበርን በዩኒስኮ ለማስመዝገብ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስታውቃለች።
የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ አባላት በ2008 ወስደው ከጋምቤላ ክልል ወስደው ካልመለሷቸው 57 ኢትዮጵያውያን በተጨማሪ 12 ሕፃናት መውሰዳቸውን፣ እንዲሁም ከ16 በላይ ሰው መግደላቸውንና ከብቶች መዝረፋቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።ጥቃቱ እስከ ትናንት ምሽት መቀጠሉና በትናንትናው ዕለት አንድ ሕፃን ተወስዶ አንድ አዛውንት መገደሉ ጨምሮ አስታውቋል። የጋምቤላ ክልል ተወላጆች ይህ ችግር በተደጋጋሚ እየተፈጠረ ያለው መንግስት ለዜጎቹ ጥበቃ ስለማያደርግ ነው ይላሉ።
ተጨማሪ ይጫኑ