በትራምፕ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ምን ሚና ይኖራቸዋል? የሚለው ጥያቄ ሰሞኑን እየተካሄደ በሚገኘው የትራምፕ ካቢኔ አባላት ግምገማ ሂደት ላይ ትኩረት የተሰጠው አጀንዳ ነበር። እንደ ቬኦው ዘጋቢ ቢል ጋሎ ዘገባ ጥያቄው ትራም በምራጫው ቅስቀሳ ቃል የገቧቸውን አነጋጋሪ ጉዳዮች የበለጠ እንዲጎሉ ያደርጓቸዋል ይላል።
እስረኞችን የማሰቃየት ችግር ኢትዮጵያ ዉስጥ ለረጅም ግዜ ሳይፈታ የዘለቀ ችግር እንደሆነ የሚናገረው የሪፖርቱ ክፍል “መንግስት የጸጥታ ሀይሎች ያደረሱትን በደሎች በተገቢው መልኩ ለመመርመርም ሆና ለዓለማቀፍ ምርመራ ጥሪዎች መልስ መስጠት አልቻለም።” ይላል። በሂውማን ራይትስ ወች ከፍተኛ የአፍሪካ ተመራማሪ የሆኑት ፌሊክስ ሆርን በርካቶች እስር ቤት በሚታጎሩባት ኢትዮጵያ እያሰቃዩ የመመርመር ተግባር ወይም ቶርቸር አሁንም ቀጥሏል ይላሉ።
የብርታንያ መንግስት ላለፉት ሦስት ዓመታት በሴቶች አቅም ግንባታና ብቃት ላይ ሲሰራ የቆየው “የኛ” መርሃ ግብርን አቋረጠ።
የገና በዓል ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ አከባበር መጋቤ ሃዲስ ሮዳስ ታደሰ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በዚህ አይስማማም- ምላሹን አካተናል
የታወቁት የሕግ ባለሞያ አቶ ተሾመ ገ/ማርያም በታኅሣሥ 7/2009 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የቀብራቸው ሥነ- ስርዓታቸውም ዕሮብ ታኅሣሥ 12 ቀን ተፈጽሟል። ጽዮን ግርማ ልዑል በዕደማርያም ስለ ጠበቃ አቶ ተሾመ ገብረማሪያም አነጋግራቸዋለች።
ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ሁለት ጋዜጠኞችን ጨምሮ በ19 የሙስሊም ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በተያያዘ በተከሰሱ ተከሳሾች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላለፈ። ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ የቅጣት አስተያየታቸውን በጽቤቱ በኩል እንዲያስገቡ ትእዛዝ ሰጠቶ ለፍርድ ውሳኔው ለታህሳስ 25 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠቷል። ጠበቃቸውን አነጋግረናል።
አቶ ዘውዱ ገብረማርያም እና አቶ ሙላው ከበደ የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በመተማ አቶ ባህሩ ይታየው የተባለ ደግሞ በጎንደር ከተማ እሁድ ዕለት መገደላቸውን ነዋሪዎችና ቤትሰብ ለአሜሪካ ድምጽ ገልፀዋል። የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ተገደሉ ስለተባሉት ወጣቶች ለጊዜው ከአካባቢው ርቀው ስለሚገኙ "መረጃ የለኝም" ብለዋል።
ላለፉት ዘጠኝ ቀናት ታስሮ ይገኝበታል በተባለው ዝዋይ እስር ቤት እንዳጡት ሲገልጹ የቆዩት ቤተሰቦቹ በዛሬው ዕለት በዐስረኛ ቀኑ እንዳገኙትና ለአምስት ደቂቃ እንዳዩት ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ። እናቱ ወ/ሮ ፋናዬ ይርዳው ታማሚ መሆናቸውን ገልፀው የእስር ጊዜውን ስለጨረሰ በአመክሮ እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል።
የእሥራት ፍርዱን እየፈፀመ ያለው የፍትሕ ጋዜጣ፣ የአዲስ ታይምስና የፋክት መጽሔት አዘጋጅና አሣታሚ ተመስገን ደሣለኝ የት እንደሚገኝ ማወቅ ከተሳናቸው ዘጠኝ ቀናት እንዳለፈ ቤተሰቦቹ ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ። የጋዜጠኞች ደህንነት ተሟጋቹ ድርጅት ሲ.ፒ. ጄ የኢትዮጵያ መንግሥት ተመስገን ያለበትን ማሳወቅ ብቻ ሳይሆን መፍታትም ጭምር አለበት ብሏል።
የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ሪፖርቱ የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ “ሪፖርቱ የመንግስትን ምላሽ ያላካተተ የአንድ ወገን ሪፖርት ነው” ብሎታል።
የሙስሊም ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ከእስር እንዲፈቱ ተንቀሳቅሳችኋል በሚል በእነከድር መሐመድ መዝገብ በሽብር አድራጎት የተከሰሱ 19 ሰዎች በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት በነበራቸው ቀጠሮ፤ በሸዋሮቢት እስር ቤት ከፍተኛ የማሰቃየት ተግባር እንደተፈፀመባቸው ለችሎት ማስረዳታቸውን ጠበቃቸውና ቤተሰብ ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።
በደቡብ ክልል በኮንሶ “የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተባበሷል” ሲሉ ወደ ዝግጅት ክፍላችን የደወሉ እና በኢሜል የላኩ ሰዎችን መሰረት አድርገን ሁለት ሰዎች አነጋግረናል።
በወቅቱ የኮሚቴው ዋና ጸሐፊና የወጣቶች ሰብሳቢ የነበሩት አቶ አደራጀው ዋኘው እዚህ አሜሪካ የሚገኙ በመሆናቸው ጽዮን ግርማ ይህን ጥያቄ መነሻ አድርጋ አነጋግራቸዋለች።
ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ ላሰቡ አሜሪካውያን ዜጎቿ ቀደም ሲል አውጥታው የነበረውን የጉዞ ማስጠንቀቂያ አራዝማለች፡፡የኢትዮጵያ መንግሥት “መሬት ላይ ያለው ሁኔታ ተሻሽሏል"ብሏል።
በኮንሶ የሕዝብ ጥያቄን ለማስመለስ በመነሳታቸው ተሰደው ጫካ ከገቡ አምስት ወር እንዳለፋቸው በሕዝብ እንደተመረጡ የሚናገሩ የኮሚቴ አባላት ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።
የአረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉዓላዊነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምዶም ገብረሥላሴ በዛሬ ዕለት ስለተካሄደው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት የካቢኔ ሹመት አስተያየት ሰጥተዋል።
"በድብደባ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይፈፀምብናል የሚሉ ለሚመለከተው አካል ማመልከት ይችላሉ" የኢትዮጵያ መንግሥት
ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት በበኩሉ ኢትዮጵያዊው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ዶር መረራ ጉዲና መታሰራቸው “በመናገር ነጻነት ላይ የተወሰደ ቅጥ ያጣና አናዳጅ እርምጃ ነው” ብሎታል
"በድብደባ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይፈፀምበናል የሚሉ ለሚመለከተው አካል ማመልከት ይችላሉ" የኢትዮጵያ መንግሥት
ተጨማሪ ይጫኑ