ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ስደተኞቹ ተላልፈው አልተሰጡም በፍላጎታቸው ጠይቀው የተመለሱ ናቸው ብሏል።
የአማራ ክልል ከተካሄደው የተቃውሞ እንቅስቃሴ በኋላ የመጀመሪያ የሆነው የካቤኔ ሹም ሽር ሕዝቡ ላነሳው ጥያቄ መልስ የሚሰጥ አይደለም ሲሉ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባላት ተችተዋል።
በኮንሶ ሰዎች አሁንም በጅምላ እንደሚታሰሩ፣የኮንሶን ሕዝብ ወክለው ጥያቄ ያቀርቡ የነበሩ የኮሚቴ አባላት የተወሰኑት መታሰራቸውን አብዛኞቹ ደግሞ መኖሪያ መንደራቸውን ትተው መሰደዳቸውን እኛም በስደት ጫካ ገብተን ነው የምናነጋግራችሁ ሲሉ ሁለት የኮንሶ ነዋሪዎች ነን ያሉ ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ።
“የሥራ ዕድሉ በጣም ጠባብ ስለሆነ ዲፓርትመንት ይቀየርልን” ብለው የጠየቁ 102 የጎንደር ዩኒቨርስቲ የእንሳት ፈርማሲ ተማሪዎች ከትናንት በስቲያ አርብ መታሰራቸውን የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።
በምዕራብ ሀረርጌ ዞን የመሰላ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በኦሮሚያ ክልል ከተቀሰቀሰው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በታሰሩ 13 ተከሳሾች ላይ አመፅ በማነሳሳትና ንብረት በማውደም ጥፋተኛ ናቸው ሲል የ11 ዓመት እስራት እና የገንዘብ ቅጣት ፈርዷል። ከፍርደኞቹ መካከል የ15 ዓመት ልጅና እና የስድስተኛ ክፍል ተማሪ እንደሚገኝበት ነዋሪዎቹ ይገልፃሉ።
በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙትና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በዋስ እንዲፈቱ የወሰነላቸው አቶ ደቀቦ ዋሪዮ የተባሉ የ80 ዓመት አዛውንትን ፖሊስ አስሮ አስቀምጧቸዋል ሲሉ ጠበቃውና ልጃቸው ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩና አናኒያ ሶሪ እንዲሁም የቀድሞው አንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ ታሰሩ። መንግስት ሰዎች በመጻፋቸው ምክኒያት አይታሰሩም ብሏል።
“እኔ ገጠር ተቀምጬ ልጆቼን ከተማ ነበር የማኖራቸው፡፡ በታጣቂዎች መገደላቸውን ሰምቼ ወደ ሚኖሩበት ከተማ ስሄድ የሦስቱንም ወንድ ልጆቼን አስከሬን ደጄ ላይ ወድቆ አገኘሁት” - አቶ ጀማል ሁሴን ለአሜሪካ ድምፅ ከተናገሩት የተወሰደ ነው፡፡
መቀመጫውን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው ፍሪደም ሃውስ የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት የ2016 የዓለማት የኢንተርኔት ነፃነት ደረጃን ይፋ ባደረገበት ሪፖርቱ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት የኢንተርኔት ነጻነት በመገደብ አንደኛ ስትሆን ከ65 ሀገራት ደግሞ በአራተኛ ደረጃ ነፃነትን ገዳቢ ሀገር ተብላለች። ቻይና የኢንተርኔት ነጻነት በመገደብ 1ኛ ናት።
አርብ ሕዳር 2 /2009 በደጋሚ የታሰረው የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምደኛ በፍቃዱ ኃይሉ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን ለማስፈፀም በተቋቋመው ኮማንድ ፖስት እዝ ስር እንደሚገኘና የታሰረውም ለአሜሪካ ድምጽ በሰጠው ቃለምልልስ “የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ በሕዝቡ ላይ ጫና ያሳድራል” የሚል ይዘት ያለው ንግግር አድርገሃል ተበሎ እንደሆነ ለጠበቃውና ሊጠይቁት ለሄዱ ሰዎች መናገሩ ታውቋል።
የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምደኛ በፍቃዱ ኃይሉ ዛሬ ማለዳ በድጋሚ ታሰረ። በሽብር ወንጀል ከሌሎች የኢንተርኔት አምደኞች ጋር ታስሮ የነበረውና በ20 ሺሕ ብር ዋስ ተፈቶ ጉዳዩን በውጭ ሲከታተል የቆየ የኢንተርኔት አምደኛው በፍቃዱ ኃይሉ ዛሬ ማለዳ ሲቪል በለበሱ ሰዎች ልዩ ስሙ "ፈረንሳይ" ከተባለው መኖሪያ ቤቱ በኮማንድ ፖስት እንደሚፈለግ ተነግሮት መታሰሩ ታውቋል። አሁኑ በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ እንደሚገኝ ጣቢያው አረጋግጦልናል።
በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የተቀሰቀሰው ተቃውሞና አመጽ አንድ ዓመት ሞላው። በኢትዮጵያ ትልቁን ቁጥር ለሚይዘው የኦሮሞ ማኅበረሰብ የተቃውሞ መነሻ የሆኑት የፖለቲካ ነፃነት እና ፍትሃዊ የምጣኔ ሃብት ክፍፍል ጥያቄዎች ዛሬስ ተመልሰው ይኾን? የአሜሪካ ድምጿ ማርታ ቫንዶርፍ ከብራስልስ ባጠናቀረችው ዘገባዋ ታነሳዋለች።
በኢትዮጵያ በተለይ ወጣቶችን በማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች እንዲነቁ በማስቻሉና በውስጠ ወይራ መልእክቱ የሚታወቀው “ፌስታሌን” የተሰኘው አንድ ሰው ብቻውን የሚተውንበት የሙሉ ሰዓት የመድረክ ተውኔት ወደ ዩናይትድ ስቴይትስ መጥቷል። በትናንትናው ዕለትም ዋሽንግተን ዲስ ውስጥ 900 ሰው ተመልክቶታል።
የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው በምስራቅ ሸዋ ዘን ቦሰት ወረዳ የሚገኙ ወ/ሮ ሎሚ ዋቀዮ የተባሉ እናት አንድ ልጃቸው እንደተገደለ ሁለቱ እንደታሰሩና አንዱ በእጅጉ መደብደቡን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የዛሬ ዓመት አዋቅረውት የነበረውን ካቢኔ ከንድ ዓመት በኋላ አፍርሰው 21 አዳዲስ ሹመቶች የተካተቱበትና የቀድሞ ዘጠኝ ሚኒስተሮችን ባሉበት የሚያቆይ አዲስ ካቢኔ በትናንትናው ዕለት ማዋቀራቸው ይታወሳል። እኛም በትናንትናው ዕለት የተለያዩ ሰዎችን አስተያየት ጠይቀን ማስተላለፋችን ይታወሳል በዛሬው ዕለት በገባነው ቃል መሰረት ሁለትኛውን ክፍል ይዘናል።
የጎብኚዎች ቁጥር መቀነስ የጀመረው በኢትዮጵያ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ከተጀመረ ጀምሮ መሆኑን የተናገሩት የአንዱ አስጎብኚ ድርጅቶቹ ኃላፊ አሁን ደግሞ በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ላይ ወዳለች ሀገር ቱሪስቶች ሊመጡ አይችሉም ብለዋል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የዛሬ ዓመት አዋቅረውት የነበረውን ካቢኔ ከንድ ዓመት በኋላ አፍርሰው በዛሬው ዕለት 21 አዳዲስ ሹመቶች የተካተቱበትና የቀድሞ ዘጠኝ ሚኒስተሮችን ባሉበት አዲስ ካቢኔ አዋቅረዋል። በዚህ ሹመት ላይ የተለያዩ ሰዎችን አስተያየት ጠይቀናል።
የኦሮሞ የሕግ ባለሞያዎች ማኅበር ባሣለፍነው ቅዳሜና ዕሁድ፤ ጥቅምት 12 እና 13/2009 ዓ.ም. ለንደን ላይ ልዩ ጉባዔ አካሂዶ ነበር።
ካሌ ከምትባለው የፈረንሳይ ሰሜናዊ ወደብ አቅራቢያ ከሚገኘውና “The Jungle” ወይም ጫካው ተብሎ በሚጠራው የስደተኞች መጠለያ መንደር ውስጥ የዐስራ አንድ ዓመት ሕፃናት ጭምር አሉ ጭምር እንደሚገኙ በስፍራው የሚገኙ ስደተኞች ገለጹ።
ቪዥን ኢትዮጵያ ፕሬዝዳንትን ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻውን ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ጋር በመሆን ነው ስላዘጋጁት ውይይት ጠይቀናቸዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ