ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች “ካሊ በተባለችው የሰሜን ፈረንሳይ ወደባዊት ከተማ ከሚገኘው የስደተኞች ሰፈር ለቀው እየወጡ ነው። ይህ ጫካው የሚል መጠሪያ ያተረፈው የስደተኞች መንደር ከነገ ጀምሮ መፍረስ እንደሚጀምር እየተነገረ ይገኛል።
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን ተከትሎ እስራት መበራከቱን በዚህም ስጋት ላይ መሆናቸውን በኦሮሚያ ክልል ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገለጹ።
የኢትዮጵያ መንግሥት ስለ አምባገነንነት በሚማሩ የፖለቲካ ሳይንስ ተማሪዎች የመማሪያ መጻሐፍት ላይ በምሳሌነት የሚያስጠቅሰውን ርምጃዎችን እየወሰደ እንደሆነ በኦሪገን ዩኒቨርስቲ የሚዲያ ጥናት የዶክትሬት ተማሪው አቶ እንዳልካቸው ኃይለሚካኤል ለአሜሪካ ድምጽ ገለጸ።
መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም በኢትዮጵያ መንግሥት የታወጀውን አስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ተከትሎ ነዋሪዎች በጅምላ እየታሰሩና ቤታቸውም እየተበረበረ እንዲሁም በተለምዶ አጠራር ዲሽ በመባል የሚታወቁት የሬድዮና ቴሌቭዥን ሞገዶች መቀበያዎች የሚከታተሉበት እንዲነቅሉ እየተገደዱ መሆኑን ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ ነዋሪዎች ይናገራሉ።
በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሰሞኑን የኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጥ መኖሩን ተጠቃሚዎች ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።
በደቡብ ክልል በጌዲኦ ዞን በሦስት ወረዳዎች ባሉ የተለያዩ ከተሞች፤ በዲላ፣ በይርጋ ጨፌ፣በወናጎ፣ በፍስሃገነትና በወረዳዎቹ አካባቢ ባሉ ከተሞች “በተፈጠረ ግጭት ከአካባቢው ተወላጆች በተሰነዘረብን ድንገተኛ ጥቃት ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ሰዎች ተገደሉ፣ ንብረታችን ተቃጠለ አሁን ቤተክርስቲያ ከተጠለልን አራኛ ቀናችን ነው” ሲሉ ያነጋገርናቸው የአካብባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።
በኢትዮጵያ ከቅዳሜ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግና ለስድስት ወር እንደሚዘልቅ ይፋ ስለሆነው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ሁለት እንግዶች አነጋግረናል።
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ የሚገድባቸውን መብቶች ለማወቅ ዝርዝርሩን ማየት እንደሚያስፈለግ የቀድሞው የፍትህ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና መምሪያ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ዘመድኩን ገለጹ።
የሕግ ባለሞያው አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ፣ የኒዩርክ አዮና ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ደረሰ ጌታቸውና ከሜልበርን ዩኒቨርሲቲ ሕግ ፋካልቲ ሪሰርቸር ረዳት መምህር ዶ/ር ጸጋዬ አራርሳ ናቸው ተወያዮቹ ። ያወያየቻቸው ደግሞ ጽዮን ግርማ ናት።
ቀደም ሲል በእስር ላይ ቆይተው ከተለቀቁት የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምደኞች አንዱ የሆነው ናትናኔል ፈለቀ፣ ጸደቀ ድጋፌ እና አዲስ ዓለም ደስታ ከሀገር እንዳይወጡ ታገደው በ5ሺህ ብር ዋስትና ይፈቱ ሲል የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በማጽናቱ ዛሬ በዋስ ተፈተዋል።
ቀደም ሲል በእስር ላይ ቆይተው ከተለቀቁት የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምደኞች አንዱ የሆነው ናትናኔል ፈለቀ እንዲሁም ጸደቀ ድጋፌ እና አዲስ አለም ደስታ ዛሬ በዋስ እንዲፈቱ ፍርድቤት ቢወስንም ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ በማለት ይግባኝ በመጠየቁ ለነገ ተቀጥሯል።
ቀደም ሲል በእስር ላይ ቆይተው ከተለቀቁት የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምደኞች አንዱ የሆነው ናትናኔል ፈለቀ እንዲሁም የዞን ዘጠኝ አባል ያልሆኑ ጸደቀ ድጋፌ እና አዲስ አለም ደስታ ተይዘው መታሰራቸው ታውቋል። የናትናኤል ጠበቃ አቶ አመሐ መኮንን ማምሻውን አነጋግረናቸዋል።
ከሚያስተምርበት የአምቦ ዩኒቨርስቲ ወሊሶ ካምፓስ ቅዳሜ መስከረም 21 ቀን 2009 ዓ.ም ተወስዶ የታሰረው ስዩም ተሾመ በአስቸኳይ እንዲፈታ ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ደህንነት ተሟጋች ድርጅት (CPJ) አሳሰበ።
በቦታው ከነበሩ ጋዜጠኞች አንዱ "እኔ ብቻ ሆስፒታል ውስጥ ተጥለው በነበሩ ድንኳኖች ሰው እንዲለያቸው ተብለው የተቀመጡ ከ50 በላይ አስክሬኖች ቆጥሬያለሁ " ይላል።
በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ኃይቅ ሊከበር በዝግጅት ላይ የነበረውና ከኦሮሞ ክብረ በዓሎች አንዱ የሆነው እሬቻ በዓል ተስተጓጉሏል፤ በግጭትና በትርምሱ ወቅት ብዙ ሕይወት መጥፋቱና በአካልም ላይ ብዙ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል፡፡
በተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ከተማ የሚገኙ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት በዋናነት ያዘጋጁት የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬ በዋሽንግተን ዲስ ውስጥ ተካሂዷል።
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ እና ምዕራብ ወለጋ ውስጥ በመንግስት ታጣቂዎች የሚፈፀም ግድያ መቀጠሉን እንዲሁም በአጄ ከተማ በነዋሪዎችና በታጣቂዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ከሕዝቡም ከታጣቂዎችም ሕይወት መጥፋቱን ነዋሪዎች ገለጹ።
በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ ትናንትና እና ከትናንት በስቲያ ከቃጠሎ የተረፈውን የገበያ ቦታ እና ሌሎች ንብረቶችን ሊያቃጥሉ ነበር ያሏቸውን ግለሰቦች መያዛቸውንና ለፖሊስ ማስረከባቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ። በጎንደር ተጨማሪ የቃጠሎ አደጋ ይደርሳል የሚል ስጋት እንዳላቸውም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በዜጎች ላይ ያደርሰዋል ያሉትን በደል ለማጋለጥ እና የመጻፍ ነፃነትን ለማረጋገጥ ማኅበራዊ ሚዲያ ያበረከተላቸውን አስተዋፆና በየገፆቻቸው ስለ ሠሩት ሥራ ገለፃ በማድረግ አራት የኢንተርኔት ማኅበራዊ ሚዲያ አራማጆች ውይይት አድርገው ነበር።
ተጨማሪ ይጫኑ