ልጃቸው አስከሬን ላይ እንደተደበደቡ ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩት እናት በተባለው ቤት እንደማይገኙ የመንግሥት ኮሙዩኔኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መሐምድ ሰኢድ መናገራቸው ይታወሳል። የዞን ኮሙዩኔኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ደግሞ ሟቹም ኤፍሬምም እናቱም ወ/ሮ ታደሉ የከተማው ነዋሪዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። ኮሙዩኔኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የሉም የተባለው በመረጃ ክፍተት መሆኑን በፌስቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል።
ቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ነበሩ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በኦህዴድ ውስጥ የተደረገው ሹም ሹር ምን እንደምታ እንዳለው አስተያየር እንዲሰጡ ተጠይቀዋል።
በአማራ ክልል በጎንደር እና በባህርዳር ከተማ ከትናንት ጀምሮ የቤት ውስጥ መቀመጥ አድማ እያደረጉ እንደሆን ፤ በባህርዳር ግን መንግሥት ባሰማራቸው ኃይሎች አማካኝነት የባጃጅ አሽከርካሪዎች ተገደው ዛሬ ሥራ እንደጀመሩ የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ።
በጎንደር ከተማ በቅዳሜ ገበያ ላይ ለደረሰው ቃጠሎ ንብረት ውድመት ተጠያቂው መንግሥት ነው ሲሉ የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ነጋዴዎች ተናገሩ። የክልሉ መንግስት እሳቱ የጠፋው ሕዝብና መንግስት ባደረገው ርብርብ ነው ብሏል።
በትናንትናው ዕለት በነቀምት ከተማ ደርጊ ወይም ቀበሌ ሁለት በተባለ ቦታ ባልታወቁ ሰዎች በኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮች ካምፕ ላይ የፈነዳ ቦምብ ጉዳት ማድረሱ ተገለጿል። ከጉዳቱ በኋላ በአካባቢው የተገኘው ሰው ሁሉ ድብደባ ደርሶበታል ሲሉ ነዋሪዎች ያማርራሉ።
የኮንሶ ነዋሪዎች ከ80 ሺሕ ሰው በላይ ፊርማ አሰባስበው በሕዝብ በተመረጡ ዐሥራ ሁለት የኮሚቴ አባላትን አዋቅረው፣ ከልዩ ወረዳነት ወደ ወረዳ ወርደው በሰገን ዞን ስር እንዲጠቃለሉ መደረጋቸውን ተቃውመው፣ እንዳውም ኮንሶ ራሱን ችሎ ዞን ሊሆን ይገባዋል በሚል ያነሱት ጥያቄ፤ እስካሁን ለሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳጋለጣቸው የኮሚቴው አባል ነኝ ያሉ አቶ ገመቹ ጎንፋ ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ።
ባለፈው ሳምንት የእሳት ቃጠሎ ተከስቶበት በነበረው ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ ታሳሪዎች ከቅዳሜ ጀምሮ የሄዱ ጠያቂ ቤተሰቦች ከአምስት ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ብቻ እንዲያዩዋቸው መደረጉን እንዲሁም አንዳንዶቹ ማነጋገር ጭምር እንደተከለከሉ ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።
የኢትዮጵያ መንግሥት በአዲስ ዓመት ዋዜማ ከፈታቸው 720 እሥረኞች መካከል በሽብር ወንጀል ተከሰው ታሥረው የነበሩት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት በአዲስ ዓመት ዋዜማ ከፈታቸው 757 እሥረኞች መካከል በሽብር ወንጀል ታሥረው የነበሩት የሙስሊም ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡
ቅዳሜ ዕለት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የሞተውን ሰው ማንነት ወዲያውኑ ለቤተሰብ ማሳወቅ ይገባ እንደነበር ኢትዮጵያ የፈረመቻቸውን ዓለም አቀፍ ሕጎች ጠቅሰው አቶ ሽብሩ በለጠ የተባሉ የሕግ ባለሞያ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። የእስረኛ ቤተሰቦች በበኩላቸው ዛሬም ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉ ማወቅ እንዳልቻሉ ይናገራሉ።
ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ አደጋ የ23 ሰዎች ህይወት ማለፉን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በሌላ በኩል ቂልንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የእስረኛ ቤተሰቦች ታሳሪ ቤተሰቦቻቸው የት እንደሚገኙ ማወቅ እንዳልቻሉና ሊጠይቁ በሄዱበት ወቅት እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ ለአሜሪካ ድምጽ ገልፀዋል።
በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ስር በሚገኘው ቂልንጦ ማረሚያ ቤት በደረሰው የእሳት አደጋ ምን ያህል ሰው እንደተጎዳ በትክክል ማረጋገጥ አልተቻለም።
በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ውጥረት መቀጠሉን ክልሉ በወታደሮች ቁጥጥር ሥር መዋሉንና፣ ከሰኞ ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ ምን ያህል የሰው ሕይወት እንደጠፋ ፣ ምን ያህል እንደቆሰለ ፣ምን ያህል እንደታሰረ ፣ ምን ያህል ንብረት እንደወደመ የተጣራ መረጃ ለማግኘት ሁኔታዎች ዝግ እንደሆኑበት መኢአድ አስታውቋል።
በአማራ ክልል የተፈጠረው ውጥረት ትናንት እና ዛሬ መባባሱን እና በመተማ የሰው ሕይወት መጥፋቱን በርካታ ንብረት መውደሙን በደብረ-ታቦር ማረምያ ቤት መቃጠሉን በአምቦጊዮርጊስ እንዲሁ የሰው ሕይወት መጥፋቱ በአጠቃላይ በክልሉ አብዛኞቹ ከተሞች የመከላከያ ሰራዊት መግባቱና የተኩስ ድምፅ ያለማቋረጥ መሰማቱን የፓርቲው ተወካዮችና ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ ነዋሪዎች ገለጹ።
በኮንሶ ከልዩ ወረዳነት ወደ ሰገን ዞን መጠቃለላቸውን የተቃወሙ የመንግሥት ሠራተኞችና የህብረተሰቡ ወኪሎች የመንግሥት ሥራ ያቆሙትና ደመወዝም አልቀበልም ያሉት በራሳቸው ፍላጎት እንደሆነ የደቡብ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ።
በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ ግጭቶች ዛሬም መቀጠላቸውን በዚህም የሰው ሕይወት መጥፋቱን የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ ገለጸ።
ጤና ጣቢያዎች ተዘግተዋል። ለደሃ ደሃ የሚሰጥ የምግብ ዋስትና ፕሮግራም ተቋርጧል። የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ተዘግተዋል ብለዋል።
መጽሐፍ አዟሪዎቹ በተለይ የተመስገን ደሳለኝ፣ የሙሉጌታ ሉሌና የዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ መጽሐፍ መሸጥ እንዳልቻሉ እነዚህን መጽሐፍትና ሌሎች የታሪክና የፖለቲካ መጽሐፍት ይዘው ሲገኙ እንደሚደበደቡ፣ እንደሚታሠሩና አንዳንዴም ለመለቀቅ ከደንብ አስከባሪዎች ጉቦ እንደሚጠየቁ ተናገሩ።
ፈይሳ ሌሊሳ እስካሁን 127,465 ዶላር ተስብስቦለታል። ሮቢል ኪሮስ ለ80 ሚሊየን ብር ፕሮጀክቱ 155 እስካሁን ፓውንድ አግኝቷል።
ተጨማሪ ይጫኑ