ከእስር የተለቀቁት አቶ በቀለ ገርባና አቶ ደጀኔ ጣፋ፤ “በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም በእስር ቤቶቹ ውስጥ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት ቃሉን አክብሮ ሁሉንም ሲፈታ ነው ለውጥ የሚመጣው” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዱዓለም አራጌንና አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) ከእስር ለመፈታት የግንቦት ሰባት አባል መሆናቸውን አምነው የይቅርታ ፎርም ላይ እንዲፈርሙ መጠየቃቸውንና ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። የአቶ ክንፈሚካኤል ደበበ እናት ወ/ሮ ብዕዓት ኃይለጊዮርጊስ፤ "እኛም ቤተሰቦቹ ሆነ እርሱ ብዙ መሰዋትነት ከፍለናል። ስለዚህ ይቅርታ ባለመጠየቃቸው በጣም ደስ ብሎኛል።" ብለዋል።
በባሌ ዞን በመዳ ወላቡ ወረዳ "መዳ" በተባለች ቀበሌ የገበያ ቦታ ላይ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በተፈጠረ ግጭት የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉንና ሰባት ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ከሟቾቹ ውስጥም አንዲት የስምንት ልጆች እና አንዲት የሰባት ልጆች እናት ወተት በመሸጥ ላይ እያሉ በመከላከያ በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዱዓለም አራጌንና አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) ከእስር ለመፈታት የግንቦት ሰባት አባል መሆናቸውን አምነው የይቅርታ ፎርም ላይ እንዲፈርሙ መጠየቃቸውን ለቤተሰቦቻቸው ገለፁ። በሌላ በኩል በይቅርታ እንዲፈቱ የተወሰነላቸው 417 ታራሚዎች ዝርዝር ለውሳኔ ወደ ሀገሪቱ ርዕሰ ብሄር መላኩን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ምንጮች ገልፀዋል፡፡
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አቶ አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ 746 እስረኞች በይቅርታና ክሳቸው ተቋርጦ እንዲለቀቁ መወሰኑ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ሰርካለም ፋሲል፤ ዜናውን ከሰማች በኋላ በጣም መደሰቷን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግራለች። የአቶ አንዷለም አራጌ ባለቤት ዶ/ር ሰላም አስቻለው በበኩሏ ካየች ብኋላ እንደምታረጋግጥ ተናግራለች።
የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በቀድሞ ፓርቲያቸው ኦሕዴድ የአንድ ጊዜ ስጦታ ሊያበረክትላቸው እንደሆነ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ። ይህ ውሳኔ እስካሁን ሲያነሱት ት ከነበረው የመብት ጥያቄ ጋ የሚገናኝ እንዳልሆነ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ለሰልፍና ለተቃውሞ አደባባይ የሚወጡ ሰዎች ሲገደሉ እንዲሁ በሰልፉ ላይ ተሳታፊ ሳይሆኑ በተባራሪ የሚገደሉ ሰዎችን በተመለከተ ገዳዮቻቸው ሊጠየቁበት የሚችሉበት ሕግ አለ ወይ? ካለስ በምን መልኩ ሊጠየቁ ይችላሉ? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎችን ይዛ ጽዮን ግርማ ሦስት የሕግ ባለሞያዎችን አነጋግራለች።
በወልዲያ፣ በመርሳ፣ በቆቦና በሌሎች የዞኑ ከተሞች የሚታሰሩ ሰዎች ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ።የክልሉ መንግሥት ሕይወት በማጥፋት፣ አካል በማጉደልና ንብረት በማውደም የተጠረጠሩት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን አረጋግጧል።
ዛሬ ጠዋት በአዳማ ከተማ ቀበሌ 13 አቅራቢያ በሚገኛና በተለምዶ “የጨረቃ ቤት” እየተባለ የሚጠራ መንደርን ለማፍረስ በተሰማራ ግብረ ኃይልና በነዋሪዎቹ መካከል በተፈጠረ ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱንና ሰዎችንም በታጣቂዎች መደብደባቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ። ሟቾቹን በተመለከተ ከክልሉ መንግሥት ያገኘነው መረጃ የለም።
በሰሜን ወሎ በወልዲያ፣ በመርሳ፣ በቆቦና በሌሎች የዞኑ ከተሞች ከተፈጠረው ግጭት በኋላ ዛሬም ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።
በምንሊክ ሆስፒታል የመረመራቸው ሃኪም ተጨማሪ ሕክብና በአስቸኳይ የማያገኙ ከሆነ ለሁልጊዜ ማየት ሊከለክላቸው እንደሚችል በሃኪም እንደተነገራቸው ልጃቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግራለች። ማረሚያ ቤቱ ወደ ግል ሆስፒታል ሊወስዳቸው እንደማይችል እንደገለፀላቸውም ጠቁማለች።
በሰሜን ወሎ በወልዲያ፣ በመርሳ፣ በቆቦና በሌሎች የዞኑ ከተሞች ውጥረት እስከዛሬ መቀጠሉንና ወጣቶች ከየቤቱ እየተለቀሙ እየታሰሩ መሆኑን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገለጹ።
በሰሜን ወሎ ዞን እስካሁን ውጥረት መንገሱን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል። በወልዲያ፣ በቆቦ በመርሳና የንግድና የሥራ እንቅስቃሴ መቋረጡን ትምሕርት ቤት መዘጋቱን ነዋሪዎቹ ጨምረው ተናግረዋል።
በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ ከማክሰኞ ጀምሮ በተቀሰቀሰ ተቃውሞና ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱን ንብረት መውደሙ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት ወጣቶች ከየቤታቸው እየታሰሩ መሆኑን ነዋሪዎች ገልፀዋል። የክልሉ ፕሬዝዳንት ችግሩ የፓርቲው ነው ብለዋል። በስደት ላይ የሚገኘው ሲኖዶስ የወልዲያን ግድያ አውግዟል።
በቆቦ ከተማ ለሁለት ቀናት በተደረገ ተቃውሞና ግጭት እስካሁን ሰባት ሰዎች መሞታቸውን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልፀዋል። ከተቃውሞው በኋላ በርካታ ንብረቶች በቃጠሎ መውደማቸንና በአሁኑ ሰዓት ከተማው በመከላከያ ሠራዊት በቁጥጥር ስር መዋሉን ነግረውናል።
በዛሬው ዕለት ቁጥራቸው የበዛ የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ለተቃውሞ ሰልፍ አደባባይ መውጣታቸው ታውቋል። የተቃውሞው ምክኒያት የመሰረተ ልማት እጦት መሆኑን የሰልፉ ተሳታፊዎችና የከተማው ነዋሪዎች ነግረውናል።
ሞያሌ ከትናንት በስቲያ አንድ የ20 ዓመት ወጣት በመከላከያ ፖሊስ መገደሉንና ሦስት ወጣቶች መቁሰላቸውን የወረዳው አስተዳዳሪ ገለጹ። ከቆሰሉት መካከል የስድስት ዓመት ልጅ እንደሚገኝበት ተናግረዋል።
ከኢትዮጵያ ሶማሌና ከሶማሌላንድ የተለያዩ ከተሞች የተባረሩ ተፈናቃይ የኦሮሞ ተወላጆች፤ በባሌ ዞን ውስጥ የምግብ እጥረትን ጨምሮ ለተለያዩ ችግሮች መጋለጣቸውን ገለጹ። የዞኑ አስተዳዳሪ ፤ “እርዳታ እየሰጠንና የተቻለንን እያደረግን ነው ለሁሉም ግን በቂ ነው ማለት አንችልም።” ብለዋል።
በእስር ላይ የሚገኘው ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ኦክስፋም ኖቪብ እና ፔን ኢንተርናሽናል በተባሉ ሁለት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የ2018 ተሸላሚ ሆኗል።
የሽብር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸውና በጥፋተኝነት ውሳኔ እስር ተፈርዶባቸው የነበሩት ሁለት ጋዜጠኞች ዳርሴማ ሶሪና ካሊድ መሐመድን ጨምሮ ስድስት የሙስሊም ጉዳዮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ዛሬ በአመክሮ ከእስር መለቀቃቸውን ተናገሩ።
ተጨማሪ ይጫኑ