ለ18 ቀናት ስብሰባ የተቀመጠው ገዢው ፓርቲ በመጨረሻ ቅዳሜ ዕለት ያወጣውን የጹሑፍ መግለጫ በተመለከተ የተለየያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ይገኛሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ትምሕርት መምሕር ረዳት ፕሮፌሰር አቶ አበባው አያሌው ከአዲስ አበባ፣ አቶ አሉላ ሰለሞን ከዋሽንግተን ዲሲና አቶ ገረሱ ቱፋ ከአምስተርዳም በመግለጫው ላይ ተወያተዋል።
የሰብዓዊ መብት ተከራካሪው አቶ ያሬድ ኃይለማርያምና የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት ጸሐፊው በፍቃዱ ኃይሉ በየትኛውም ቋንቋ ቢገለፅ ኢትዮጵያ ውስጥ ቁጥራቸው እንኳን በግልፅ የማይታወቅ የፖለቲካ እስረኞች መኖራቸውን ይናገራሉ።
እስረኛ መፍታትና ማዕከላዊን መዝጋትን የተመለከተው የኢሕአዴግ መግለጫ በአነስተኛ ዋጋ ብዙ ትርፍ ሊያስገኙ የሚችሉ በፖለቲካው ዓለም ሁለት ስስ ጉዳዮች የተመረቱበት እንደሆነ የቀድሞው የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጅ መስፍን ነጋሽ ይናገራል። "ከማሰር ይልቅ መፍታቱ ሕግና ደንብን መከተል እንዳለበት እየተነገረን ነው" የምትለው ደግሞ የአዲስ ስታንዳርድ ዋና አዘጋጅ ፀዳለ ለማ ናት። የውይይቱን ሙሉ ክፍል አድምጡት።
በአዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተወለደው ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊ ረቡዕ ታኅሣሥ 25 ቀን 2010 ዓ.ም በናይሮቢ ከተማ ላንጋታ በተሰኘው ቦታ ልክ በ40ኛ ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ዛሬ አርብ ታኅሣሥ 27 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ በኮልፌ እስላም መቃብር የቀብር ሥነ ስርዓቱ ተፈጽሟል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ለዘመናት ሲክደው የነበረውን የፖለቲካ እስረኞች አምኖ ለመፍታት መወሰኑ የሚያስደስት ነው ያሉ ከዚህ ቀደም ታስረው የተፈቱ ሦስት የኢንተርኔት አምደኞች፤ “ነገር ግን ጉዳዩ እንደተለመደው የፖለቲካ ማታለያ ሆኖ እንዳይቀር ውሳኔው ግልጽ ሊደረግና በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ እስር ቤቶች በየትኛውም የፖለቲካ አመለካከታቸው የታሰሩ ሰዎች በአስቸኳይ ሊፈቱ” ይገባል ብለዋል።
በሀገሪቱ የተቃውሞ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚታወቁት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስና ሰማያዊው ፓርቲ “መግለጫው ምንም አዲስ ነገር የለውም የተለመደው አዘናግቶ መግዢያና አምባገነንነትን ማስቀጠያ ነው” ብለውታል።
በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሻምቡ ከተማ ውስጥ ዛሬ ጠዋት በተነሳ ግጭት በተኩስ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ አራት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
ዘመቻው ማረሚያ ቤቱ ውስጥ እየተፈፀመ ያለውን የመብት ጥሰት ምስል ያሳየ ነበር ያሉት አስተባባሪዎቹ ለአንድ ቀንም ቢሆን ብዙ ሰው የተሳተፈበትና የእስረኞቹ ታሪኮች የተነገሩበት ነው ብለዋል።
እስረኞቹ በምርመራ ወቅት አሰቃቂ ተግባር እንደተፈፀመባቸና ይህንንም ችሎት በሚቀርቡበት ወቅት እንደሚናገሩ አንዳንዶቹም ልብሳቸውን ገልጠው የተጎዳውን የሰውነታቸውን ክፍል ለችሎት እንደሚያሳዩ ጠበቀቻቸው ተናግረዋል።
"መታከምም ሆን ማንበብ ተከልክሏል" የምትለው በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበር ልጅ ወ/ት ቦንቱ በቀለ አባቷን ልትጠይቅ ስትሄድ መታመማቸውን እንደነገሯት ተናግራለች።
ተዋናይት፣ድምፃዊት፣የፋሽን ባለሞያና ዳይሬክተር በአሜሪካ ድምፅ ስቱዲዮ ተገኝታ ስለ ሥራዋ አጫውታናለች።
99 በመቶ በኢሕዴግ አባላት የሚመራው የኢትዮጵያው ፓርላማ አባላት ሰዎች ከቀያቸው እየተፈናቀሉና እየሞቱ ውይይት ሊደረግ አይገባም ሲሉ ለዛሬ ተጠርቶ የነበረውን የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም በተመለከተ የተዘጋጀን የዐዋጅ ረቂቅ ውይይት ላልተወሰነ ጊዜ አራዘሙት።
ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከሰቱ ላሉ ግጭቶች፣ሞቶችና ንብረት መውደምን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ቀርበው ማብራሪያ ሊሰጡን ይገባል ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄ ማቅረባቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። ለጥያቄዎችቻቸው ቀርበው ምላሽ ካልሰጧቸው ሥራቸውን መቀጠል እንደሚሳናቸው መናገራቸውን ጠቁመዋል።
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞችና ወረዳዎች ውስጥ “ግድያ ይቁም” የሚል መልዕክት ያነገቡ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ እያካሂዱ መሆኑን ገለፁ። በተለያየ ከተማ የሚገኙ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ እንደተናገሩት በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየጠፋ ያለው የሰው ሕይወት እንደዲቆም የሚጠይቅ ሰልፍ እየተካሄደ ነው ብለዋል።
በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ውስጥ በሁለት ወረዳዎች በሁለት ቀን ብቻ 32 የሶማሌ ብሔረሰብ አባላትና 29 የኦሮሞ ብሄረሰብ አባላት ሕይወት ማለፉን የክልል ባለሥልጣናት እየተናገሩ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ የተፈፀመ ግድያ ነው ያሉብት ጋዱሉ ውስጥ ፖሊስ ጣቢያ እንደሌለ የዞኑ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ገለፁ።
በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በሐዊ ጉዲና ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች ውስጥ የሶማሌ ክልል የታጠቁ ኃይሎች ገብተው ከ80 በላይ የአርሶ አደር ቤቶች ማቃጠላቸውንና እስካሁን ቦታውን ተቆጣጥረው መያዛቸውን የዞኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ተናገሩ። በሌላ በኩል ጋዱሎ በተባለ ቀበሌ ላይ በዚህ የተበሳጩ የሟች ቤተሰቦች የኢትዮጵያ ሶማሌዎችን ማጥቃታቸውን መረጃ እንደደረሳቸው ተናግረዋል።
በአዲግራት ዩኒቨርስቲ በተማሪዎች መካከል በአንድ ዘፈን ምክኒያት ቡድን የለየና ብሔርን ያማከለ ግጭት ተነስቶ የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱን ተማሪዎችና ባለሥልጣናት አስታወቁ። ግጭቱ ወደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ተዛምቷል ተብሏል።
“በሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስና ሚሊሺያዎች አማካኝነት የሚደርሱ ጥቃቶች አሁንም አልተቋረጡም ” ሲሉ ነዋሪዎች አማረሩ
የአረና ትግራይ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ አምዶም ገ/ስላሴ ሲሆኑ ሁለተኛው የአምቦ ዩኒቨርስቲ ወሊሶ ካምፓስ መምሕሩ አቶ ስዩም ተሾመ ናቸው።
የሟቾቹ የቀብር ሥነ ሥርዓት አንዱ በወልዲያ አንዱ ደግሞ በማይጨው መፈፀሙ ታውቋል። ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መቁሰላቸውና ከ200 ሰው በላይ የንብረት ውድመት እንዳጋጠመው የክልሉ መንግሥት አስታውቋል።
ተጨማሪ ይጫኑ