በዚህ ምክኒያት ፍትሕ የማግኘት መብታቸው እንደተጣሰና በማረሚያ ቤት ይደርስብናል የሚሉትን በደል እንኳን በአግባቡ ማመልከት እንዳልቻሉ ጠበቃው ገልፀዋል።
የሕወሓት ሹም ሽርም ሆነ እግድ አንዱ ሥርወ መንግሥት ገርስሶ ሌላ ሥርወ መንግሥት ሥልጣን እንዲይዝ ያደረገ የአንድ ፓርቲ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ነው ሲሉ አቶ ገብሩ አስራት ተቹ።
በዩኒቨርስቲዎች ትምሕርት መቋረጡንና የሰዎች ሞት አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና ነዋሪዎች ይናገራሉ።
በእናቶች ሞት ቅነሳ ከፍተኛ አስተዋፆ ካበረከቱ በኋላ ሞያቸውንና ራሳቸውን ለማሳደግ የሚችሉበት ከፍተኛ ትምሕርት እንዳያገኙ መከልከላቸውን፣ ይህን ለማድረግ የሚያችል የትምሕርት ክፍል እንደሌለም በኢትዮጵያ የተቀናጀ ድንገተኛ ቀዶ ሕክምና ሞያተኞች ገለጹ። የጤና ጥበቃ ሚኒስትር መሥሪያቤት ሚኒስትሮች በተቀያየሩ ቁጥር የተገባላቸው ቃል እንደታጠፈም ተናግረዋል። “ታማኝ አገልጋይ ብቻ ተደርገን የተተውን ሰዎችን ነን”ሲሉም አማረዋል።
የሳውዲ አረቢያ መንግስሥት በሙስና ከጠረጠራቸውና በቁም እስር ከሚገኙት የመንግሥት ባለስልጣናትና ነጋዴዎች መካከል የሚገኙት ኢትዮጵያዊ ትውልድ ያላቸው የሳውዲ ቱጃር ሼክ ሞሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ በሳውዲ መንግሥት እየተመረመሩ መሆኑንና የታገደው ንብረታቸው ከሳውዲ ውጪ ያለን አያካትትም ሲሉ ለንደን የሚገኙት የሼኩ ቃል አቀባይ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
የብሔራዊ ደኅንነት እና መረጃ አገልግሎት ከኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ስልክ ላይ ቀድቸዋልሁ በሚል በጹሑፍ ያቀረበውን ሪፖርት በጽምጽ ያቅርብ ሲል የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ። ከኮሎኔሉ ጋር ስለ ሽብር ያወራሉ የተባሉት ሁለት ሰዎች ስልክ ቁጥርም እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
በአማራ ክልል በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በአረርቲ ከተማ አስተዳደር ለ15 ቀናት ያህል መብራት በመጥፋቱ ምክኒያት ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸውን ገልፁ። ሰልፉም ወደ ግጭት አምርቷል።
አረና ትግራይ ቅዳሜ ዕለት በመቀሌ የጠራው ሰልፍ በፀጥታ ኃይሎች አማካኝነት የታወከ እንደነበር ገልፆ ነገር ግን በብሔር ላይ ያነጣጠር ግድያ ይቁም፣እኛ ኢትዮጵያውያን አንድ ነን፣ ሕወሓት የትግራይ ሕዝብን አይወክልም የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን የያዘ ሰልፍ መካሄዱን አስታውቋል።
ኢትዮጵያው ትውልድ ያላቸው አል-አሙዲ በኢትዮጵያ ቁጥር አንድ የግል ኢንቨስተር ሲሆኑ፤ በኢትዮጵያ የሚወክሏቸው የግል ጠበቃ መታሰር፤ አለመታሰራቸውን ሳያረጋግጡ፤ ዜናውን እንደማንኛውም ሰው እንደሰሙ እስከ ትናንት ጠዋት ድረስ በስልክ እንዳገኟቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
በብሔር ላይ የሚደረግ ጥቃንት ለማውገዝ እንደሆነ ገልፆ ሕዝቡ ሰልፉ ላይ እንዳይገኝ ጫና እየተደረገበት ነው ብሏል።
አማራና የኦሮሞን ሕዝብ ትስስር ለማጠናከር በባህርዳር ጉባኤ ይካሄዳል። የሁለቱን ክልል ቃል አቀባዮች አነጋግረናል።
በሌላ የፍርድ ቤት ዜና የአቶ ዮናታን ተስፋዬ የይግባኝ ክርክር ተሰምቷል የአቶ ማሙሸት አማረ የክስ መቃወሚያ ደግሞ ውድቅ ተደረጓል።
ኦሮመኛ ድምፃዊት ሴና ሰለሞንን ጨምሮ ሰባት የኪነጥበብ ባለሞያዎች በማረሚያ ቤት ያለውን አያያዛቸው ሰብዓዊ መብትን የጣሰ መሆኑን በመግለጽ አማረሩ። "ከዚህ ማረሚያ ቤት ተርፈን የምንወጣ አይመስለንም” ብለዋል።
የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪ የሞተው ሰው ዐሥር መሆኑን ሲናገሩ የክልሉ መንግሥት ስምንት ነው ብሏል።
በማረሚያ ቤት የሚደርሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለፍርድ ቤት አቤት በማለቷ በማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣት ለችሎት ገለፀች።
ባሳለፍነው ሳምንት በቤንሻንጉል ክልል በተፈጠረ ግጭት የስምንት ሰው ሕይወት ማለፉ ተነግሯል። በነቀምቴም እንዲሁ የሦስት ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል።
ከ15 ሰው በላይ ቆስሏል ብለዋል። የሰራዊቱ አባላት እርምጃን ተከትሎ ሰልፈኞች በቁጣ የጭነት መኪናዎችን ማቃጠላቸውን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ውስጥ እየተከሰተ ላለው ግጭትም ሆነ ችግር ተጠያቂው ኢሐዴግ ነው ሲሉ የመድረክ ስራ አስፈፃሚ አባላት ገለፁ።
በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል በዋለው ችሎት በእነ ብስራት አበራ መዝገብ ከቀረቡት ተከሳሾች መካከል አለማየሁ ዋቄ የተባለ ተከሰሽ እስር ቤት ውስጥ በድብደባ ሕይወቱ ማለፉን አብሮት ተከሶ የነበረ እስረኛ ለችሎት አስረድቷል።
ሰሞኑን ግጭት ከተቀሰቀሰበት የኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ጮራ ወረዳ የተፈናቀሉ ነዋሪ ንብረታቸው ተቃጥሎ ሸሽተው ወደ መጠለያ መግባታቸውን ገልፀው፤ “አሁን በአብዛኛው ቦታ መረጋጋት ቢታይም በአንዳንድ ቦታዎች ግን ግጭቱ አለ” ብለዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ