የ12 ሰው ሕይወት ጠፍቷል፣ 14 ሰው ቆሏል፣ 52 ቤት ተቃጥሏል እንዲሁም ከ1500 ሰዎች በላይ ተፈናቅለዋል ተብሏል።
በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች ውስጥ ሰሞንኑ የተደረጉ ሰልፎች ከተለያዩ ክልሎችና የኦሮሚያ ከተሞች ሆን ብለው በተደራጁ ሰዎች የተመሩ መሆናቸውን መረጃ እንደደረሰው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ።
የ93 ዓመቱ የቀድሞው አምባሳደር፣ጋዜጠኛና ዲፕሎማት አምባሳደር አሃዱ ሳቡሬ በሕይወታቸው መጨረሻ ወዳደጉበት ድሬደዋ መሄድ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ። በእኔ ዘመን " እጅግ ሰላማዊ የሆነ የማኅበረሰብ ትሥሥር ነበር" በማለት በአሁኑ ሁኔታ ይቆጫሉ። ከጽዮን ግርማ ጋር ተወያይተዋል።
ጋቢና ቪኦኤ - የጋቢና ጉዞ በሚል ላዘጋጀው ፕሮግራም በሲያትል በግዙፎቹ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በጎግል፣ ቦይንግ፣ አማዞን፣ በኢንሹራንስ ኩባንያና በሌሎች ድርጅቶች ውስጥ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ከሚሠሩ ወጣቶች ጋር ተወያይቷል። ወጣቶቹ ስለ ሕይወትና የሥራ ልምዳቸው አካፍለውናል። የውይይቱ አዘጋጅና አቅራቢ ጽዮን ግርማ ናት። (ክፍል ሁለት)
ጋቢና ቪኦኤ - የጋቢና ጉዞ በሚል ላዘጋጀው ፕሮግራም በሲያትል በግዙፎቹ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በጎግል፣ ቦይንግ፣ አማዞን፣ በኢንሹራንስ ኩባንያና በሌሎች ድርጅቶች ውስጥ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ከሚሠሩ ወጣቶች ጋር ተወያይቷል። ወጣቶቹ ስለ ሕይወትና የሥራ ልምዳቸው አካፍለውናል። የውይይቱ አዘጋጅና አቅራቢ ጽዮን ግርማ ናት። (ክፍል ሁለቱን እዚሁ ገፅ ላይ ታገኙታላችሁ)
በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ እንቅስቃሴ መቀጠሉንና የሰው ሕይወት መጥፋቱን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገለፁ።
ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ እኛም ከሚዲያ ነው የሰማነው ብለዋል
በጣና ሐይቅ ላይ ያንዣበበ በ"አንቦጭ" አረም የመጥፋት አደጋ ያሳሰባቸው የኦሮሚያ ክልል ወጣቶች በጣና ሰንብተው ነበር። በዚህ ላይ የተሳተፉ የሁለቱን ክልል ወጣቶች አነጋግረናል።
“ከዛሬ በኋላ የሚታሰረው እስር ‘ሕገ ወጥ’ ነው” ሲሉ ጠበቃው አቶ አመሐ መኮንን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ቤተሰቦቹና ጠበቃውን አነጋግረናል።
ግጭቱን ለመፍታት እየሠራን ነው ብለዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ከትናንት በስተያ በሰጡት መግለጫ ከሥልጣን ለመልቀቅ እንደምክንያት ባቀረቡት ጉዳይ ውስጥ ውኃ የሚቋጥር ቁም ነገር ሳይኖር እንደማይቀር ዶ/ር ነገሪ አመላክተዋል።
የቀድሞው ብቸኛ የፓርላማ አባል አቶ ግርማ ሰይፉና ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ደረሰ ጌታቸው አስተያያየት አላቸው።
የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንትና የአሁኑ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ስማቸውና ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አንድ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።
አሜሪካ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ከሚሠማሩባቸው የሥራ ዘርፎች አንዱ የታክሲ አገልግሎት ነው። ጽዮን ግርማ በአትላንታ ቆይታዋ ከባለታክሲው በቃሉ አዳነ ጋር በጥቂቱ ተጨዋውታለች።
በፓርቲያቸው ስም ምንም ዓይነት መግለጫ እንዳይሰጡ፣ ከቤት እንዳይወጡና ሥራ እንዳይሠሩ ከተደረጉ አንድ ዓመት ከዘጠኝ ወር እንደተቆጠረ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
የአሜሪካ ድምፅ ጋቢና ቪኦኤ የተሰኘው የወጣቶች ፕሮግራም ዝግጅት በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ተዟዙሮ ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለሞያዎች ጋር ተወያይቷል።አንዱ ውይይት በሲያትል ከተማ በቴክኖሎጂ ዙሪያ የተደረገ ነው።ፕሮግራሙን ያዘጋጀችውና ውይይቱን ያካሄደችው ጽዮን ግርማ ነች።የውይይቱን ሙሉ ክፍል ከቪዲዮው ላይ ታገኙታላችሁ።
በአማዞን የፍይናንስ ማናጀር የሆነችው ወ/ሮ አጋር መኩሪያ፣ ከታክሲ ሥራ የማይክሮሶፍት የአይቲ ግሎባል ሰርቪስ ኢንጅነሪንግ ዳይሬክተር አቶ መኮንን ካሳ እና የቦይንግ ኳሊቲ ኢንጂነር ከሆነው ዶ/ር እሸቱ እንየው ጋር ጽዮን ግርማ ያደረገችው ውይይት::
የአሜሪካ ድምፅ የወጣቶች ፕሮግራም ጋቢና ቪኦኤ በመንገድ ላይ በሚል ላዘጋጀው ፕሮግራም በአራት የአሜሪካ ከተሞች በመዘዋወር ከወጣቶች ጋር ተወያይቷል።በዩኒቨርስቲ ውስጥ በኃላፊነት ከወጣቶች ጋር ከምትሠራ ወጣት ፣የማስታወቂያ ክሬቲቭ ዳይሬክተርና ከጸሐፊና ፕሮዲዮሰር ጋር የተደረገ ውይይት ነው።ውይይቱን ያዘጋጀችውና ያወያየችው ጽዮን ግርማ ናት።
የአሜሪካ ድምፅ የወጣቶች ፕሮግራም ጋቢና ቪኦኤ በመንገድ ላይ በሚል ላዘጋጀው ፕሮግራም በአራት የአሜሪካ ከተሞች በመዘዋወር ከወጣቶች ጋር ተወያይቷል። የመጀመሪያው ውይይት በአትላንታ ከተማ የተካሄደ ሲሆን ውይይቱን ያዘጋጀችውና ያወያየችው ጽዮን ግርማ ናት። ይህ የውይይቱ ሁለተኛና የመጨረሻ ክፍል ነው።
የአሜሪካ ድምፅ ጋቢና ቪኦኤ ለተሰኘው የሬዲዮ ፕሮግራም በአራት የተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች ውይይቶችን አዘጋጅቷል። የመጀመሪያው በትምህርት ጉዳይ ላይ በአትላንታ የተካሄደው ሲሆን አዘጋጅታ ያወያየችው ጽዮን ግርማ ነች። የውይይቱን የመጀመሪያ ክፍል ተከታተሉት። (ሁለተኛውን ክፍልም በድረ ገፃችን ላይ ታገኙታላችሁ።
በመድረኩ ላይም ምርቃትና ንግግር የሚያደርጉት አባ ገዳዎች ብቻ ናቸው ብለዋል። የዛሬ ዓመት በተከበረው የእሬቻ በዓል ላይ የበርካቶች ሕይወት መጥፋቱ ይታወሳል።
ተጨማሪ ይጫኑ