ዋሽንግተን ዲሲ —
የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የይቅርታና የክስ ማቋረጥ እንደሚያደርግ በወሰነው መሰረት እስረኞች ከእስር መለቀቅ መጀመራቸውን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እያስታወቀ ይገኛል። በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንዶቹ የግንቦት ሰባት አባል መሆቻቸውን አምነው እንዲፈርሙ ሲጠየቁ፣ የተወሰኑት እስረኞች ክሳቸው ሲቋረጥ ሌሎቹ ደግሞ የይቅርታ ደብዳቤ እየፈረሙ እንደሚገኙ የታሳሪ ቤተሰቦች ይናገራሉ። አንዳንዶቹ ከማረሚያ ቤት ወጥተው ለተሃድሶ ስልጠና መግባታቸውም እየተሰማ ነው።
ጽዮን ግርማ የተወሰኑትን የእስረኛ ቤተሰቦች አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ