የአገር ፈተናዎች፥ የመውጫ መንገዶችና ተሥፋ፤ አንጋፋው የኢትዮጵያ ጉዳይ አዋቂ፥ ደራሲና የመብት ተሟጋች ፕሮፈሰር መስፍን ወልደማሪያም ትላንትናችንን፥ ዛሬንና ነገን፤ መንታ መንገድ ላይ ያለች በምትመስለው ሃገር ሰሞንኛ ይዞታ ውስጥ ይቃኛሉ።
“ኢትዮጵያ የሚያማታ መንገድ ላይ እንዳለች በግልጽ ያሳያል። የመጀመሪያው መፍትሔ የሚሆነው የቆየውን የዓመታት ጥያቄ መፍታት ነው። ይሄ ለሃገሪቷም ሥልጣን ላይ ላለውም ፓርቲ ለሌሎችም ስለ ኢትዮጵያ ለሚቆረቆሩ ሁሉ እስትንፋስ የሚሰጥ ነው።” ዶ/ር አሰግድ ሃብተወልድ የሥራ አመራር ሥልጠና ባለ ሞያ ከዋሽንግተን ዲሲ።
“በኃላፊነት መወጣት አለብን። በምንሠራው ሥራ ነው የባህላችንን የጥያቄያችንን ትልቅነት ማሳየት ያለብን። በአገራችን ”ወደ ገነት በሲኦል በኩል አይኬድም” የሚል አባባል አለ” አቶ ዳንኤል ክብረት
“ከተሞች በፍጥነት እያደጉ ነው፤ እንቅስቃሴውም እንዲሁ። የአለማችን አየር ንብረት ለውጥ በወባ ትንኝ ምክንያት ለሚከሰቱ በሽታዎች መስፋፋት የራሱ የሆነ አስተዋፆ እያደረገም ይገኛል። ነገርግን ክትባቶችን በበቂ በማዳረስ ልንቆጣጠረው እንችላለን ብዬ አስባለሁ። ስለዚህ አላማችን በአለም ከመስፋፋቱ በፊት እንዴት ልንቆጣጠረው እንችላለን የሚለው ነው።” ታሪክ ጃሳርቪክ የዓለም ጤና ድርጅት ቃል አቀባይ።
ሂላሪ ክሊንተን የዴሞክራቲክ ፓርቲያቸው እጩ ሆነው ተመረጡ። በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት የአንድ አብይ ፓርቲ ፕሬዝዳንታዊ እጩ በመሆንም ታሪክ ሠሩ።
“ከዚህ ቀደም ማንም! ወንድም ሆነ ሴት፤ እኔ አይደለሁም! ቢል አይደለም! ማንም! ይህችን አገር ለመምራት የሂላሪን ያህል ብቃት ኖሮት አያውቅም!” የዩናይትድ ስቴሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ “ተተኪዬ” ስላሏቸው ሴናተር ሂላሪ ክሊንተን የተናገሩት።
“እንደምን ዋላችሁ ልዑካን! አንዳች ታሪክ እውን ልናደርግ ተዘጋጅተናል?” የኦሃዮ ክፍለ ግዛቷ ዲሞክራት ማርሻ ፈጅ፤ የዲሞክራቲክ ፓርቲው ልዑካን ሂላሪ ክሊንተንን የፓርቲው እጩው ያደረጉበትን ድምጽ ለመስጠት በተሰናዱበት ያቀረቡት ሃሳብ አዘል ጥያቄያቸው።
“ተምሳሌት“ የስድሳ አራት በስራቸውና በበጎ ተግባራቸው የሚጠቀሱ ኢትዮጵያዊያን ታሪክ የያዘው መጽሐፍ በቅርቡ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ምክርቤት ቤተ መጻህፍት ተመረቀ።
“ብሪታንያ በአውሮፓ ሕብረት አባልነቷ ትቀጥል ወይስ ትውጣ?” ለሕዝበ ውሳኔ የታጨ ምርጫ፤ ቆይተው ከሚለዩት የሁለት ወገን ጥያቆዎችና ሥጋቶች ዛሬ በዜጎች ብይን የተሰጠባቸው፤ የነገው ዕውነታ መሠረቶች ሆነዋል።
የሳምንቱ የእረፍት ጊዜ የእሁድ ምሽት የመዝናኛ ምርጫችሁ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ።
የዩናይትድ ስቴትስ መንግስትና በዓለም ዙሪያ በርካታ አገሮች ከፍተኛ ትኩረት ቢሰጡትም፤ ዓለም አቀፍ ሽብር፤ በተለይም በሽብር ተዋናይ ግለሰቦች በተናጠል የሚፈጸም የሽብር ጥቃት አሁንም አደጋ ደቃኝነቱ እንዳለ፣ ለመንግስታትም አዳጋችነቱን የእሁዱ የኦርላንዶ ፍሎሪዳ ግዛቱ ጥቃት ማረጋገጡ ተዘገበ።
"በህገወጥ መንገድ ስደተኞችን ከሃገር ወደ ሃገር በማስተላለፍ ወንጀል ተጠርጥሮ የተያዘው ግለሰብ በወንጀለኝነት የሚፈለገው ትክክለኛው ሰው አይደለም" የሚሉ ድምፆች እየተሰሙ ነው። ተጠርጣሪውን መከታተልና በቁጥጥር ስር በማዋሉ ስራ የተሳተፉት የብሪታንያንና የጣልያን የደህንነት ባለስልጣናት በበኩላቸው በጉዳዩ ላይ አስቸኳይ ምርመራ መያዛቸው ተዘግቧል።
“ብጥብጥና ቀውስ እንዲቀሰቀስ፥ አለያም ለገዛ ራስ አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር ሲባል ከግጭት ቋፍ በሚያዳርሱ መንገዶችን አንገፋም፤ ነው ያሉት። እውነትና ፍትህ እንዲረጋገጥ እንሻለን። ለዚህም ነው የምርጫ ኮምሽኑ ሊቀመንበር ኃላፊነታቸውን በፍጥነት ለማስረከብ መዘጋጀት አለባቸው፤ የምንለው።” የተቃዋሚው መሪ Raila Odinga
“ትምባሆን በትክክለኛ ምንነቱ በግልጽ የሚያሳይ ነው። በተባለው መንገድ ጥቅም ላይ ሲውል ከተጠቃሚዎቹ የገሚሱን ያህል ሕይወት የሚቀጥፍ በዓለም ብቸኛው ህጋዊ ሸቀጥ ነው።” Douglas Bettcher ባለሙ ጤና ድርጅት የተለላፊ በሽታዎች መከላከያ ፕሮግራሞች ዲሬክተር
ዲሬክተሩ ማትሺዲሶ ሞዊቲ በተለይ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፤ የ2014ቱ ኢቦላ ወረርሽኝ ዋነኛ ተጠቂዎች፥ ላይቤሪያ፥ ሴራሊዮንና ጊኒ በበሽታዎች ክትትል፥ የላቦራቶር ምርመራ እና የጤና ክብካቤ አገልግሎት አቅማቸውን በወጉ በማጎልበታቸው ለመሰል ድንገተኛ ሁኔታዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት በሚያስችል ደረጃ ላይ ናቸው።
“ምንም እንኳን የተፈቀደ ቢሆንም፤ ሁለት ራሳቸውን የቻሉ የኢሜል አድራሻዎች መጠቀም ነበረብኝ። አንዱ የግል፤ ሌላው ከሥራ፥ ከኃላፊነቴ ጋር ለተዛመዱ አገልግሎቶች የሚውል። ያን ያለማድረጌ ስህተት ነው። ይቅርታ እጠይቃለሁ። ኃላፊነት የምወስድበት ነው።” በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ተፎካካሪ ሂላሪ ክሊንተን።
ተጨማሪ ይጫኑ