“በሶሪያ በሚታየው ሁኔታ አንዳችንም አረጋጊ ስሜት ጨርሶ ሊያድርብን አይችልም። እጅግ አዋኪ ነው። የተኩስአቁሙን ፈተና ላይ የጣለውና እየከፋ በመጣው የሰሞኑ ቀውስ ሁላችንንም በእጅጉ አሳስቦናል። ይሄን ሁሉ በወረቀት ላይ ከሰፈሩ ቃላት በላይ እውን ለማድረግ፤ ዛሬ ያረቀቅናቸውን በየደረጃው የሚከናወኑ ዕቅዶች ዳርማድረስ የሚያስችሉ ግልጽና በቁርጠኝነት የተመሉ ተጨባጭ እርምጃዎችን ይጠይቃል።” የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይሚንስትር ጆን ኬሪ።
“የጅምላ ፍጅት የተፈጸመባቸውን ንጹሃንና በስብዕና ላይ የተቃጣ የጦር ወንጀል ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በሚደረጉ ጥረቶች ላይ ለሚሳለቅን የአገር መሪ ተገቢ ምላሽ ነው።” የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ ኤልዛቤጥ ትሩዶ።
“ለምሳሌ በኢትዮጵያ ባካሄዱት የፓርላማ አባላት ምርጫ አንድም እንኳ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ለሸንጎ አባልነት አልበቃም። በሌላ በኩል የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት የኃይል እርምጃ በመቶዎች የተቆጠሩ ዜጎች ተገደለዋል። በቻድ ለፕሬዝዳንቱ ድምጻቸውን ባለመሥጠታቸው ብቻ በርካታ የጦር ሠራዊቱ አዛዞች ዘብጥያ ወርደዋል። ይሁንና አሜሪካ ለዚህ ተገቢውን ምላሽ ስትሰጥ አላየሁም።” በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ከፍተኛ አመራር አባል ሴናተር Ben Cardin
የአፍሪካ ህብረት (Great Green Wall)በግርድፉም “ታላቁ አረንጓዴ ግድግዳ” በመባል በሚታወቀውና በረሃማነትን ለመዋጋት በታለመው ዕቅድ ዙሪያ የሚመክር ዓለም አቀፍ ጉባዔ በያዝነው ሳምንት የመጀመሪያ ጉባኤውን በሴኔጋል በማካሄድ ላይ ነው። እንደ ባለ ሞያዎች አስተያየት፥ ዕቅዱ ድህነትን ለመቅረፍና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዓይነተኛ መንገድ ተደርጎ ተወስዷል።
“ማቻር ወደ ጁባ በሚመለሱበት ሂደት ወቅት የታዩት እክሎች፤ በደም መፋሰሱ ሳቢያ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያጠላው፥ እርስ-በእርስ በከፍተኛ ጥርጣሬ የመተያየትና ያለመተማመን ግዙፍ ችግር ማሳያ መሆኑን ሁሉም በግልጽ ይረዳል።” ሰማንታ ፓወር በተባበሩት መንግስታት የዩናይትድ ስቴትሷ አምባሳደር።
“የጸሃይ ብርሃን እንዳናይ፤ ውሃ እንኳን እንድንለምን ተደርገናል። ልጆቻችንና ዘመዶቻችን እኛን ለማየት እንዳይችሉ ተደርገናል።” አቶ ደጀኔ ጣፋ ታሳሪ የኦሮሞ ፌድራሊስት አመራር አባል።
መሲንቆ፥ ሥነ ግጥም፥ የኢትዮጵያውያን የባሕልና የስፖርት ሳምንት፤ ታሪክና ሕይወት፤ የሳምንቱ የእሁድ ምሽት የመዝናኛ ምርጫችሁ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ።
“ጠዋት ቂሊንጦ ስንሄድ አራቱ ሰዎች የሉም። ያሉበትን የሚነግረን አላገኘንም።” ወ/ሮ ዓይናለም ደበሎ፤ ላለፉት አራት ወራት በማዕከላዊ እሥር ቤት የነበሩትና ካለፈው አርብ አንስቶ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተዛውረዋል፤ ከተባሉት የኦሮሞ ፌድራሊስት አመራር አባላት ቤተሰብ አባላት አንዷ ናቸው።
የሳምንቱ መገባደጂያ የእሁድ ምሽት የእረፍት ጊዜ የመዝናኛ ምርጫችሁ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ። የቴአትርና የሙዚቃ ወጎች:- ከአምስት ተዋናዮች፤ እንዲሁም በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ስለተለየው የሙዚቃ ሰው ህይወትና ሥራ፤ ከአንጋፋ ሙዚቀኞች ጋር፤
“እዚህ ላይ እጅግ በጣም አሳሳቢው ጉዳይ፤ አሁን ማድረግ ያለብንን ፈጥነን ካላደረግን፤ የፈራነው እውን የመሆኑን አይቀሬነት ማወቃችን ነው። ያንዣበበውን አደጋ ለመታደግ፥ የኢትዮጵያ መንግስት የሚችለውን ሁሉ ቢያደርግም፤ እጅግ የከፋና መጠነ ሠፊ በመሆኑ ለብቻቸው ሁኔታውን ለመቀልበስ አይቻላቸውም።” የዓለም አቀፉ የሕጻናት አድን ድርጅት Save the Children ዋና ሥራ አስፈጻሚ Helle Thorning-Schmidt
“ከባለ አድራሻው ውጭ ማንም የመልዕክቱን ይዘት ማወቅ ወይም ማየት አይችልም። የትኛውም የኢንተርኔት ቀበኛ ወይም ቀማኛ፤ አለያም ጨካኝ መንግስታት፤ ማንም ምንም ማድረግ ሆነ ምንም ማግኘት አይቻለውም። እኛ ራሳችን እንኳን ያለ ባለቤቱ ፈቃድ መልዕክቱን ማወቅ ወይም ማየት አንችልም።” ጃን ኮም የዋትስአፕ(WhatsApp) ዋና ሥራ አስፈጻሚ።
“በኦሮሚያ አድማ በታኝ ፖሊስና በፌድራል ሠራዊት ተደበደብን። የሃይል እርምጃውን ለመውሰድ ቀድሞውኑ ተዘጋጅተው ነበር።” የመንዲ ከተማ ነዋሪ። “መዝሙር በመዘመራቸው የተወሰደ እርምጃ የለም።” የመንዲ ከተማ ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሰንበታ።
“የጨው ክምር ሲናድ ሞኝ ይስቃል ብልጥ ያለቅሳል፤ እንደሚባለው አሁን ያለው ሁኔታ እኔ ያሳስበኛል።” ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ። “አደገኛ ሁኔታ ነው። ... ምን ዓይነት ለውጥ? ... ዕድልም አደጋም የያዘ አጋጣሚ የያዘ ነው፤ የሚመስለኝ።” አቶ ፈቃደ ሸዋቀና።
በዘንድሮው የኒው ዮርኩ የሥነ ጥበብ፥ የደቡብ አፍሪቃ፥ የኬንያ፥ የናይጄሪያና የአይቮሪኮስት ታዋቂና ወጣት ባለ ሞያዎች፥ የተለያዩ የሥነ ጥበብ ማሳያዎች ባለቤቶችና እንዲሁም የጥበብ ዘርፉ አዋቂዎች ተገኝተዋል።
“ቁጥራቸው 10 ሺህ የሚጠጋ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆነ ሕጻናት ጨርሶ በተንኮታኮተው የአገሪቱ የጤና አገልግሎት ሳቢያ ሊታከሙ በሚችሉ በሽታዎች እንዳያልቁ ከፍተኛ ሥጋት አለኝ።” በየመን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሕጻናት መርጃ ፕሮግራም ዩኒሴፍ (UNICEF)ተጠሪ ጁልየን ሃርኒስ
“‘ኮሌስትሮል’ ሲባል ሁሌ እንደ መጥፎ ነገር የማየት ዝንባሌ አለ። በመሠረቱ ያለ ‘ኮሌስትሮል’ ሕይወት የለም። ኮሌስትሮል ጠቃሚም ነው፤ መጠኑ ሲበዛ ደግሞ ለአደጋ የሚዳርግ ይሆናል።” የልብና የውስጥ ደዌ ከፍተኛ አማካሪ ሃኪም ፕሮፌሰር ከበደ ኦሊ።
“የሶሪያ መንግስት ኃይሎች በፓልሚራ አይሲስ’ን ድል ለመንሳትና ብሎም ቡድኑ ያወደመውን መልሶ ለመገንባት የያዙት እቅድ በሰብዓዊነት ላይና በባሕል እሴቶች ላይ የተቃጣን ለመከላከል መቻሉ አበረታች ነው። የተናገሩትን ተግባራዊ ማድረግ ይሳካላቸዋል ብዬም ተሥፋ አደርጋለሁ።” የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ባን ኪሙን
“መሠረት ያለው የማንነት ስሜት አይሰማቸውም። ምክኒያቱም ከሞሮኮያውያን ወይም ቱኒዝያዊያን፤ ሱዳናውያን አለያምም ሌላ ወገን ከሆኑ ወላጆቻቸው የሚወለዱ ሁለተኛና ሦሥተኛ ትውልድ ሊሆኑ ስለሚችሉ፤ የወላጆቻቸውን አገር ማንነት አይላበሱም፤ ወይም ራሳቸውን የዚያ የተወለዱና ያደጉበት ተቀባይ አገር አካል አድርገው አይቆጥሩም።"ቶም ሳንደርሰን የስትራተጂና የዓለም አቀፍ ጥናቶች ማዕከል ዲሬክተር
ይህ ድንቅ ታላቅ ምሽት ነው። ዶናልድ ትራምፕ። “ለሌሎች ሃሳብ ደንታ ቢስ በመሆንና በድንፋታ ፋንታ አንዳችን ለሌላችን በአክብሮት፥ በትህትናና በፍቅር ብንቀርብ፤ አንዳችን ሌላችንን ከመጣል አንዳችን ሌላችንን ከፍ ብናደርግና ብናነሳ፤ ተባብረን ከዳር የማደርሰው ነገር አይኖርም።” ሴናተር ሂላሪ ክሊንተን።
"የንግግር ነጻነትን በማረጋግጥና ዲሞክራሲያዊ እርምጃዎችን በማጎልበት የኢትዮጵያ መንግስት ቀደም ሲል የወሰዳቸውን አዎንታዊ እርምጃዎች እንዲያጠናክ እያሳሰብን፤ በነጻ ድምጾች ላይ የሚፈጸመው አፈና ይህን መሰሉን አዎንታዊ እርምጃ ማደናቀፍ ብቻ ሳይሆን፤ የልማትና የምጣኔ ሃብት እድገትንም የሚገታ መሆኑን መጠቆም እንፈልጋለን።” የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር።
ተጨማሪ ይጫኑ