ዋሽንግተን ዲሲ —
የትምባሆ ምርቶችን አስተሻሸግ መለወጥ ሰዎች ለዚህ ገዳይ ሸቀጥ ያላቸውን ፍላጎት እንዲቀንስእያገዘ ነው፤ ሲል የዓለም ጤና ድርጅት WHO አስታወቀ።
የዓለሙ ጤና ድርጅት የዛሬውን ዓመታዊ ከትምባሆ የጸዳ ቀን ለማስታወስ አገሮች በአማላይ የትምባሆምርት ማሸጊያዎች ምትክ ተራ ፓኮዎችን በመጠቀም ማራኪነቱ እንዲቀንስ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
የተለያዩ የትምባሆ ምርቶች ማሸጊዎችን አስመልክቶ የዓለም ጤና ድርጅት ያቀረበው አዲስ ሃሳብ፤ካሁን ቀደም በሲጋራ ፓኮዎች የሚታተሙትን ለየት ባለ አለባበሳቸው የሚታወቁ ፈረስ ጋላቢዎችመስክ ላይ ሲጋራ ይዘው የሚታዩባቸውን ምስሎች በእጅጉ የተለየ ገጽታ የሚያንጸባርቁ ናቸው።
ለናሙና የወጡት ፓኮዎች፤ በጥቁር መደብ ላይ ሲጋራ ገዳይ መሆኑን የሚያመለክቱ ጽሁፎች በጉልህየሰፈሩባቸውና በካንሰር ሳቢያ ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች ምስል የሚታይባቸው ናቸው።