በአምቦ እስር ቤት ተቃጥሏል፤አንድ የዘጠኝ ዓመት አዳጊ ተገድሏል
ኮመዲያን ክበበው ገዳ በማኅበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካ ነክ ነቃሽ ቀልዶቹ ይታወቃል፡፡ ቀልድ ከማዝናናት ባለፈ በማኅበረሰቡ ውስጥ ስለሚኖረው ቦታ ከጽዮን ግርማ ጋር ቆይታ አድርግጓል፡፡
ዶ/ር አብርሃም ዓለሙ የሥነ ጹሑፍና ፎክሎር ተመራማሪ ናቸው፡፡ ከሥነ ሕዝብ ጥበብ ውስጥ አንዱ የኾነው ቀልድ በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ስለሚኖረው ማኅበራዊ፣ፖለቲካዊና ባሕላዊ ፋይዳ ይነግሩናል፡፡በዚህ ጉዳይ ላይ ከጽዮን ግርማ ጋር ውይይት አድርገዋል።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና በኢቢኤስ ቴሌቭዠን ጣቢያዎች ላይ ከዘጠኝ በላይ ተከታታይ የቴሌቭዠን ፕሮግራሞች በመተላለፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ ድራማዎቹ በከፍተኛ ሁኔታ አብዛኛውን የኅብረተሰብ ክፍል እይታ የተቆጣጠሩ ናቸው፡፡ በእነዚህ በብዛት እየቀርቡ ባሉ የቴሌቭዥን ድራማዎች የታሪክ ጭብጥና የገጸ ባሕሪያት አሳሳል ለትውልድ የሚተላለፈው መልዕክት ምንድነው? በሚል መጠይቅ የሚንደረደረው የዛሬው የትንታኔ ፕሮግራም ባለሞያዎችን አካቶ ይዟል፡፡አዘጋጇ ጽዮን ግርማ ነች፡፡
ከ54 አፍሪካ አገራት ለሚሳፉበት የዘንድሮው የአፍሪካውያን የሙዚቃ (Kora) ውድድር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቲዲ አፍሮ) በዝነኛ ድምጻዊ (Legendary Award) ዘርፍ እንዲሁም በሴት ምርጥ የባህል ሙዚቃ (Best Traditional Music Artist) አርቲስት አቢ ላቀው እጩ ኾነዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ከአንዷ እጩ አቢ ላቀው እና ቀደም ሲል ይህን ሽልማት ካገነችው ከጸደንያ ገ/ማርቆስ ጋራ ቆይታ አድርገናል፡፡
ስደት ብዙ መልክ አለው፡፡ ሰዎች በሥራ እና በትምሕርት ምክንያት ከተወለዱበትና ካደጉበት ሀገር ወደ ሌላ ሀገር በመዛወር በፍላጎታቸው አዲስ ኑሮን ይጀምራሉ፡፡ የተማሩ ሰዎች በተማሩበት ትምሕርት ልክ የተመቻቸ ነገር ማግኘት ሲያቅታቸውም ይሰደዳሉ፡፡ ይህንንም ምሑራዊ ስደት እንለዋለን፡፡ እንዲሁም ሰዎች በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ምክንያት አገር ጥለው ይሰደዳሉ፡፡ ከዚህ ውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ለምን ይሰደዳሉ? ይህ ዘገባ የሚለው ይኖረዋል።
ግዙፍ የኾኑ የመጠጥ አምራች ኩባንያዎች ፊታቸውን ወደ አፍሪካና ኢትዮጵያ ገበያ አዙረዋል፡፡ አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው በኢትዮጵያ የመጠጥ ማስታወቂያ ገደብ እየተደረገበት አይደለም ይላሉ፡፡ ብስራት ተሾመ፣ቁምላቸው ዳኜ፣አሌክስ አብርሃም እና አቶ ውብሸት ወርቃለማሁ፡፡ በጉዳዩ ላይ በየሞያቸው አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
"የአንደኛ ደረጃ ትምሕርት ሽፋንና ጥራት በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች ምን ይመስላል?" በሚል መነሻ ሐሳብ ይህ ዘገባ በአማራ፣በአፋር እና በኦሮሚያ የአንደኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት መምሕራንን ስለ ትምሕርት ጥራቱ ይጠይቃል፡፡ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ ያጠናው ጥናት በዘገባው ተካቷል፡፡
ብሌን ሣሕሉ ትባላለች፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕግ ትምሕርት ክፍል መምህር ናት፡፡እሁድ ለሚከብረው የፍቅርኞች ቀን አበባ በመሸጥ በሚገኘው ገንዘብ ለሴት ተማሪዎች መሰረታዊ ችግር መፍቻ ለማዋል በ“yellow movement“ ስር ስለሚደረግው እንቅስቃሴ በሙዚቃ ቃና ፕሮግራም ታጫውተናለች፡፡ ምርጥ፣ምርጥ የፍቅረኞች ቀን ሙዚቃ ምርጫም ይኖረናል፡፡አዘጋጅና አቅራቢዋ ጽዮን ግርማ ነች፡፡
ደራሲ እና ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም “ባለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት የሚጻፉ አንዳንድ መጽሐፎች በሕብረተሰብ መካከል፣ በተለይ በኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል ያለውን ትስስር የሚያላሉ፣አልፎ አልፎ ደግሞ እንዲበጠስ የሚያግዙ አስተያየቶችን እና ሐሳቦችን አያለሁ፡፡”ይላል፡፡
በመሰላ አባድር ከተማ ደግሞ የአንድ ሌላ ተማሪ አስክሬን ጉድጓድ ውስጥ ወድቆ ተገኘ፡፡
“በማንኛውም ትግል ውስጥ ተማሪን ተማሪ ገደለው ሲባል ሰምቼ አላውቅም” ሲሉ ሰሞኑን በሮቤው መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተገደለው ተማሪ ሣሙዔል አባት አቶ ከተማ በቀለ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ልማት ማስተር ፕላን ዕቅድ ላይ የተነሣው ተቃውሞ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በኋላ የዛሬ ወር ተኩል አካባቢ አገርሽቶ እንደገና የመረጋጋት አዝማሚያ ያሳየ መስሎ ነበር፡፡ይሁን እንጂ ሰሞኑን ደግሞ እንደገና የመነሣሣት አዝማሚያዎች ተስተውለዋል፡፡
የገንጂ ከተማ ከንቲባ "ኦነግን የሚያወድስ ዘፈን ስለዘፈኑ ነው"ብለዋል
የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኣቶ ዮናታን ተስፋዬ በዛሬው ዕለት መታሠራቸውን የፓርቲው ሊቀመንበር ኣቶ ይልቃል ጌትነት ኣስታወቁ። ኣቶ ይልቃል ጌትነት ይህንና ወቅታቂ ጉዳዮችን በተመለከተም በነገው ዕለት መግለጫ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።ይህ ጉዳይ በተመለከተ ከቶ ይልቃል ጌትነት ጋር አጠር ያለ ቆይታ ያደረገችው ጽዮን ግርማ ነች።
ኢትዮጵያውያን ማኅበራዊ ሚዲያን እንዴት ይጠቀሙበታል? እንዲሁም ታዋቂ ኢትዮጵውያን እና የማያውቁት የፌስቡክ ገጾቻቸው በሚል ርእስ ጽዮን ግርማ ውይይት አዘጋጅታለች፡፡ እንዳልካቸው ኀይለ ሚካኤል፣ የትነበርክ ታደለ፣በእውቀቱ ስዩም ፣ ሳያት ደምሴ፣ አምለሰት ሙጬ እና ኤልሻዳይ ነጋሽ በዚህ ዘገባ ተካተዋል፡፡
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራር አባላትም ኾነ የሰማያዊው ፓርቲ ወጣቶች የታሠሩት፤በወንጀል ተጠርጥረው እንጂ በፖለቲካ ድርጅት ውስጥ ስለተሳተፉም ኾነ ስለጻፉ አይደለም ሲሉ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮቸ ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ፤ የፓርቲው ልሳን የኾነው የ"ነገረ ኢትዮጵያ" ጋዜጣ አዘጋጅና ሌሎች ሦስት ንቁ ተሳታፊ አባላቶቹ እንደታሠሩበት አስታወቀ፡፡
በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ታስረው ፣ጉዳያቸው ለአንድ ዓመት ከአምስት ወር በላይ ሲታይ ቆይቶ ከአንዱ በስተቀር "መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ" ተብሎ ከሁለት ወራት በፊት ተወስኖላቸው የነበሩት አምስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ይግባኝ ተጠየቀባቸው፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ