ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላንና ከኦሮሚያ ከተሞች ዐዋጅ ጋር ተያይዞ ኦሮሚያ ውስጥ በተነሣው ተቃውሞና ግጭት የበርካታ ሰው ሕይወት መጥፋቱና ከ3,500 ሰው በላይ መታሠሩን ኦ.ፌ.ኮ አስታወቀ፡፡ ከአምስት ወራት በፊት የተፈቱት የቀድሞ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ገርባም መታሠራቸው ታውቋል፡፡
"ይህን መንግሥት ከሌሎቸ መንግሥታት ለየት የሚያደርገው፤ ‘እኔ ይህን ያሕል ሞተብኝ’ ብሎ ከተሰላፊዎቹ እኩል ጭቅጭቅ ውስጥ ይገባል" ከሕግ ባለሞያ አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ጋር የተደረገ ቃል ምልልስ (ክፍል ሁለት)
አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ይባላሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምሕርት ክፍል የቀድሞ መምሕር ነበሩ። በአውስትራሊያ ሜልበርን ከተማ፤ በሜልበርን የሕግ ትምሕርት ቤት “በሕገ-መንግሥት ሕግ” የዶክሬት ዲግሪያቸውን አጠናቀዋል።የሕግ አስተማሪና ተመራማሪም ናቸው። በአዲስ አበባና ዙሪያዋ የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ መደረግን ተከትሎ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ በድጋሚ ስላገርሸው ተቃውሞ እና የመንግሥት ምላሽ፤ ከሕግ አኳያ ትንታኔ ሰጥተዋል፡፡
ላለፉት ሦስት ሳምንታት የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ተማሪዎች የአዲስ አበባ እና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ሲቃወሙ ሰንብተዋል። የተቃውሞውን ጅምር የሚያትተውን የማርታ ፋን ደር ቮልፍ የአዲስ አበባ ዘገባ ጨምራ፤ ጽዮን ግርማ የዛሬዉን የተቃውሞ ሰልፍ ውሎ የተመለከት ርእሶችን ይዛለች፡፡
የአዲስ አበባ እና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ያገረሸው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ፡፡የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ለሰጡት አስተያየትም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞኖች የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ የመደረግን እቅድ ተከትሎ፤ በአብዛኛው የኦሮሚያ ክልል ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላ ያገረሸው ተቃውሞ የዛሬው ውሎ ምን መልክ እንደነበረው ከኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ ጋር የተካሄደ ቃለ ምልልስና በርዕሱ ዙሪያ የተጠናከረ ዘገባ።
“ድርቅና ረሃብ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ትናንት በአውሮፓ ፓርላማ የተካሄደው ውይይትና ክርክር በጣም ጥሩ እንደነበር የገለጹት የፓርላማው አባል ሚስ አና ጎሜሽ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋም በስብሰባው ላይ የተገኙት በአውሮፓ ፓርላማ አባላት ተጋብዘው መኾኑንም አረጋግጠዋል፡፡
የአርበኞት ግንቦት ሰባት መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ብረስልስ ቤልጄም በሚገኘዉ የአዉሮፓ ፓርላማ በኢትዮጽያ ስለተከሰተዉ ድርቅና ረሃብ ማብራሪያ መስጠታቸዉ ታዉቋል።
ዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የሰብዓዊ መብቶች ክንፍ እና የታም ላንቶስ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ኮሚሽን የዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ደኅንነት ተሟጋቹ ቡድን ሲፒጄ የዘንድሮ ተሸላሚዎችን ምስክርነት አደመጠ። ከተሸላሚዎቹ አንዱ የዞን ዘጠኝ ብሎገሮች ቡድን አባሏ ሶሊያና ሽመልስ ተናግራለች።
ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከገጠሟት ሁሉ በከፋ ሁኔታ በድርቅ እንደተመታች እየተነገረ ነው። በተለይ በአፋር፣ በሶማሌ፣ በትግራይ፣ በምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ እንዲሁም በአማራ ክልል ከፍተኛ ርብርብ ካልተደረገ ሁኔታው ተባብሶ ወደ ከፍተኛ ረሃብ ሊቀየር ይችላል የሚል ስጋት አለ። የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ጣቢያ የአፋር፣የሁምራ እና የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ነዋሪዎችን በማነጋገር ተከታዩን ዘገባ አጠናክሯል፡፡