ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት (ICC) አምስ ት የተለያዩ የጦር ወንጀሎችና ሰብአዊ ፍጡር ላይ ወንጀል በመፈጸም ቀድሞ የኮንጎ ምክትል ፕሬዚደንት ዣን ፔሬ ቢምባ ላይ ዛሬ ብይን አስተላፏል። ዘጋቢያችን ሪቻርድ ግሪን ያጠናቀረዉን ጽዮን ግርማ ታቀርባለች።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የሁለት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ትናንት እሁድ ኩባ ገብተዋል። ለግማሽ ምዕተ ዓመት የዘለቀውን የሁለቱን ሀገራት የባላንጣ ግንኙነት ምዕራፍ ይዘጋል የተባለውን ውይይትም በዛሬው ዕለት ከኩባ መሪዎች ጋር በማድረግ ላይ ናቸው።
በኦሮሚያ የተነሳው ተቃውሞ አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች መቀጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎቸ ይናገራሉ፡፡ በአርሲና በምዕራብ ወለጋ ዞን ተማሪዎችና ነዋሪዎች እየታሠሩና ድብደባ እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ባልደረቦች ጃለኔ ገመዳና ነሞ ዳንዲ ያጠናቀሩትን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋለች፡፡
እሁድ ዕለት በኮንሶ ደበና በተባለች መንደር ሁለት አርሶ አደሮች በታጣቂዎች መገደላቸውን የሟች ሞሌ አዛዥ አባትና የሟች ፋንታዬ ጊዮርጊስ አጎት ተናግረዋል።ወደ 55 ሺሕ የሚኾኑ ነዋሪዎች ተፈራርመው ኮንሶ ከወረዳ ወደ ዞን ከፍ እንዲል ጥያቄ በማቅረባቸው ምክንያት፤ ጥያቄውን ለመንግሥስት ካቀረቡት የኮሚቴ አባላት መካከል አንዱ መታሠራቸውን ሌሎች ደግሞ በስጋት ተሸሽገው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ጽዮን ግርማ የሟች ቤተሰቦችንና የኮሚቴውን አባላት አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች፡፡
አራት ወራትን ያስቆጠረው የኦሮሚያ ተቃውሞ አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች እንደቀጠለ መኾኑን ዘገባዎች እየጠቆሙ ነው። ከትናንት ወድያ ማምሻውን በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ በነበረ ተቃዎሞ ተማሪዎች መታሠራቸው ተነሯል። የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት የታሠረ ተማሪ የለም ብለዋል።
“ከዚህም የከፋ ነገር በየእሥር ቤቱ ይፈጸማል” የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ መርማሪና የሕግ ባለሞያ አቶ ያሬድ ኃይለማሪያም በደቡብ ኦሞ ስለሚፈጸሙ የመብት ጥሰት ይናገራሉ፡፡
ካለፈው እሁድ ጀምሮ በማኅበራዊ ሚድያ ሲሰራጩ የቆዩት፤በደቡብ ክልል በኦሞ ዞን የሚገኙ አራት ኢትዮጵያዊያን እርስ በርስ እግር ለእግርና አንገት ለአንገት በቃጫ ገመድ ታሥረውና እንግልት ደርሶባቸው የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን በተመለከተ የክልሉ ፖሊስ ኮሚቴ አቋቁሞ እያጣራ እንደኾነ ሲገልፅ አንድ የሱርማ ነዋሪ ፤ ያስቸገረን ወንጀለኛን በገመድ አስሮ መያዝ በሱርማ የተለመደ እንደኾነ ይናገራሉ፡፡ ጽዮን ግርማ ተከታዩን ዘግባለች፡፡
ኮንሶ ወረዳ መኾኑ ቀርቶ ዞን እንዲኾን ጥያቄ በማቅረባቸው ምክንያት ባሕላዊ አባታቸውን (የኮንሶ ንጉስ) ጨምሮ ወደ 200 የሚጠጉ ሰዎች እንደታሠሩባቸው ከኮሚቴው አባላት አንዱ አቶ ገመቹ ገንፌ ገለጹ፡፡ጽዮን ግርማ አቶ ገመቹ ገንፌን አነጋግራቸዋልች፡፡
በኦሮሚያ ከተቀሰቀሰው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ እስካሁን በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ከተማ ውጥረት መንገሱን፣ የመማር ማስተማር ሂደቱ መስተጓጎሉንና ተማሪዎች ከሚማሩበት ትምሕርት ቤት እየታሠሩ እንደሚወሰዱ አንድ የነጆ ከተማ ነዋሪ ተናገሩ፡፡ ፖሊስ ከተማዋ ሠላም መኾኗን ይናገራል፡፡ ጃለኔ ገመዳ ያጠናቀረችውን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋልች፡፡
“ከሃምሳ በላይ ተማሪዎች ታሥረዋል። የዐሥራ ስምንቱ ዝርዝር አለኝ፡፡”የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ
የ20 ዓመት ወጣትና የዐሥረኛ ክፍል ተማሪ ሞቱማ ፈዬራ በታጣቂዎች መገደሉን ለቤተሰቡ ቅርበት እንዳላቸው የገለጹ ምንጮች ሲናገሩ፤የወረዳው መስተዳድር በበኩላቸው የሟቹን አስክሬን መመለከታቸን ተናገረው ‘በማን ተገደለ?’ ስለሚለው ግን የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገለፀዋል፡፡
ሕዳር ሁለት ቀን የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች ቀጥሏል። በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች፤ ዞኖችና ወረዳዎች ተቃውሞው ስለመቀጠሉ የአካባቢው ነዋሪዎች አስተያየት ሲሰጡ ይደመጣል። ዛሬም ሰዎች ይሞታሉ፣ይታሠራሉ እንዲሁም ይደበደባሉ የሚሉ አስተያየቶች ይነገራሉ። የዘገባዎቹን ዝርዝር ጽዮን ግርማ ይዛለች።
የኢትዮጵያ ታሪክና ሥን ጥበብ መምሕሩ አቶ አበባው አያሌው ምላሽ አላቸው
በሰሜን አሜሪካ በሜሪላንድ ክፍለ ግዛት በርካታ ኢትዮጵያዊያን የሚኖሩበት ሞንትጎመሪ አውራጃ (Montgomery County) መጋቢት ወር የዓድዋ ድል በዓል ኾኖ እንዲታሰብ ወስኗል።
“ሁላችንም የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ነን።ሕጉ ተግባራዊ የሚደረግ ከሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ክሥራ ውጪ እንሆናለን።’’ በዛሬው ዕለት የታክሲ ማቆም አድማ ካደረጉት የታክሲ አሽከርካሪዎች በከፊል፡፡
“የሕሊና እሥረኞች ይፈቱ” በሚል ርእስ ትናንት ሐሙስ እና ከትናንት በስቲያ የበይነ-መረብ ዘመቻ በፌስቡክ እና በትዊተር ተካሂዷል፡፡
አራተኛ ወሩን የያዘው በኦሮሚያ የተለያዩ የዞን ከተሞች እየተካሄደ ያለው ተቃውሞ የቀጠለ ሲኾን በያቤሎ፣ በአሬሮ፣ ሂድ ሎላ፣ በጉጂ ዞን ሻኪሶ ከተሞች የተደረጉ ሰልፎች አብዛኞቹ ሕገወጥ ናቸው። በአንዳንዶቹ ቦታዎች ደግሞ ከሕዝቡ ጋር እየተነጋገርን ነው ሲል የወረዳ እና የዞኑ ባለሥልጣናት ለአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡፡
ኢሕአዴግ በአንድ ወገን ሕገ መንግሥቱን እየጠቀሰ በሌላ ወገን የሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አፈራርሶ "አትግደል" የሚለውን ተራውን ሕግ እንኳን በየቀኑ እንደሚጥስ የተናገሩት ዶ/ር ጸጋዬ ረጋሣ ናቸው - በክፍል ሁለት የቃለ-ምምልሱ ክፍል። ጽዮን ግርማ አነጋግራቸዋለች።
ዶ/ር ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ይባላሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምሕርት ክፍል የቀድሞ መምሕር ነበሩ። በተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት የሰብዓዊ መብትና መልካም አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ ኾነው ሠርተዋል።በማኅበራዊ ሚዲያ በተለይም ፌስቡክ ላይ በኦሮሚያ የተነሳውን ተቃውሞ በትኩረት እየተከታተሉ አስተያየታቸውን በማስፈር ይታወቃሉ፡፡ ጽዮን ግርማ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ አነጋግራቸዋለች፡፡
በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የተቀለዱ ቀልዶችን አሰባስበዋል፤በቃለ ምልልሱም ተካቷል
ተጨማሪ ይጫኑ