ሚስትና ልጁን ያጣ፣እናትና ወንድሞቹን ውሃ የበላበት፣እህቱን እና 28 ጓደኞቹን ያጣ ናቸው። ስላሳለፉት ጉዞ አስቸጋሪነትና ለመሄድ ስለተዘጋጁ ስደተኖች የሚነግረን ወጣትም ከግብጽ አነጋግረናል።
ከግብፅ ወደ ጣልያን በመጓዝ ላይ እያለ በሰጠመው ጀልባ ላይ በአንድ ጊዜ ሦስት ቤተሰቦቹን አጥቷል። ሙሐዝ ሞሐመድ ባለቤቱንና የሁለት ወር ልጁን አጥቶ እሱ ተርፏል።
በአምቦ ዩኒቨርስቲ አዋሮ ግቢ ካለፈው አርብ ጀምሮ ውሃ መቋረጡን፣ መብራት ከዕረቡ ጀምሮ መጥፋቱን እንዲሁም በምስራቅ ወለጋ መነሲቡ ወረዳ ከሠላሳ በላይ ሰዎች መታሠራቸው በዚህ ዘገባ ተካቷል።
የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ቀደም ሲል ያጸደቀው የከተሞች ዐዋጅ ሦስት አንቀጾች መሰረዙ የሚያመጣው አዲስ ነገር እንደማይኖር፣ ሕዝቡ ስላልተቀበለው ሙሉ በሙሉ መሰረዝ አለበት፤ "ጠቃሚ ኾኖ ቢገኝ እንዃን ሕዝብ ስላልተወያየበት ተቀባይነተ ሊኖረው አይገባም።" ሲሉ የኦሮሞ ፌዴራሊስ ኮንግረስ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ማምሻውን ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል።
የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) 26ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በምዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ ነዋሪዎችና ተማሪዎች ተቃውሞ ገጠመው፡፡
የቢሾፍቱ መሰናዶ ትምሕርት ቤት ተማሪዎች ትናንትና እና ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ሙከራ ማድረጋቸውንና በፖሊስ መደብደባቸውን ተማሪዎችና ነዋሪዎች ገለፁ፡፡
ብዙ ጊዜ ከድርቅ በኋላ የጎርፍ አደጋ ስለሚከሰት፤ አሁንም የጎርፍ አደጋ ስጋት እንዳለና በጅግጅጋና በአፋር በደረሰው የጎርፍ አደጋ ለተጎዱት እርዳታ እየተሰጠ መኾኑን የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። አስክሬን ፍለጋው ቀጥሏል ተብሏል።
ኢትዮ ቴሌኮም የነፃ የስልክ ጹሑፍ መልዕክትን ጨመሮ፤ ለቫይበር፣ ዋትስ አፕ፣ ዊቻትና ለመሳሰሉት ነጻ የኢንተርኔት አፕሊኬሽኖች ተጨማሪ ክፍያ የሚያስክፈል፤ አስፈላጊ ኾኖ ከተገኘ ደግሞ እነዚህን አፕሊኬሽኖች የሚዘጋ (ወይም ብሎክ የሚያደርግ) አዲስ ቴክኖሎጂ ሀገር ውስጥ ማስገባቱን አስታውቋል፡፡
ነዋሪዎች “የሟቾች ቁጥር ከ40 በላይ ይኾናል፤ ከአንድ ቤት ስምንት ሰው ሕይወት ጠፍቷል” ይላሉ።
በታንዛኒያ፣በኬንያ እና በኢትዮጵያ የሚገኙ ወጣቶች የኢንተርኔትና ስልክ አጠቃቀማቸው ምን ይመስላል? በየሚኖሩበት አካባቢ የሚያገኙት አገልግሎትስ? በሚሉ ጥያቄዎች ላይ እንዲወያዩ ሦስት እንግዶችን ጋብዘናል ጽዮን ግርማ ናት ያወያየቻቸው፡፡ እንግዶቹ ራሳቸውን በማስተዋወቅ ይጀምራሉ፡፡
በቪዠን ኢትዮጵያና በኢሳት መጋቢት 17 የተዘጋጀ የሦስት ፓርቲዎች ውይይት ኢትዮጵያ ውስጥ እየጨመሩ የሚሄዱትን ግጭቶች ለመፍታትና የብሔራዊ አንድነት መንፈስን ለማጠናከር በሚያስችሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በቪዥን ኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያ ሳተላይት ሬዲዮና ቴሌቭዥን (ኢሳት)አዘጋጅነት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ቅዳሜ መጋቢት 17 እና እሁድ መጋቢት 18 የሁለት ቀን ውይይት ተካሂዶ ነበር።
ከተጀመረ አምስተኛ ወሩን ሊደፍን ጥቂት ቀናት የቀረው የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ተቃውሞ በአንዳንድ ከተሞች በሚገኙ ትምሕርት ቤቶች ከትናንት በስቲያ፣ ትናንትና ዛሬ በቢሾፍቱ ከተማና ደባዩ በተባለ አንደኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት እንዲሁም በበደሌ ከተማና ለሊሳ ሃሮ ቶሬ በተባለች የገጠር ቀበሌ ተማሪዎች እንደታሠሩና በአስለቃሽ ጭስ ምክንያት፤ ሆስፒታል እንደገቡ ነዋሪዎችና ተማሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።
ከአምስት ወራት በፊት ከእሥር የተለቀቁት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች፤ ከእስር ከተለቀቁም በኋላ አገር ውስጥ በነጻነት መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ እንዲሁም ለሽልማት፣ለትምሕርትና ለሥልጠና ላገኟቸው ዕድሎች ከአገር መውጣት እንደተከለከሉ ገለጹ፡፡
ቪዥን ኢትዮጵያና ኢሳት ዋሽንግተን ውስጥ ባዘጋጁት የሁለት ቀን ጉባኤ እየጨመሩ የሚሄዱትን ግጭቶች ለመፍታትና ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር "ሽግግር፣ ዴሞክራሲና ብሔራዊ አንድነት” በሚለው የውይይት ርእስ ሥር፤ የሕዝባዊ እንቅስቃሴዎችና የማኅበራት አደረጃጀቶች፤ ግጭቶችን በመፍታትና ዴሞክራሲን በማስፈን ረገድ ሊኖራቸው ስለሚገባው ሚናና ከግጭቶች መርገብ በኋላ በሚኖረው የሽግግር ወቅት ምን ይጠበቅባቸዋል?በሚል ርእስ አራት ተወያዮች ጹሑፍ አቅርበው ውይይት ተካሂዷል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ እየጨመሩ የሚሄዱትን ግጭቶች ለመፍታትና የብሔራዊ አንድነት መንፈስን ለማጠናከር በሚያስችሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በቪዥን ኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያ ሳተላይት ሬዲዮና ቴሌቭዥን(ኢሳት)አዘጋጅነት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ የሁለት ቀን ውይይት ተካሂዶ ነበር። ጽዮን ግርማ ስለውይይቱና ውይይቱን በተመለከተ የቪዥን ኢትዮጵያን ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻውን አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች፡፡
የኖርዌይ ከለላ ጠያቂዎች ድርጅት ከፍተኛ አማካሪና የሕግ ባለሞያ በፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው ስደተኞች ስጋታቸው ተገቢ ነው ይላሉ።
በኦሮሚያ ከተሞች ከተነሳው ተቃውሞ ጋራ በተያያዘ ተጠርጥረው በእሥር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች እሥረኞች የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውን ጥቆማ እንደደረሳት ልጃቸው ቦንቱ በቀለ ለሜሪካ ድምፅ ገልፃለች፡፡
በኦሮሚያ ክልል ከሚካሄደው ሕዝባዊ ተቃውሞ ጋራ በተያያዘ ያጋጠመውን ወቅታዊ ችግር ለመፍታት ኃላፊነታቸውን አልተወጡም በሚል ሦስት መቶ ሰዎችን ከሃላፊነታቸዉ ማንሳት ለተነሳው ጥያቄ መፈትሔ እንደማያመጣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሰብሳቢ አቶ ሙላቱ ገመቹ ተናገሩ፡፡
በምዕራብ ወለጋ ዞን መንዲ ከተማ መምሕራንና ተማሪዎች ታሥረው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን እንዲሁም ማክሰኞ መጋቢት 13 ቀን በከተማው ውስጥ የሚገኝ የገበያ ቦታ መቃጠሉን በዚህ ቃጠሎም የመንግሥት እጅ አለበት የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ለሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
የአረና ትግራይ ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዓንዶም ገብረሥላሴ እና የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ዘነበ ሲሳይ በዛሬው ዕለት ጠዋት በፓርቲው ፅ/ቤት የሚገኙ የቆዩ ሰነዶችና ቆሻሻ በማቃጠል ላይ እያሉ በልዩ ኃይል ፖሊሶች ታግተው በመቀሌ ከተማ ውስጥ ለአምስት ስዓታት ታሥረው መቆየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ