እያወዛገበ በሚገኘው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ጉዳይ በትምሕርት ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይና ከፍትኛ ባለሞያ አቶ አህሕምድሲራጅ ሚስባሕን አነጋግረናል። ጽዮን ግርማ ነች ያነጋገረቻቸው።(ክፍል አንድ)
የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ሾልኮ በመውጣቱና የሁለት ፈተና ጥያቄዎች ከእነ መልሳቸው በማኅበራዊ ሚዲያ በመሰራጨቱ ምክንያት፤ የትምህርት ሚኒስቴር ሊሰጥ የነበርውን ፈተናው ማዛወሩ ይታወሳል።በውጭ ሀገር የሚገኙ የኦሮሞ ተቃውሞ አስተባባሪዎች እና የድምጻችን ይሰማ የድጋፍ ግብረሃይል አባላት ይህን ውሳኔ ተቃውመውታል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቀድሞው የፍልስፍና መምሕሩ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በበኩላቸው የብሔራዊ ፈተና መጥፋት ስለሥርዓቱ የሚናገረው አለ ይላሉ።
ከረጅም ዓመታት በፊት በፖለቲካ ምክንያት በሶማሊያ መኖር እንዳልቻሉ በመግለጽ በኖርዌይ ያቀረቡት የጥገኝነት ጥያቄ ተቀባይንት አግኝቶ ፤ የመኖሪያ ፈቃድ እና ዜግነንት ተሰጥቷቸው የነበሩ ወደ አንድ መቶ የሚጠጉ ሶማሌያውያን የኖርዌይ ዜግነታቸውን ተነጠቁ። ለዚህ ሁሉ የዳረጋቸው ደግሞ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ስለራሳቸው የሚያወጡት መረጃ ጥገኝነት ካቀረቡበት ታሪካቸው ጋር ስለማይመሳሰል ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥት በፀር ሽብር ሕጉን በሀገር ውስጥ ፖለቲካው ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ለማድረግ እየተጠቀመበት ነው በሚል መከሰስ ከጀመር አራት ዓመታት ተቆጥሯል። አሁን ደግሞ የኢንተርኔት አምደኞች እና ፖለቲከኞች ሐሳብን የመግለጽ ነፃነትን የበለጠ ስጋት ላይ የሚጥል አዲስ የኮምፒዩተር ረቂቅ ወንጀል ዐዋጅ ወጥቷል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያና ኤርትራዊያን ይሠሩበታል በሚባለው በካናዳ አልበርታ ግዛት ፎርት ማክመሪ ከተማ ከዐሥራ አምስት ቀናት በፊት የተነሳውን የዱር እሳት በቁጥጥር ስር የዋለ ቢምስልም በትናንትናው ዕለት አቅጣጫውን ወደ ሰሜቱ ክፍል አዙሮ 665 መኖሪያዎች ያሉት የአንድ የነዳጅ ማውጫ ድርጅት አዲስ የመኖሪያ ካምፕ አቃጠለ።
በኢትዮጵያ የተለያዩ ከፍሎች እየዘነበ ያለው ዝናብ በመሠረት ልማት ላይም አደጋ እያደረሰ መኾኑ እየተነገረ ነው። ዝናብ ሲዘንብ ለምን መንገዶች በጎርፍ ይዘጋጋሉ? ለምንስ ይሰነጠቃሉ? መንገዶቹ ሲሠሩ ለምን አስቀደሞ የጎርፉ ሁኔታ ከግምት ውስጥ አይገባም? ለኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሳምሶን ወንድሙ የቀረበላቸው ጥያቄ ነው። ጽዮን ግርማ አቶ ሳምሶን ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ እንዲሰጡ ጠይቃቸዋለች።
ሰሞኑን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽና በመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተሠራጩትን የተሳሳቱ ፎቶግራፎች በተመለከተ ባልደረባችን ጽዮን ግርማ “እንዲህ ያሉ ስሕተቶች ምን ያሳያሉ?” የሚል ጥያቄን አንስታ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን መምሕር አቶ አቤል አዳሙንና በዩናይትድ ስቴትስ ኦሪገን ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት ኮሙዩኒኬን የዶክትሬት ተማሪ አቶ እንዳልካቸው ኃይለ ሚካኤልን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ ሠርታልች።
ሴት አትሌቶች ራሳቸውን ከእንዲህ ያለ አደጋ ለመጠበቅ የሕይወት ክህሎት ሥልጠና እንደሚያስፈልጋቸው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ የጥናት ባለሞያ አቶ ስለሺ ብስራት ተናግረዋል።
ከአዲስ አበባ 131 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው መቂ አካባቢ ባሉ እርሻ ቦታዎች ቦታውን ስቶ የገባ ጎርፍ እርሻቸውን በሙሉ ከጥቅም ውጭ እንዳደረገባቸው የአካባቢው ገበሬዎች ይናገራሉ። እንዲህ ያለ የጎርፍ አደጋ ቀድም ብሎ ተከስቶ ያውቅ ስለነበረም ቦታው በአፈር እንዲገደብ አስቀድመው ጠይቀው ሰሚ አለማግኘታቸውን ይገልፃሉ። የአካባቢው አስተዳደድር በተፈጥሮ የመጣ ስለኾነ ምንም ማድረግ አይቻልም ይላል።
ወደ ከ86 ሺሕ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል፤ 400 ሺሕ ይፈናቀላሉ የሚል ስጋት አለ። በአየር ንብረት መለዋወጥ ምክንያት እየተቀባበሉ የሚከሰቱት ድርቅና የጎርፍ አደጋዎች የበርካታ ሰዎችን ሕይወት አደጋ ላይ የጣሉበት ዓመት ሆኗል - 2008። በድርቅና ዝናብ እጥረት የተነሳ 10.2 ሚሊዮን ሰው ለዕለት ደራሽ ምግብ ርዳታ ፈላጊነት ሲጋለጥ፤ ሰሞናቱን በስድስት ክልሎች ውስጥ በደረሱ የጎርፍ አደጋዎች እስካሁን 92 ሰው መሞቱን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል።
ከአንድ ቤተሰብ ስምንት ሰው ከእነ መኖሪያ ቤታቸው ተወስደዋል። የአምስቱ አስክሬን ሲገኝ ሦስቱ እየተፈለገ ነው።
በዛሬው ዕለት ከቀኑ ሰባት ሰዓት አካባቢ ከሌላ ቦታ የዘነበ ዝናብ ድሬደዋ ውስጥ የጎርፍ አደጋ አስከትሎ ነበር። አሁን የጎርፉ ኃይል ቢቀንስም ጎርፉን ለመከላከል የተሠራውን ግድብ በከፊል አፍርሶታል። በዚህም የተነሳ ነዋሪው ስጋት ላይ ወድቋል ሲሉ ነዋሪዎች ይናገራሉ።
እስካሁን ሺሕ ስድስት መቶ ሕንፃዎች ወድመዋል። ነዋሪዎች መጠለያ ውስጥ ገብተዋል። እስከ ዐሥራ አምስት ሺሕ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ይኖሩበታል በሚባለው በካናዳ አልበርታ ግዛት ፎርት መክመሪ ከተማ የተነሳውን ሰደድ እሳት መቆጣጠር ስላልተቻል ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው ውጥተው በመጠለያዎች ገብተዋል። ጽዮን ግርማ የአካባቢው ነዋሪን አቶ ሰይፈ መኮንን አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች።
እስከ ከዐሥር እስከ 15 ሺሕ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ይኖሩበት የነበረ አካባቢ ነው ተብሏል። ቤት ንብረታቸው እየወደመ ነው።
ዛሬ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ቀን ነው። ይህን ቀን ምክንያት በማድረግ “በኢትዮጵያ ያለው የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት ምን ይመስላል?” ስትል ጽዮን ግርማ የሂዩማን ራይትስ ዎች የጥናት ባለሞያ ፍሊክስ ሆርንና የደህንነት ጥናት ተቋም የጥናትና ምርምር ባለሞያ ሃሌሉያ ሉሌን ጠይቃለች። ሁለቱም ባለሞያዎች በኢትዮያ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት እጦት ተባብሷል ይላሉ። ሙሉ ዘገባውን ከዝግጅቱ።
በኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ ዋና ተጠቂዎች ሕናት በመሆናቸው፤ከስድስት ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ለምግብ እጥረት፣ለበሽታና ለትምህርት መስተጓጎል ተጋልጠዋል። የአሜሪካድምጽ ዘጋቢ ማርታ ቫን ደርዎልፍ በድርቁ ምክንያት የተጎዱና አሁን በሚሰጣቸው ሰብአዊ ርዳታ የሚተዳደሩ ሰዎች የሚኖሩበት መተሐራ አካባቢ ተዘዋውራ ያጠናቀረችውን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋልች።
በኢትዮጵያ በተከሰተው የድርቅ አደጋ ዋና ተጠቂዎች ሕጻናት በመሆናቸው ከስድስት ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ለምግብ እጥረት፣ለበሽታና ለትምህርት መስተጓጎል ተጋልጠዋል። የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ማርታ ቫን ደርዎልፍ በድርቁ ምክንያት የተጎዱና አሁን በሚሰጣቸው ሰብአዊ ርዳታ የሚተዳደሩ ሰዎች የሚኖሩበት መተሐራ አካባቢ ተዘዋውራ ያጠናቀረችውን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋልች።
በድሬደዋ ከተማ እና በአጎራባች ምስራቅ ሐረርጌ ከተሞች በትናንትናው ዕለት የዘነበው ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ሦስት ሰዎች ሞቱ፣ አንድ ሰው ቆሰለ። አንድ ባጃጅ እና ዩዲ መኪናም በጎርፉ ተወስዷል፡፡ ሳቢያን እየተባለ በሚጠራው ሰፈር የተገንባ ትልቅ ድልድይም ለሁለት ተከፍሏል። ጽዮን ግርማ የድሬደዋ ከተማ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ በየነን አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች።
በጋምቤላ ከተማ በስተምሥራቅ 17 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው ጃዊ የስደተኞች መጠለያ ሠፈር በደቡብ ሱዳን ስደተኞች በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉት ኢትዮጵያውያን ቁጥር 15 መድረሱን ነዋሪዎች ተናገሩ። በሥራ ላይ እያለ በድንጋይ እንደተወገረ የሚናገረው መብራቱ የተባለ አንድ የቀን ሠራተኛ፤ጊዚያዊ ሕክምና በነጻ ቢያገኝም መድኃኒት የገዛው በግሉ ተበድሮ እንደኾነ ይናገራል። ተጨማሪ ሕክምና አግኝቶ ከሕመሙ ማገገም ፍላጎቱ እንደኾነ ይገለጻል።
እስከአሁን ባደረግነው ክትትል በትናንትናው ዕለት 14 ኢትዮጵያውያን በደቡብ ሱዳን ስደተኞች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውንና አስከሬኖቻቸው ተለይተው ዛሬ ለዘመድ አዝማድ መላካቸውን ለሆስፒታል ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልፀዋል። አስክሬን ፍለጋው መቀጠሉ ተነግሯል።
ተጨማሪ ይጫኑ