አበረታች መድሃኒቶችና ቅመሞች ተጠቅመዋል በሚል በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌደሬሽኖች ማኅበር የጸረ አበረታች መድሃኒቶችና ቅመሞች ኤጀንሲ አማካኝነት ምርመራ ከተጀመረባቸው ስድስት አትሌቶች ውስጥ ሁለቱ ቅመሞቹን በትክክል መጠቀማቸው በመረጋገጡ ቅጣት እንደተጣለባባቸው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አስታወቀ።
በጎንደር ከተማ በነዋሪዎችና በፀጥታ ኃይሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት በመንግስት ታጣቂዎች ሕይወታቸው ያለፈ አቶ ሲሳይ ታከለ የተባሉ አንድ አዛውንት የቀብር ሥነ ስርዓት በዛሬው ዕለት በጎንደር ከተማ መፈጸሙን ነዋሪዎች ይናገራሉ። መንግሥት በግጭቱ አምስት ሰዎች በተባራሪ ጥይት ሕይወታቸው ማለፉን አስታውቋል።
ከኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልቀቂያ ፈተና ጋር በተያያዘ በመንግሥት ከተዘጋ አምስት ቀናት ስላስቆጠረው ማኅበራዊ ሚዲያ ጽዮን ግርማ የተለያዩ ሰዎችን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።
የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምሕርት መግቢያ ፈተና መሰጠት ከማኅበራዊ መገናኛ ድረ ገጾች መዘጋት ጋር መያያዙ እያነጋገረ ነው። አቶ አበባው አያሌው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጥበብና ዲዛይን ት/ቤት የኢትዮጵያ ሥነ ጥበብና ታሪክ መምሕር ናቸው። በልዩ ልዩ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ትንታኔ በመስጠትም ይታወቃሉ።
የቅዱስ ሮማዳን ወር ማብቂያ የሆነው 1437ኛው ኢል አል ፍጥር ዛሬ በመላ ዓለም ሙስሊሞች ዘንድ እየተከበረ ነው፡፡
የሥራ ባልደረባቸውና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ ዊሊ ኪማኒ፣ የደንበኛው ጆስፓት መወንዳ እንዲሁም የሹፌራቸውን ሞት ያስቆጣቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ የኬንያ የሕግ ባለሞያዎች ዛሬ በናይሮቢ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ። ሕገ-ወጥ ግድያን አስመልክቶ በዚህ ሳምንት የተካሄደ ሁለተኛው ትልቁ የተቃውሞ ሰልፍ መሆኑም ታውቋል።
በአዳማ ከተማ ከትናንት በስቲያ ለሊት በደረሰው ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ የተፈናቃዮች ቁጥር 4,500 መድረሱ ተነገረ። የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የከተማው ነዋሪዎች፤በጎርፍ አደጋው ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው መጠለያ ማጣቸውን ይናገራሉ።
ዩናይትድ ስቴትስ ከብሪታንያ ግዛት ነጻ የወጣችበትን 240ኛ የነፃነት በዓል ዛሬ ሃምሌ 4 ቀን እያከበረች ትገኛለች።
ትናንት ለሊት በአዳማ ከተማ በደረሰ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ሁለት ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።
የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ሀብታሙ አያሌው ከሀገር ወጥቶ እንዲታከም የቀረበውን የእግድ ይነሳልን አቤቱታ የተመለከተው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፤ አቶ ሀብታሙ በሀገር ውስጥ መታከም እንደማይችልና ሕክምናውን ከሀገር ውጪ ማድረግ አለበት የሚል በዶክተሮች የተወሰነ ማስረጃ ካቀረባችሁ በማንኛውም ሰዓት እግዱ ይነሳል እንደተባሉ ጠበቃው አቶ አመሐ መኮንን ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ።
በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለመዶ ሀና ማርያም፣ ፉሪ፣ ቀርሳ፣ ኮንቱማ እና ማንጎ ጨፌ በተባሉ አካባቢዎች የመኖሪያ ቤታቸው በዶዘር እየፈረሰና ወንዶች በአካባቢው እንዳይጠጉ መከልከሉን ነዋሪዎች ተናገሩ።
የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ሃብታሙ ሀብታሙ አያሌው ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ መምሪያ በነበረበት ወቅት፤ የጀመረው ሕመም ተባብሶ ራሱን መርዳት በማይችልበት ሁኔታ በሆስፒታል አልጋ ላይ እንደሚገኝ ቤተሰቦቹ ገለጹ።
በአዲስ አበባ ከተማ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀና ማርያም፣ ፉሪ፣ ማንጎ ጨፌ ሌሎች በክፍለ ከተማው ስር ባሉ መንደሮች ከቤት መፍረስ ጋር በተያያዘ የሰው ሕይወት ጠፋ።
ሌሎች 167 ድርጅቶች ደግሞ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸውና መሻሻል እንዲያደርጉ ዛሬ በተጠራ የምክክር ስብሰባ ላይ መታዘዛቸው ተዘግቧል፡፡
በሻሸመኔ ከተማ ጨለማን ተገን በማድረግ በሚፈፀሙ ወንጀሎች ሰዎች እየተገደሉ እንደሆነ፤ በሦስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሰባት ሰዎች መሞታቸውንና ግድያው የሚፈፀመው ደግሞ በፌሮ ብረት እና በስለት እንደሆነ በሻሸመኔ ከተማ የሚኖሩ ተማሪዎች ገለጹ።
ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሂውማን ራይትስ ዎች በኦሮምያ ተቃውሞ ወቅት ደርሷል ስላለው አስከፊ እና ተከታታይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት 61 ገጽ ያለው ሪፖርት ትናንት ማምሻውን አውጥቷል። በዚህ ሪፖርት መሰረት በኢትዮጵያ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ከ400 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር ፈተናው የሚሰጥበት ቀን ለአንድ ሳምንት ማራዘሙ ሀገር ውስጥ ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን አስታውቋል። ምክንያቱ ደግሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፈተናው ከረመዳን ጾም ፍቺ በኋላ እንዲሰጥ በመጠየቁ ነው ብሏል። የአሜሪካ ድምፅ ይህንኑ በተመለከተ በውጭ ሀገር የሚገኙ የኦሮሞ ተቃውሞ አስተባባሪዎች አቶ ጃዋር መሐመድን የድምጻችን ይሰማ የድጋፍ ግብረሃይል አቶ ሳዲቅ አሕመድን አነጋግሯል።
ዩናይትድ ስቴትስ ፕረዝዳንት ባራክ ኦባማ በኦርላንዶ-ፍሎሪዳ የተፈጸመውን ግድያ በማስመልከት ትላንት እሁድ በሰጡት መግለጫ “በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ አሰቃቂ ግድያ” ሲሉ አውግዘውታል። የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች የምሽት ከለብ ውስጥ የተፈጸመው ግድያ 50 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈ ሲሆን ሌሎች ከ50 በላይ ማቁሰሉን ታውቋል። የከተማዋ ባለሥልጣናት ግድያው የሽብር ተግባር መኾኖን ለማጣራት ምርመራ ላይ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።
ብራዚል ውስጥ የሚካሄደው የዘንድሮው “ሪዮ ኦሎምፒክ 2016” ሊደረግ ሃምሳ ሰባት ቀናት ብቻ ቀርተውታል። እንደ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አገላለጽ ይህ ጊዜ ለአትሌቶች የመጀመሪያ ልምምድ ጊዜያቸውን አጠናቀው ለሁለተኛ ልምምድ የሚዘጋጁበት ነበር። በኢትዮጵያ ግን በአትሌቶችና በትሌቲክስ ፌደሬሽን መካከል በአትሌቶች ምርጫ በተፈጠረ አለመግባባት ውዝግብ ላይ ናቸው። ጽዮን ግርማ ዘገባ አላት።
እያወዛገበ በሚገኘው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ጉዳይ በትምሕርት ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይና ከፍትኛ ባለሞያ አቶ አሕመድ ሲራጅ ሚስባሕን በትናንትናው ዕለት ክፍል አንድ ቃለምልልስ ማነጋገራችን ይታወሳል። ክፍል ሁለት ይቀጥላል።
ተጨማሪ ይጫኑ