እውቁ አሜሪካዊ ስቲቭ ሃርቬይ “ኪሪኩ ብራዘርስ” በሚል የቡድን መጠሪያ የሚታወቁ ሁለት ታዳጊዎችና ሁለት ወጣቶች የሰርከስ ትርዒት አቅርቦ ተመልካቹን አስደንቋል።
በባሌ ዞን በሰዌና ወረዳ ቡርቃ ጠሬ በተባለ መንደር የሚኖሩ ነዋሪዎች ላይ የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ተኩስ ከፍቶ ከአንድ ቤት ቤተሰብ አምስት ሰዎች ተገደሉ ሲሉ ለቤተሰቡ የቅርብ ምንጮችና አንድ የወረዳ አስተዳዳሪ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። በተጨማሪም የልጆቹ እናትና አንድ ልጅ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ገልፀዋል።
ከእስር በቅርቡ የተፈቱት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዷለም አራጌና ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ወልዲያ ናቸው።
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሀገር ውስጥ ለሚገኙ ለተፈናቀሉና ቤተሰቦቻቸው ለተገደሉባቸው ቤተሰቦች በዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት በኩል የሚያደርጉትን እርዳታ በተመለከተ ከሰብሳቢ አቶ ታማኝ በየነና ከትብብሩን አቅም ግንባታ ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ተሾመ ጋራ ውይይት አድርገናል።
"ለፍተሻ ሲያመጡት እጆቹን በካቴና ታስሮ ነበር” - ባለቤታቸው "አስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ሰዎችን ዝም ማሰኛና ትችንት ወንጀል ማድረጊያ መሳሪያ ነው”- አምነስቲ
በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ከግንቦት ሰባት ጋራ በመተባበር የሽብር ወንጀል ክስ ቀርቦበት ጉዳዩን በመከታተል ላይ የሚገኘው አቶ አስቻለው ደሴ በድብደባ የተጎዳውን የዘር ፍሬ እንዳይታከም እክል እንደገጠመው በዛሬው ዕለት ለፍርድ ቤት ማመልከቱ ተሰማ።
ስደተኞቹን የመመዝገብ ሥራው እንዳልተጠናቀቀም አስታውቋል። "አባቴን ቀብሬ ብቻዬን ቁጭ ብያለሁ" የሚለውን አባቱ የተገደለበት ወጣትና "እቤቴ ውስጥ ቁጭ ብዬ በጥይት ተመታሁ"የሚሉ በሆስፒታል ተኝተው በመታከም ላይ የሚገኙ የአምስት ልጆች እናት አነጋግረናል።
የኦሮሚያ ክልል ፍትሕ ቢሮ በሞያሌ ከተማ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈፀመው ግድያ በስሕተት የተፈፀመ ነው ብሎ እንደማያምን አስታወቀ።
በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በሞያሌ ከተማ “ሸዋበር” በተባለ የመኖሪያ መንደር በትናንትናው ዕለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በፈፀሙት ጥቃት ዐሥር ሰዎች ተገድለው ሌሎች ዐሥራ አንድ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች፣ የከተማው አስተዳደርና ኮማንድ ፖስቱ አረጋግጠዋል።
አብዛኛው የኦሮሚያ ከተሞችና አዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ ንግድ ቤቶች አስቸኳይ ጊዜ አዐዋጁን በመቃወም ዝግ ናቸው።
“ለኢትዮጵያ አምላክ ሰላም እንዲያወርድ እፀልያለሁ” - ባለቤታቸው የተገደለባቸው ልጃቸው የቆሰለባቸው እናት።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ አፀዳደቅ በሕገ መንግስቱ መሰረት ግድፈት አለበት ሲሉ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ፓርቲ አመራርና የሕግ ባለሞያ ገለፁ። በሀገሪቱ ሕገ መንግስት ላይ ዐዋጁ በሁለት ሦስተኛ ድምፅ መፅደቅ እንዳለበት በግልፅ እንደሚያስቀምጥና ይህ ድምፅ ደግሞ አለመገኘቱን ይናገራሉ።
በኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ፣በምዕራብ ወለጋ፣በምስራቅ ወለጋና በሆሮ ጉድሩ ወለጋ የሚገኙ አንዳንድ ከተሞች ውስጥ በዛሬው ዕለት በፀጥታ ኃይሎች በተወሰደ እርምጃ የሰው ሕይወት መጥፋቱን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
ጉዳዩን የሚከታተሉ ምሑራን ፤ የኢሕአዴግ ምክር ቤት አባላት ፓርቲያቸውን በየትኛውም መድረክ እንዲደግፉ የሚያስገድድ መታነፅ ወይም ዲስፕሊን እንዳላቸው ይናገራሉ።
ሦስቱ ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን አስታውቀዋል። የኢሕአዴግ ምክር ቤትና የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ለመወሰን በምክር ቤቱ በሚደረገው ምርጫ ላይ ለመወሰን ዕጩ ያላቀረብው ፓርቲ የተሻለ ዕድል እንዳለው ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ይናገራሉ።
በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት የምንኩስና ልብሳቸውን እንዲያወልቁ መገደዳቸውን በተመለከተ ለፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ላይ እስር ቤቱ ምላሽ እንዲሰጥ ታዟል።
በኢህአዴግ መንግሥትና መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ጉልህ ስፍራ የነበራቸው መኮንኖች በዛሬው ዕለት ከዝዋይና ቃሊቲ ማረሚያ ቤቶች መለቀቃቸው ታውቋል፡፡
- የሃይማኖት ልብሳቸውን እንዲያወልቁ መገደዳቸና መደብደባቸውን ለችሎት ተናግረዋል ተብሏል - ዛሬ ከእስር የተፈቱትን ኮሎኔል ደመቀ ይዘናቸዋል - በጎንደር እቤት ውስጥ የቀመጥ አድማ መካሄዱን ነዋሪዎች ገልፀዋል
በዛሬው ዕለት ለጋዜጠኞች በተሰጠው ማብራሪያ፤ ዐዋጁ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ከፀደቀ በኋላ ለቀጣይ ስድስት ተግባራዊ ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋል። ዐዋጁ በሁሉም የአካባቢው ክፍሎች እንደሚተገበርም ተናግረዋል።
ጠቅላይ ኢኒስትሩ በዛሬው ዕለት ለመንግሥት መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መገልጫ ያቀረቡት መልቀቂያ በፓርቲያቸው ደህዲንና በኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ተቀባይነት ማግኘቱን አስታውቀዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚጠብቁም ገልፀዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ