የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሞአማር ጋዳፊ አገር ጥለው ወደ ላቲን አሜሪካ ሳይኮበልሉ እንዳልቀሩ ተነገረ።
ቡና፥ ባህል፥ የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት መብት (Intellectual Property Rights) እና ልማት ምን ያገናቸው ይሆን?
በአመዛኙ በእግር ላይ አብጦ የሚታየው ይህ የደም ስር፥ በዘር ሊተላለፍ እንደሚችል የጠቆሙት የደም ስሮች ቀዶ ህክምና ባለ ሞያ፤ ባሉት የህክምና አማሮች በአግባቡ ከተረዳ አመርቂ ውጤት የሚገኝበት መሆኑንና እብጠቱንም ሆነ የህመም ስሜቱን ለመቀነስ የሚያስችሉ በህሙማኑ በራሳቸው የሚወሰዱ የመቆጣጠሪያ ዕርምጃዎች መኖራቸውንም ያስረዳሉ።
በግብፅ የተካሄደው የወጣቶች አብዮት፥ ለሰላሳ ዓመታት በጠንካራ መዳፍ አገሪቱን የገዙትን ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክን የማይነቃነቅ ይመስል ከነበረ መንበራቸው አወረደ።
ሙባረክ በስልጣን እስከ ቆዩ ድረስ ተቃዋሚው ወገን ዋስትና የለውም። የሚቀጥለው ምርጫ ከቀደሙት ለየት ያለ፥ ነፃና ገለልተኛ ምርጫ ይሆናል፤ የሚል እምነት የላተውም። ስለዚህ አስተማማኝ ለውጥ ይመጣል ብሎ ማመን ስለሚከብድ ነው፤ ፕሬዝዳንት ኦባማ፥ ሙባራክ አሁኑኑ ለውጥ እንዲያመጡ ጫና በማድረጉ የገፉበት።
አንድ ቡና ዓይነተኝነት ወይም መለያ ሲሰጠው፤ አተካከሉን፥ አበቃቀሉን፤ ሲታጠብ ያለው ሁኔታ፤ ቡናው በበቀለበት ባህል የሚጠጣበት ጨምሮ፥ ያንን ሁሉ አንድ ላይ ይዞ ይመጣል። መለያውም ይሆናል።
በወጣትነት የመዘንጋት አዝማሚያ በብዛት የሚከሰተው፥ በአመዛኙ በኑሮ ጫናና በውጥረት ነው። የአልኮል አዘውታሪነት፤ ከልክ በላይ ለረዥም ጊዜ አልኮል መጠጣት፤ ከሰዎች ጋር የመጋጨት፤ ትንሹን ትልቁን የሚያመርና ይቅር የማይል ባህሪ ባለቤትነት፤ አንዳንድ መድሃኒቶችና አንዳንድ ተላላፊ በሽታዎች ከመርሳት በሽታ ጋር ሊያያዙ ይችላሉ።
ሃኪምዎን ይጠይቁ፤ በመዘንጋት ችግሮች፥ ትውስታና የአዕምሮ አሠራር ዙሪያ ከመስኩ ባለ ሞያ ጋር በተካሄደ ቃለ ምልልስ ለዚህና ለሌሎች ተዛማች ጥያቄዎች፥ ምላሽ ያፈላልጋል።
የኢትዮጵያ ሥነ ፅሁፍ ዘመን የጠገበ ታሪካዊ መሠረት ቢኖረውም ያን ያህል ለማደግ ለመበልፀግ ግን አልታደለም። ጥበቡ ብቻ ሳይሆን ጥበበኛውም እንደተሰቃየ ነው፤ ለማለፍ የተገደደው፤ ይላሉ ተወያዮቹ። መፅሃፍት የማንበብ ልማድ፥ ህትመትና ስርጭት ውይይቱ የሚያተኩርባቸው አቢይ ነጥቦች ናቸው።
«እኔ ”ተቃዋሚ” ነኝ፤ ብዬ አላምንም። ጋዜጠኛ ነኝ። ዕውነትን መዘገብ መቀጠል ነው የምፈልገው። ያ በተቃዋሚነት ካስፈረጀኝ ግን፤ በዚያ መልኩ ለፈረጁኝ ሰዎች አዝናለሁ።» ከተሸላሚዎቹ አንዱ ዳዊት ከበደ።
‘ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው አደገኛ ሁኔታ አንፃር ትንሽ ያስፈራል፤ ምንም ጥያቄ የለውም። ግን በፍርሃት አስተዋፅኦ ማድረግ አይቻልም። ስለዚህ ፍርሃትን በማሸነፍ ያቅማችንን አስተዋፅኦ እያደረግ ነው።’ ሲሳይ አጌና።
ሃኪምዎን ይጠይቁ፥ በሃኪም የሚታዘዙ ፀረ-ተህዋስያን መድሃኒቶችም ሆኑ ያለ ሃኪም ትዕዛዝ የሚወሰዱ መድሃኒቶችን ስንጠቀም ማወቅና ማድረግ የሚገቡን ጥንቃቄዎች።
የመጨረሻ ሪፖርቱን በአዲስ አበባ ይፋ እንዳያደርግ የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደውን የማገድ እርምጃ «ኢ-ዲሞክራሲያዊ ነው፤» ሲል የነቀፈው የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑካን ቡድን፤ በምርጫ ትዝብቱ ተመለከትኩ ያላቸውን ግድፈቶች በዛሬው ዕለት በብራስልስ ባካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫው ዘርዝሯል።
ሪፐብሊካኖች ምርጫውን አሸንፈው ሁለቱንም ምክር ቤቶች ወይም አንዱን ብቻ እንኳን ከቆጣጠሩ፥ የፕሬዝዳንት ኦባማ አስተዳደር በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከተላቸውን ፖሊሲዎች አስመልክቶ በርከት ያሉ ለውጦች ሊመጡ ይችላሉ።
ሁለት ዓመታት ከተቃረበ እስር በኋላ በቅርቡ የተለቀቁት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀ መንበር ወ/ሪት ብርቱካን «ይቅርታ፥» - የእስር የተለቀቁበት ሁኔታና የእስር ቤት ቆይታ እያነጋገረ ነው።
የፖለቲካ ሳይንስና የህግ ምሁር፥ ጋዜጠኛና «ወ/ሪት ብርቱካን ነፃ ይውጡ፤» የተባለው ቡድን አንዲት ወጣት አባል ይወያያሉ።
ያሬድ ከዩናይትድ ስቴትሷ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ሂላሪ ክሊንተን ዕጅ ሽልማቱን ተቀበለ
«የቡድሂዝም መሠረታዊ ባህሪያት ተብለው የሚጠቀሱት፥ ተፈጥሮ ጊዜያዊና አላፊ መሆኗ፤ ተፈጥሮ በሥቃይ ዑደት ውስጥ መመላለሷና በተፈጥሮ ውስጥ የሚከሰቱ ሁነቶች በሙሉ በሳቢያና ውጤት ሰንሰለት የተሳሰሩ መሆናቸው ነው።»
ኢትዮጵያ ወደ አገር በምታስገባውና ወደ ውጭ በምትልከው ምርት መካከል ያለው የገንዘብ መጠን ልዩነት ከምንዛሪ ቅናሹ ሊያመጣ የሚችለውን ለውጥ ላያስገኝ ይችላል ተባለ።
ተጨማሪ ይጫኑ