ከምርጫ 2002 በኋላ መድብለ ፓርቲ በኢትዮጵያ አብቅቶለታል ይላሉ አንዳንድ ተቃዋሚዎች። መንግስቱን የሚደግፉ ኢህአዴግ በአብላጫ ድምጽ ጎልቶ ወጣ እንጂ ብቸኛ አልሆነም ሲሉ ይከራከራሉ።
«አዲስ ዘይቤ ሲጀመር ሳታስበው ስለሱ ብዙ ታነባለህ፤ በእርሱ ላይ ብዙ ሰላስላለህና ወደድክም ጠላህ፥ ጭንቅላትህ የፀነፀው ሃሳብ ቅርፅ ይዞ ሲወለድ፥ እርሱን ነው የምትወልደው።»
“አልዛሃይመር ከዕድሜ ጋር የሚጣ በሽታ እንደ መሆኑ ዕድሜያቸው ከ65 እስከ 75 ከሆኑት 7 በመቶው፤ ከ85 በላይ ከሆኑ ደግሞ እስከ 25 በመቶ የሚሆኑት ለበሽታው ሊጋለጡ ይችላሉ።” ዶ/ር ዮናስ እንዳለ
“ሠዎች ደስ ብሏቸውና በፈገግታ ተመልተው ሳይ ደስ ይለኛል። ለዚህም ነው የማላቃቸውንም ቢሆን በቀና መንፈስ የማቅፈው፤” አይሻ ኪንግ
በህፃናት የተሰሩ ሃያ ሦሥት ባለ አንድ ደቂቃ ፊልሞች በአዲስ አበባ ለእይታ ቀርበዋል። ልሞቹን የሰሩት ከዘጠኝ እስከ 15 አመት እድሜ ያላቸው ታዳጊ ህፃናት ናቸው።
ሴቶች ቫይረሱ ካለበት ወንድ በሽታው እንዳይተላለፍባቸው የሚያስችላቸው ቅባት መሰል መድሃኒት በደቡብ አፍሪካ አጥኝዎች ይፋ ተደርጓል።
«ሠልፉ፥ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በቅርቡ ያወጣውን መግለጫ በመደገፍና ተጨባጭ የፖሊሲ ለውጥ ዕርምጃዎች እንዲታገዝ ለመጠየቅ የተዘጋጀ ነው፤» ዶ/ር ካሳ አያሌው፤ ከሠልፉ አስተባባሪዎች አንዱ።
«ማንም ሰው በምንም ዓይነት ሁኔታ እንዳይዋከብ፤ የልማት ሥራው እንዳይስተጓጎል ግልፅ የመንግስት መመሪያ ወጥቷል፤» አቶ መስፍን አሰፋ።
«የምርጫ ታዛቢ ሆነው ባቀረቡት ትችት የአንድ አባሌ ባለቤት ተገደሉ፤» መኢአድ። «በደጋፊዎቼ ላይ የሚደርሰው ወከባ አሁንም ቀጥሏል፤» የኦሮሞ ኅዝብ ኮንግሬስ።
የሰብአዊ መብት ቡድኑ የኢትዮጵያ መንግስት «ኢህአዴግን ካልመረጣችሁ ሥራችሁን ታጣላችሁ፤» የሚለውን ማስጠንቀቂያ ጨምሮ አዳዲስና አስገዳጅ የማዋከቢያ ዘዴዎችን በመጠቀም ግፊት ሲያደርግ ቆይቷል ብሏል።