ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የፓርቲዎቻቸው እጩ በመወዳደር ላይ ያሉት ተፎካካሪዎች ውድድሩን ወደ ኒው ሃምፕሸር አዙረዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ድርጅት (CDC) ዲሬክተር ዶ/ር ቶም ፍሪደን “ወደ ላቲን አሜሪካ ከተደረገ ጉዞ ጋር ሳይያያዝ በዩናይትድ ስቴትስ መኖሩ በላቦራቶር ምርመራ የተረጋገጠ የመጀመሪያው የዚካ ቫይረስ ክስተት ነው፤” ብለዋል።
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በቦልቲሞር ከተማ በሚገኝ መስጊድ ተገኝተው፣ የቦልትሞር የሙስሊም ማኅበረሰብ በተባለ ተቋም የእስልምና እምነት ተከታይ ከሆኑ አሜሪካውያን ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል።
የዚካ(ZIKA) ቫይረስ ወረርሺኝ የተከሰተው በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ዘንድሮ ብራዚል በምታስተናግደው የኦሊምፒክ ውድድር ላይ ለመገኘት እየተዘጋጁባሉበት ወቅት ነው።
“መቶ ሰማኒያ ወይም መቶ አርባ ሰው ሲሞት፤ ሌላ አገር ቢሆን ባንዲራ ዝቅ ተብሎ የአገሪቷ ብሔራዊ ሃዘን ይደረጋል። ሰው ነው፤ ታዳጊዎች ናቸው፤ ልጆች ናቸው ነገ አገር ሊመሩ የሚችሉ ናቸው የሞቱት። እንዴት ብዬ ልነግርህ እንደምችል አላውቅም። ሰው ሲሞት አገር የሚያስተዳድር ዝም ማለት? ምን እንደምል አላውቅም። አስቸጋሪ ነው።”
“መጠለያና ከለላ ፍለጋ ወደ አውሮፓ ከሚፈልሰው ሕዝብ መሃል የሆኑት ሴቶችና ሕጻናት ለከፉ የጾታ ጥቃቶች ይጋለጣሉ” በቅርቡ ይፋ የሆነ የተባበሩት መንግስታት አዲስ የጥናት ዘገባ።
ከሁለት ወራት በላይ ያስቆጠረው የተቀሰቀሰው የተቃውሞ እንቀስቃሴ፣ ዛሬም በአንዳንድ አካባቢዎች መቀጠሉ እየተዘገበ ነው።
“ካራ በተባለ ሥፍራ ነው፤ ዛሬ ጠዋት አራት ሰዓት ላይ ፖሊስ ተኩሶ የገደለው። በቀደመው ሰልፍ ላይ በመሳተፉ ነው፤ የተገደለው።” አንድ የሚኤሶ ከተማ ነዋሪ። “በመጀመሪያ ልዩ ፖሊስ ኃይል የሚባል በወረዳችንም ሆነ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የለም። ይህ ፕሮፖጋንዳና የሃሰት ወሬ ነው። በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ሥርዓት መሠረት ሰው በሰላም የመኖር መብት አለው።” አቶ መሃመድ ጀማል የሚኤሶ ወረዳ ምክትል ሊቀ መንበር።
"የሕዝቦቻችንን ጥቅሞች ማዕከል ያላደረጉና ሕዝብን ያላሳተፉ በልማት ስም የሚካሄዱ እርምጃዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙና የሃገሪቱ ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌዎች እንዲጠበቁ እንጠይቃለን።” መድረክ።
በኦሮሚያ ክልል የአዲስ አበባንና የፊንፊኔን ልዩ ዞኖችን ለማቀናጀት የተነደፈዉን ማስተር ፕላን በመቃወም የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ትላንትና በዛሬዉ እለት በጂማና በሃሮማያ ዩኒቬርሲቲዎች ተካሂደዋል፥ የመንግስት ጸጥታ አስከባሪ ሃይሎችም ተማሪዎቹን በመደብደብ ተቃዉሞዉን መበተናቸዉ ታዉቋል።
የበሽታዎቹን መከሰት ከወዲሁ የሚጠቁሙ አስቀድመው የሚታዩ ምልክቶች ይኖሩ ይሆን? የስኳር ሕሙማን በራሳቸው ሊወስዱ የሚችሏቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች ይኖሩ ይሆን? የስኳር በሽታን ተከትለው የሚከሰቱት አሳሳቢዎቹ የዓይን ሕመም ዓይነቶች የትኞቹ ናቸው? ተከታታይ ቅንብሮቹ የሕክምና አማራጮቹን ጨምረው ሕሙማንና የቤተሰብ አባላት ሊጠይቁና ሊመልሱ የሚሿቸውን ጭብጦች ይዳሳሳሉ።
በኦሮምያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ትምሕርት ቤቶች ተማሪዎች መሰንበቻውን በማካሄድ ላይ ያሏቸው የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ዛሬም ቀጥለዋል።
ከአዲስ አበባ አቅራቢያ የሚገኙ አርሶ አደሮችና ነዋሪዎች ተገቢ ካሳ ሳያገኙ ከይዞታቸው ሊፈናቀሉ ይችላሉ፤ በሚል ስጋት የተቃውሞ ሰልፍ እያካሄዱ ባሉበት የተማሪዎች ተቃውሞ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች እየተስፋፋ ነው፤” ሲል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት (Human Rights Watch) ዘገበ።
ዲሞክራሲ፥ ለዜጎች እኩል የተሻለ እድል የሚሰጡ ምርጫዎችና መጪው ጊዜ፤
“ቀድሞ የአምስት ሜትሮች ጥልቀት የነበረው የቻድ ሃይቅ ዛሬ ከአንድ እስከ አንድ ነጥብ አምስት ሜትር ጥልቀት ብቻ ነው ያለው። የሰው ልጆች አንዳች ሁነኛ እርምጃ በአፋጣኝ ተግባር ላይ እንዲያውሉ የሚጠይቅ የክፍለ ዘመኑ የከፋ ውድመት እየደረሰ ያለው።” የቻዱ ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ ናቸው። የዓየር ንብረት መዛባት ባስከተለው ጉዳት ክፉኛ እየተራቆተ ስላለው የቻድ ሃይቅ ከተናገሩት የተወሰደ።
ከሰላሳ በላይ ዓመታት፤ ከስድስት በላይ ቤተሰቦችና ልጆቻቸው የምሥጋና ቀን አከባበር ልማድና ወግ፤
የሳምንቱ የእረፍት ጊዜ የእሁድ ምሽት የመዝናኛ ምርጫችሁ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ።
የዓለም የጤና ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ጠንካራ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጥሪ መግለጫ አውጥቷል።
ተጨማሪ ይጫኑ