የስኳር በሽታን ተከትለው በዓይን ላይ የሚደርሱ ዋና ዋና የጉዳት ዓይነቶች ምን ይሆኑ? አስቀድሞ የሚታዩ ምልክቶችስ ይኖሩ ይሆን? ተከታታይ ቅንብራችን የሚመለከታቸው ጭብጦች ናቸው።
በፓሪስ የደረሰውን የሽብር ጥቃት ከፈጸሙት አጥፍቶ ጠፊዎች አንዱ የሶሪያ ፓስፖርት የያዘ እናም ባለፈው ወር ግሪክን በጀልባ አቋርጠው ወደ ፈረንሳይና ሌሎች አገሮች ከዘለቁት ስደተኞች ጋር መጓዙ ታውቋል።
በሶማሊያዋ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች በተጠለሉበት ካምፕ በወታደሮች መካከል በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ ሰባት ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል።
“ሃብት ያለው ሰው አይታሰርም። ተፈርዶባቸው እስር ቤት ያሉ ባለ ሃብት መንገድ ላይ ሲሄዱ ሌላ ሰው ገጭተው ሌላ ክስ ተመሠረተባቸው። አቃቤ ሕግ ምሥክር ማስፈራራት የሃሰት መረጃ ማስጠናት። በጥናቱ ካገኘናቸው ውስጥ ናቸው።” አቶ ተካ ገብረ የሱስ፤ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዲሬክተር።
ዑጋንዳ በኤልኒኞ ሳቢያ ሊከተል የሚችለውን እጅግ ከባድ ጎርፍና የመሬት ናዳ ለመቋቋም እየተሰናዳ መሆኑን መንግስት ይፋ አድርጓል።
ወጣ ገባው የታየበት ግንኙነት ያላቸው ሁለቱ መሪዎች ለመጨረሻ ጊዜ ተገናኝተው ከተወያዩ ከአንድ ዓመት በላይ ሆኗቸዋል።
አንድ የቀድሞ የዮርዳኖስ ፖሊስ ባደረሰው ጥቃት ሁለት አሜሪካውያን ወታደራዊ አሰልጣኞችና አንድ ደቡብ አፍሪቃዊ ሲገድሉ ሌሎች ስድስት ሰዎች ቆስለዋል።
አዳዲሶቹ የካናዳ ምክር ቤት አባላት ቃለ-መሓላ እየፈጸሙ መሆናቸው ተሰማ፣ አንዱ ተመራጭ የሶማልያ ተወላጅ መሆናቸውም ተገለጸ።
በኢልኒኞ የዓየር ጠባይ ለውጥ ምክንያት የደቡብ አፍሪቃ ግብርና ዘርፍ መጠቃቱ ታውቋል።
አብዛኛውን ቻይናውያን ጥንዶች፤ ከአንድ ልጅ በላይ እንዳያፈሩ የሚያስገድደውና ሰላሳ አምስት ዓመታት ያስቆጠረው ሕግ ተሻረ።
“ዋናው የሚያሳስበን ነገር ጸሃፊዎችን ለማፈን ብሔራዊ ጸጥታ ወይም ደህንነት የሚባለው ሰበብ እንደ መሳሪያ ሥራ ላይ እየዋለ ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን፤ በሌሎች የአፍሪቃ አገሮችና በዓለም ዙሪያም እየተስፋፋ መምጣቱ ነው።”
“ዛሬ ከበለጸጉት ያለም አገሮች ተርታ የምትገኘው እስራኤል ራሷ ከጥቂት ዓመታት በፊት በመልማት ላይ የነበረች አገር ናት። የአፍሪቃ ሕብረት እስራኤልን ቢደግፍ አሕጉሪቱ ይበልጥ የምትጠቀምበት ሁኔታ ይፈጠር ነበር።” ሻሮን ባር-ሊ በእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የአፍሪካ ምጣኔ ሃብት ጉዳዮች ዲሬክተር።
ግጭቱ ከመቀስቀሱ አስቀድሞም በቋፍ የነበረው የተጎራባቾቹ ብሩንዲና ሩዋንዳ ግንኙነት ከባሰ ውጥረት ከመግባቱም ባሻገር አንዱ የሌላውን ባለጋራ ያግዛል በሚል መወነጃጀል ይዘዋል።
ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን እስካሁን በእስርዓይ የሚገኙት አራቱ የዞን ዘጠኝ አምደኞችና ጋዜጠኞች ክሳቸው እንዲነሳና ከእስር እንዲለቀቁ ጉዳያቸውን የሚያየውን የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ጠየቀ።
“እርቅ ማለት ነው። መስማማት፥ አንድነት፤ እግዚአብሔር ታረቀን ማለት ነው” በእሬቻ ምንነት ላይ መጽሐፍ የጻፉ ተወያይ።
“አንድ የተፈረደበት የሕግ እስረኛ ከቦታ ወደ ቦታ መንቀሳቀስን ጨምሮ የሚታገዱበትና የሚከላከላቸው በርካታ መብቶች አሉ። የሕክምና አገልግሎት የማግኘት መብት ግን ከሚከለከሉት አንዱ አይደለም።” የሕግ ጠበቃው።
ሪቻርድ ሰተንግል (Richard Stengel)፡ "አንድ ብቸኛ መንገድ የለም። ISIL ወጣቶችን እየፈተረከ የሚወስድባቸው በጅምላ የሚሰሩ የማኅበረሰብ መገናኛዎች አይደሉም ዋነኞቹ መንገዶች። በዚያ አንድ ሰው ላይ የተነጣጠሩ መልዕክቶች፤ የስልክ ግንኙነቶችና የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃንን የተጠቀሙ ዘዴዎች ናቸው መንገዶች። የISIL’ን የዩቱብ ቪዲዮዎች በመመልከት ብቻ ጽንፈኝነትን የሚላበስና የራሱ የሚያደርግ ሰው የለም።”
«ባለሥልጣናቱ እያሉ ያሉት ተመክሮ ‘እንቀስማለን’ የሚል ነው። ዝም ብሎ ማሰርና መግረፍ ትክክል ስላለመሆኑ (የግድ) ከአሜሪካ መማር የለብንም። ይቺ አገር እኮ ብዙ ሺህ ዓመት የቆየች አገር ነች።» ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ።
ተጨማሪ ይጫኑ