የገዳ ሥርዓት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምሕርት፥ የሳይንስ እና የባሕ ተቋም ዩኔስኮ የማይዳሰስ ወካይ የዓለም ቅርስነት ተመዘገበ።
“አይበለውና ከአንዳች የቁማር መጫወቻ ሥፍራ ብሆን፤ ይህ ምርጫ እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር በ2012ዓ.ም. ከተካሄደውም ሆነ ከዚያ በፊት ከተካሄደው ይበልጥ የተበታተነችና ንቅዘት የተንሰራፋባት ሶማሊያን እንድትፈጠር ምክያት ይሆናል ብዬ ባለፉት ሰላሣ ዓመታት በሥራዬ ያጠራቀምኩትን ገንዘብ ለውርርድ አቀርባለሁ፤ የሚታየው ሙስና በቃላት መግለጥ ከሚቻለው በላይ ነው።” በሜኔሶታ የሚኖሩ የሶማሊያ ተወላጅ
“በዚያ በከፋ ጦርነት ተጠምደው እንደነበሩት አያት እንደ ቅድመ-አያቶቻቸው ሁሉ አሜሪካውያን ዛሬም መልካም ተመልካችና ነገን በቀና የሚያስቡ ሕዝቦች እንደመሆናቸው፤ የዛሬውንም የምሥጋና ቀን ክብረ በዓል ከወዳጅ-ጓደኞችና ቤተሰቦች ጋር በመሰባሰብ፤ እንደ ትላንቱ ሁሉ ዛሬም የበዓሉን መልካም መንፈስ ተላብሰው፤ በነጻ ምድር የሚኖሩበትን የነገ ተሥፋና የህይወትን በረከቶች በማወደስ እና በምሥጋና ያከብራሉ።” የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ
አንዳንድ ከፍተኛ የአመራር አባላቶቻቸውን ጨምሮ በርካታ አባላትና ቁጥራቸው የበዛ ደጋፊዎቻቸው የታሰሩባቸው መሆኑን፤ ከታሰሩባቸው የአካባቢ እስር ቤቶች ዘመድ ጠያቂ ወደማያገኙባቸው ካምፖች አዛውረዋቸዋል ሲሉ ሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎች አማረሩ።
የቀድሞው የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት እና የአማፂያኑ መሪ ሪች ማቻር የኢትዮጵያ መንግሥት ከሀገሩ እንዲወጡ ማድረጉ ተነግሮኛል ሲል የደቡብ ሱዳን መንግሥት አስታወቀ።
የሳምንቱ የእረፍት ጊዜ የእሁድ ምሽት የመዝናኛ ምርጫችሁ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ።
ካሜሮን ውስጥ በአሳለፍነው ሣምንት የሥራ ማቆም አድማ በመቱ ጥበቆችና በፖሊሶች መካከል ግጭት የቀላቀለ ፍጥጫ እንደነበር ተዘገበ። ካሜሩን ሁለት የሥራ ቋንቋዎች አሏት እንግሊዝኛ እና ፈረንሣይኛ።
ዴሞክራትዋ ዕጩ ፕሬዚዳንት ሂላሪ ክሊንተን እጅግ አስደንጋጭ በሆኑ ቁጥር በቢሊዩነሩ ነጋዴ ዶናልድ ትራምፕ ድል ተመተዋል፡፡
“ኢትዮጵያዊነትን፣ የባሕል እሴቶቻችንን የያዙ ምርቶች ለመሥራት ነው አሁን ሙሉ ጊዜዬን የሰጠሁት። ይከብዳል ግን ዓላማዬ አድርጌው ተነስቻለሁ።” የፎቶግራፍ ጥበብ ባለሞያው ዮሃንስ አስረስ።
በመቶዎች የተቆጠሩ የፈረንሣይ ፖሊሶች ዋና ከተማ ፓሪስ ሰሜን ምሥራቅ ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ ግዙፍ የሆነ የፍልሰተኞች ካምፕ ዛሬ ማፈራረስ ጀምረዋል።
የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት፥ በሃገሪቱ ያንዣበበውን አደጋ ለመቀልበስ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ማወጁን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አስታወቁ።
“የዚህ ሕግ ዓላማ ሙሉ በሙሉ የተጻፈውን ነገር ሁሉ ተግባር ላይ ማዋል አይመስለኝም። ዋና ዓላማው የሥነ ልቦና ጫና ማሳደር ነው።” መስፍን ነጋሽ። “መሬት ላይ ያለውን እውነታ መቀበል እንደ ትልቅ ሽንፈት ስለተቆጠረ በኢህአዴግ ዘንድ እያወቁ እንዳላወቁ የመሆን ነገር ነው የነበረው። ... ወደ መፍትሄዎቹ እንኳን መንገድ እንዳንጀምር። ከዚህ መሠረታዊ ሥህተት ይነሳል።” አርጋው አሽኔ።
“እነዚህ እርምጃዎች ሥርዓትን ለመመለስ የታሰቡ ቢሆኑ እንኳ - ነፃ ድምፆችን ማፈንና በኢትዮጵያዊያን መብቶች ውስጥ እራስን የሚጎዳ ጣልቃ ገብነት ማድረግ ለብሦቶቹ መፍትኄ ከማግኘት ይልቅ ሁኔታዎችን የሚያባብሱ ነው የሚሆኑት፡፡”
“ችግሩ የአሁንና አዲስ ሳይሆን፤ ለረዥም ጊዜ ሲታፈን የቆየ ችግር ነው። ሰው እንዳይሳተፍ፥ ሕዝብ እንዳይነጋገር፥ ሃሳብ እንዳይንሸራሸር፤ የአንድ ወገን ብቻ ጥቅም እንዲጠበቅ በመደረጉ ነው። ፌድራሊዝም ደግሞ ፈጽሞ ሊኖር የማይችለው እንዲህ ባለ ክፍተት ሲደረግ ቆየ። አንደኛው ችግር እንደዚህ ያሉ ችግሮች በየአካባቢው በመታፈናቸው የመጣ ይመስለኛል።” አቶ ክቡር ገና
“ዶናልድ ትራምፕ እያደረጉ ባሏቸውና በተለይም በቅርቡ የታዩት መረጃዎች የተነሳ የሕዝብ አስተያየት ድምጽ ወደ ሂላሪ ክሊንተን አዘንብለዋል። ነገር ግን የመጨረሻው ግን ማን ወጥቶ እንደሚመርጥ፤ ማን እንደሚያሸንፍ እስከ መጨረሻዋ ቀን አይታወቅም።” አቶ ዮሃንስ አሰፋ የሕግ ባለ ሞያ።
“ዜጎች ለመብቶቻቸው ዘብ የመቆም አማራጭ በማጣታቸው ነው ትግሉ ወደ ሕዝባዊ እምቢተኝት ያደገው።” አቶ በትሩ ገብረ-እግዚብሔር በዳላስ ቴክሳስ የሞርጌጅ ባንክ ባለ ሞያ። “ከዚህ አጣብቂኝ ለመውጣት ሌሎች በተመሳሳይ መንገድ ያለፉ አገሮችስ ምን አደረጉ? በሚል መጠየቅ ተገቢ ነው። ዓይንህን ለአፈር የሚለው የሚገባ አቋም አይመስለኝም።” ፕሮፌሰር ብርሃኑ አበጋዝ በዊልያም ኤንድ ሜሪ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት መምሕር እና የትምህርት ክፍሉ ሊቀ-መንበር።
“በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ በዓሉን የምናከብርበትን መልክ ለውጦታል።” ዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት።
ከዋሽንግተን ዲሲና ከአካባቢው እንዲሁም ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የመጡ ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በዛሬው እለት በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት፣ በዋይት ሃውስ እና በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ደጃፎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ።
የአዲስ ዓመት ልዩ እንግዳ በአገር ጉዳይ በራዲዮ መጽሔት ወጎች ይነጋገራሉ፤ ዕለቱን የመሰለ ሥነ ግጥም፤ የአውደ ዓመት ገበያና ሰሞንኛ ጉዳዮች አሜሪካ ድምጽ ራዲዮ።
የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ አውጪ ምክር ቤት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ የተነጣጠረ ረቂቅ ውሳኔ በዛሬው ዕለት ይፋ አደረገ።
ተጨማሪ ይጫኑ