“ይሄ ፊልም ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፏል። ብዙ ላብ ፈሶበታል። ... ልክ እንደ ሥሙ መቋጫ የሌለው ዙር ሆኖ ይነጋል ይመሻል። ቀረጻ ይቀረጻል። ... ዙሩ አላልቅ ስላለ ብዙዎች እንደ ምትሃት አይተውት ነበር።” ተመስገን አፈወርቅ የተከታታይ ፊልሙ ደራሲ።
“ሁለት ነገር ነው። አንደኛው ለመረዳት መፍቀድ ወይም ያለመፍቀድ፤ ሁለተኛው ደግሞ መቻል እና ያለመቻል ነው። አንድን ነገር ለመረዳት ፍቃድ ሲኖር ነው ጥልቀት ያለውን የችግሩን መጠን ማወቅ፤ መፍትሄውንም ማየት የሚቻለው። በተዘጋ ልብ ምንም እውነት አይገለጥም።” ቴዲ አፍሮ።
ሕይወትና ሙዚቃ በጥበባዊ ሥራዎቹ ለማኅበረሠብ ባበረከተው አጽተዋፅፆ ከዩናይትድ ስቴትሱ የኢትዮጵያውያን የሽልማት ድርጅት የተሰጠ ክብርና ዕውቅናም ከቴዲ ጋር የምናደራው ወግ አካል ነው።
የሳምንቱ መገባደጂያ የእሁድ ምሽት የእረፍት ጊዜ የመዝናኛ ምርጫችሁ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ። የኢትዮጵያውያን የሽልማት ድርጅት ሃያ አምስተኛ ዓመት፤ የአገር የሙዚቃና የሥነ ግጥም ወጎች፤ “ኢትዮጵያ ትቅደም” በንጉሴ አክሊሉ የአዲስ አበባ የድምጽ መስኮት እና ሌሎች ወጎች
“በልጅነት የተጫወትነው ጫወታ .. 'እረ-አምሳለ' .. ያ ሁሉ ሕጻን የናፈቃት 'አምሳለ ማን ናት ምሳሌዋ?' ስል እጠይቅ ነበር። አምሳለን ብዙ ሰው እንደፈለገ ሊያስባት ይችላል። በግጥሙ አምሳለ እናት ልትሆን፥ ሃገር፥ ፍትህ ልትሆን ትችላለች። ነጻነት ሊሆን ይችላል። አምሳለን የሚፈልጉትም ሕጻናት መሆናቸው ራሱ ሕጻናት ንጹህ በመሆናቸው፤ እነሱ የናፈቋት አምሳለ ዓለም ላይ ምን ያህል ለውጥ እንደምታመጣ ለማሳየት ነው።” ወጣት ገጣሚ ምልዕቲ
"..ቤት ውስጥ ኦሮምኛ፥ ገበያ ጋሞኛ ትምሕርት ቤት ደግሞ አማርኛ ይናገራሉ። ጋሞነቴና ኢትዮጵያዊነቴ ተጣልተውብኝ አያውቁም፤ ይላል። ..በቃ አሁን ያለንን ክስረት አውቆታል። ደራሲ እንዳለ ጌታ ከበደ። በጣም ይቅር ባይ ልብ ያለው ሰው ነው። ለምሳሌ ያህል፥ በትዝታ ፈለግ.. (መጽሃፉ) መግቢያ ላይ ጠላት የለኝም’ ብሎ ይጀምራል። እውነቱም ለመናገር ከተፈለገ ግን፤ በጸጉሩ ልክ ጠላት ያለው ሰው ነው። ምክኒያቱም ፊት ለፊት ነው የሚነግራቸው። ደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላ።
“በአንድ ወቅት ልዩ ኃይል ያቋቋመ፤ የአውሮፕላን ጠለፋ በኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የየዕለት ሥራ ላይ ከፍተኛ አደጋ በደቀነበት ወቅት የመጀመሪያውን የበረራ ደህንነት ተቋም የቆረቆረ እና በሬንጀር በዓየር ወለድ፥ በመረጃ ትምሕርትና ሌሎች የወታደራዊ ሳይንስ ትምህርት ዘርፎች የሰለጠነ፤ ተዋጊና በጦር ትምሕርት መምሕርነት ጭምር ያገለገለ ወታደር ነው።” የመጽሃፉ ደራሲ ዶ/ር ስንታየሁ ካሳ
“የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ባይታወጅ ኖሮ የት ነው የሚቆመው አመጹ? የት ነው ጋብ የሚለው ነገር በጣም አጠያያቂ ነው የነበረው።” አቶ አታክልት አምባዬ። “የአስቸኳይ ጊዜውን አዋጁን ያወጁትም ሰዎች መፍትሔው እንፈልጋለን መፍትሔ አልተፈለገም። መፍትሔው ምንድ ነው? ችግሩ ምንድነው? የሚለው ነገር ላይ ውይይት አላየንም።” አቶ ፈቃደ ሸዋ ቀና።
“በተለያዩ ሁኔታ በፍርድ ቤት ሂደቶች አልፈው ጉዳያቸው ሳይሳካላቸው ቀርቶ ነገር ግን ወንጀል ስለሌላቸው ሊሆን ይችላል ከአገር ያልተባረሩ፤ በዓመት ወይ በስድስት ወር አንዴ ወደ ኢሚግራሽን መሥሪያ ቤት እየፈረሙ በሰላም የመሚኖሩ .. ለእነኚህና ለሌሎች አሁን አሳሳቢ ሁኔታ እየተፈጠረ ነው።” የሚ ጌታቸው በካሊፎኒያ የአሜሪካ የሕግ-ጠበቆች ማኅበር የሳንታክላራ ቫሊ ሊቀመንበር።
“የልብ ትርታ መረበሽ ብዙውን ጊዜ ያንን ያህል ለጤና የሚያሰጋ ነገር የለውም። ምን ሊሆን ይችላል በሚል ግለሰቡን ማሳሰቡ ነው። ነገር ግን ረዘም ላለ ጊዜ ተደጋግሞ ሲመጣ፥ ከእርሱ ጋር ተያይዞም የትንፋሽ ማጠር እና ደረት ላይ ጫና በሚሰማበት ጊዜ ግን ሌላ ክትትል ሊያስፈልገው ይችላል።” ዶ/ር ውብሸት አየነው የልብ ሕክምና ከፍተኛ አማካሪ ሃኪም ናቸው።
“ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን ለመናድ ኦነግና ግንቦት ሰባት ከሚባሉት ድርጅቶች ግንኙነት ፈጥራችሁ ተንቀሳቅሳችኃል የሚል ነው። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መርማሪ ቦርድ የሚባል ኮሚቴ ጎብኝቶን ነበር በአንድ ወቅት። የነበሩትን ችግሮች፤ አዋጁ ግለሰቦችን በቂም በቀል ለማጥቂያነትና አስፈጻሚዎች የአዋጁን መንፈስ ባለመረዳት ጉቦ ለመብያነት ጭምር እንዳዋሉት፤ በተለያዩ አስቂኝ ምክኒያቶች ሳይቀር የገቡ መኖራቸውን ገለጥናላቸው።” አናንያ ሶሪ።
“በዘፈቀደ የመኖር መብትን መቀማትና በፖለቲካ ሳቢያ የተውጠነጠኑ ግድያዎች፤ የገቡበት ያለመታወቅ ወይም ደብዛ መጥፋት፤ ስቃይና እንግልት፤ ሰብዓዊነት የጎደለው የጭካኔ ተግባር፣ እስርና የመሳሰሉትን በመንግስት ኃይሎች የተፈጸሙ የበዙ ጥቃቶችና ሌሎች መብቶች መገፈፍ ይመለከታል።” አርባ አንደኛው የዩናይትድ ስቴትስ ዓመታዊ የአገሮች የሰብዓዊ መብት አያያዝ ግምገማ ሪፖርት።
“የሕጉን መሠረት ሲጥሉ ይሄው እስካሁን ድረስ ከሞላ ጎደል በዚያ ማዕቀፍ ሥር ነው ይሄ ማኅበረሰብ የሚንቀሳቀሰው። ምን ድነው መርሳት የሌለብን ያችኛዋ አሜሪካ በ1789 ሕገ መንግስት የተወለደችውን። ይሄ ኅገ-መንግስት ሲቀረጽ በጊዜው ለማን ነው የተቀረጸው? የሚለውን ነው።” ዶ/ር ብሩክ ኃይሉ የፖለቲካ ሳይንስ መምሕር
"ይህ ሁኔታ ሲከሰት ወቅት የውሃውን መጠን ማጉደል የሚያስችል እርምጃ ወሰድን። በዚያም ጎርፉ በሚያደርሰው መሸርሸር ሳቢያ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ ችለናል።” ቤል ክሮይል የካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት የውሃ ሃብት መምሪያ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ናቸው።
“ይህ ትዕዛዝ ስራ ላይ የዋለው ከውጭ ጉዳይ፥ ከመከላከያ፥ ከፍርድና ከአገር ደህንነት ሚኒስተር መሥሪያ ቤቶች ጋር በቂ ወይም ምንም ዓይነት ምክክር ሳይደረግ ነው የሚሉት ሪፖርቶች በተለይ አሳስበውናል። እንዲህ ያለው ችኮላ ውጤቱ ጎጂ ሊሆን ይችላል። በአውሮፕላን ጣቢያዎች የተፈጠረው ትርምስ ትዕዛዙ በሚገባ ያልተጠና መሆኑን ያመለክታል።” የዩናይትድ ስቴትስ የመወሰኛ ምክር ቤት የሪፐሊካን ፓርቲ አንጋፋ አባላት ሴኔተር ጆን መኬይናና ሴኔተር ሊንዚግራሃም “ደካማ የኢሚግሬሽን አቁዋም ነው ያላችሁ። ይልቁንስ የእስልምና መንግስት ቡድን ሕገ-ወጥ ኢሚጊሬሽንን እና የድንበር ጸጥታ ላይ ብታተኩሩስ?” ፕሬዝዳንት ትራምፕ
“የሥልጣን ክፍፍል ያለው ሥልጣን በሙሉ በአንድ ሠው ወይም አካል መከማት እንደሌለበትና (ግለሰብም ሆነ ፓርቲ ሊሆን ይችላል) ለመቆጣጠር ሚዛናዊ በሆነ ሁኔታ ለሦሥቱ የመንግሥት አካላት ተመጣጣኝ የሆነ ሥልጣን በመስጠት ሚዛኑን ለመጠበቅ የታለመ ነው። ከግለሰቦች ጠባይ አስተዳደር የመጣ ነው።” ዶ/ር ብሩክ ኃይሉ በኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምሕር
“በሀገር አቀፍ ፈረጃ የኢትዮጵያን የጤና አቅርቦት ሥርዓት ለማሻሻል የተወጠነ የተሃድሶ ዕቅድ በመምራትና በመርዳት አገልግያለሁ። ... ውጤትም አግኝቻለሁ። በዓለም አቀፍ ደረጃም ዋና ዋና የሚባሉትን ዓለም አቀፍ የጤና አገልግሎት ተቋማት በቦርድ ሰብሳቢነት አገልግያለሁ።” - የቀድሞው የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ
“በደማችን ውስጥ የሚገኝ የስኳር መጠን .. አመጋገባችን፥ የሰውነታችን ክብደት መጨመር እና የአካል እንቅስቃሴ መኖር ወይም ያለመኖር፤ ያኔ ‘የስኳር ሕመም ያዘኝ’ የሚባለው አባባል ይመጣል።” ዶ/ር ኤልያስ ሰይድ ሲራጅ የሥኳር ሕሙማን ክትትል ባለ ሞያ።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ ባን ኪ-ሙን በያዝነው የአውሮፓዊያን ወር - ዲሴምበር መጨረሻ ላይ መንበራቸውን ለተተኪያቸው ያስረክባሉ።
“ይህ የኢትዮጵያ መንግሥት ይበልጥ አምባገነናዊ ወደሆነ አስተዳደር እያመራ ያለበትን አዝማሚያ የሚጠቁም ሌላ አዋኪ ምልክት ነው። ውስብስቡን ውስጣዊ የፖለቲካና የክልል አወቃቀር፤ እንዲሁም ከባድ ሊሰኙ የሚችሉትን ታሪካዊ ገጠመኞቻቸውን እገነዘባለሁ። ይሁንና መንግሥቱ በቅርቡ የወሰዳቸው የኃይል እርምጃዎች ግን ዘለቄታ ላለው ዲሞክራሲ ተጨባጭ አደጋዎች ናቸው።” ሴናተር ክሪስ ኩንስ በየዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የውጭ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ አባል።
ተጨማሪ ይጫኑ