“ለሃገሩ ራሱን የሰጠ ወታደር እንጂ ለቡድን የሚሰጥ መሆን የለበትም። ፖለቲካ ሌላ ነው ወታደር ሌላ ነው። በግልጽ መለየት አለባቸው። ይሄ ሁኔታ ነው ለሃገርም የሚጠቅመው። ነገር ግን ከፖለቲካ ጋር ወታደሩ ወዲህ ወዲያ የሚሄድ ከሆነ የሃገር ጥበቃ ትክክል አይመጣም።የጃንሆይም የደርግም ወታደር አልነበርኩም አሁንም ከዚህኛውም ጋርም ግንኙነት የለኝም።” ብርጋዲየር ጀነራል አሸናፊ ገብረ-ጻድቅ ከዘንድሮው “የጀግኖች ቀን” ተሸላሚዎች አንዱ።
“የ2017ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በሕገ መንግስቱና በጽሁፍ በተቀመጡ የአገሪቱ የምርጫ ሕጎች ድንጋጌ መሠረት ያለመካሄዱን ነው ያጤንነው። ግልጽም፣ በማረጋገጫ ሊደገፍ የቻለም አይደለም። በዚህ የሕጉ አግባብ እና በምርጫ ሕጉ አንቀጽ 83 የሕግ ትርጓሜ ብቻ እንኳን የምርጫውን ውጤት ውድቅ ከማድረግ የተለየ አማራጭ አልነበረንም።” ፊሎሜና ምዊሉ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ውጤት ‘ውድቅ ይደረግ’ ሲሉ፤ ውሳኔ ካሳለፉት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች አንዷ ናቸው።
“ኢትዮጵያ በየጊዜው ከፍተኛ መጠን ያለው እርዳታ ከካናዳ መንግስትና ሕዝብ ታገኛለች። በቅድሚያ ያ እርዳታ በረሃብ አለንጋ ለሚገረፉት ለእነኚያ ለታሰበላቸው ተረጂዎች መድረሱንና የሰዎች መብት መጠበቁን ማረጋገጥ እንሻለን። በእርግጥ የምናየው የሰብዓዊ መብት ረገጣ ግን በተዘዋዋሪም ቢሆን ያን ዓይነት አመኔታ እንድናሳድር የሚያግዝ አይደለም።” ለኢትዮጵያው ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ግልጽ ደብዳቤ የጻፉት የካናዳ ፓርላማ አባል አሌክስ ናዳል።
“በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እየተወሰደ ያለው ጥቃት ይቁም። ግድያዎቹ በገለልተኛ ወገን ይጣሩ።” ኢትዮጵያውያኑ ለዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እና ምክር ቤቶች ያስገቡት ደብዳቤ።
“የኢትዮጵያ ሕዝብ (በተራ ሕዝብነት የምንመለከተው) ብዙ ዕውቀትና አስተዋይነት ያለው ነው። ከእነሱ ብዙ ተምሬያለሁ። ደግሞም ስለነሱም ነው ከበሬታ ያለኝ። በኢትዮጵያዊነት፤ ፈሪሃ እግዚአብሔር፥ እንግዳ ተቀባይነት ለሌላው ማሰብ፥ ሲታመም ሄዶ መጠየቅ፤ ይሄ ይሄንን ሳይ ይነካኛል።”ዶ/ር አያሌው ገብረስላሴ የትምሕርት ባለሞያ።
“የይሁዳ ከንፈር” ትሰኛለች፤ የሳምንቷ ምርጥ ግጥም በወጣቷ ገጣሚ ትዕግስት ዓለምነህ ናት።
“እዚህ በዩናይትድ ስቴትስ የምንኖር ሰዎች እንደ ብዛታችን እንደ ቁጥራችን ሃሳብ የምንለዋወጥባቸው መድረኮች ለምንድነው የሌሉን በሚል በማዘጋጀው የቴሌቭዥን ከምጋብዛቸው እንግዶች ጋር ዘወትር የምናነሳቸው ጥያቄዎች ናቸው መነሻ የሆኑን” ሄለን መስፍን የፕሮግራሙ አዘጋጅ።
“ጥሩ ትምሕርት ልዩ ልዩ የአኗኗር መመሪያዎችን፤ ለምሳሌ ሕግን ስለማክበር፤ በሕግ ስለመተዳደር መማርን ሲጨምር ነው። ገንጥለን ግን ሂሳብን፤ ሳይንስን ብቻ በመማር የኑሮ እድላችንን እናሻሻል ይሆናል እንጂ ከዚያ ወደ ሰብዓዊ ችግር ወደ ሰብዓዊነት ሲወስድ ግን ብዙ አልታየም።” ዶ/ር አያሌው ገብረስላሴ የትምሕርት ባለሞያ።
"በኢራን የባሃይ፥ የክርስትና እና ሌሎች ሕዳጣን ማኅበረሰቦች በዕምነታቸው ሳቢያ ይሳደዳሉ። ኢራን ዕምነትን በመጣል በሚለው የተድበሰበሰ ሕጓ አማካኝነት በዜጎች ላይ የሞት ቅጣት መበየኗን ቀጥላለች።
በቅርቡ በመንግሥት የተጣለውን ግብር ግምት ተከትሎ ሰሞኑን በተለያዩ በአማራ ክልል በሚገኙ ከተሞች በራቸውን በመዝጋት ተቃውሟቸውን ሲገልፁ ከሰነበቱት የንግድ ድርጅቶች አንዳንዶቹ አሁንም በቅዋሜው መቀጠላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ።
በአሁኑ ሰዓት በተለይ በግብር አተማመን የተነሳ በጣም ከፍተኛ የሆነ ሕዝባዊ ቅሬታ በሁሉም ቦታዎች አለ።
በባሕር ዳር ከተማ በዛሬው ዕለት በቤት ውስጥ የመዋል አድማ ተደርጎ ዋለ።
“ክርክሩ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን መነጋገሪያ መድረክ የት ነው? እያንዳንዱ ሰው ከራሱ መንገድ ነው የሚጽፈው። በታሪክ ሞያ ውስጥ ይሄን ምንድን ነው የምንለው? መርጦ ማስታወስ እና መርጦ መርሳት። የተወሰኑ ነገሮች ተመርጠው ይታወሳሉ። ተመርጠውም ይረሳሉ። ታዲያ እነኚህ ጨርሶ እውነታ የላቸውም ማለት አይደለም። ነገር ግን ጎዶሎ እውነታዎች ነው የሚሆኑት። የራስን ፍላጎት ለማስፈጸም ነው የሚውሉት።” ዶ/ር ሽመልስ ቦንሳ።
“ማወቅ የምፈልገው፤ “ማ” ስለ ከትላንት ውስጥ “ምንን” ወይም የትኛውን ክፍል ጠቅሶ ዛሬ ላይ ምን ዓይነት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሥርዓት መገንባት ይፈልጋል? ወይም እየገነባ ነው? ምን ዓይነት የአገዛዝ ሥርዓት እንዲቀጥል ይፈልጋል? .. ነገ ምን ዓይነት ሥርዓት እንዲመጣ በመናፈቅ ነው? የሚለው ነው።” ሱራፌል ወንድሙ።
ከተማሪ መምህር እና የጥበብ ሰው ጋር የተያዘ ወግ! አሉላ ከበደ እና ሱራፌል ወንድሙ (ፀሐፊ ተውኔት፣ ዳይሬክተር እና ገጣሚ )
ሰንሰለት ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ የድራማው ደራሲና ዳይሬክተር ተመስገን አፈወርቅ እና ሌላው የፊልሙ ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ለገሰ ከአሜሪካ ድምፁ አሉላ ከበደ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ። ቪዲዮ ኤዲቲንግ አበባየሁ ገበያው
"የተለያዩ ታሪኮች ተሰናስለው አንድ ቦይ ውስጥ የሚፈሱበት መንገድ ነው። ኢትዮጵያና እዚህ ያለውን ሕብረተሰብ በአንድ ታሪክ ውስጥ እየገመደ የሚራመድ ረዥም ፊልም ነው።" - ተመስገን አፈወርቅ የተከታታይ ፊልሙ ደራሲና ከዳይሬክተሮቹ አንዱ።
ከፈረንሳይ በስተቀር አብዛኞቹ የአውሮፓ ጦር ኃይሎች ለየትኛውም ወታደራዊ ጣልቃ ገብ ሥራ የተሰናዱ አይደሉም።
የፕሬስ ነጻነት እና ጋዜጠኝነት በኢትዮጵያ እሰጥ አገባ ትኩረት ያደረገበት የተከታታይ ክርክር ጭብጥ ነው።
ተጨማሪ ይጫኑ