"ከስምንታችን መሃከል አንድ እርሡ ወንድሜ ብቻ ነው የታሰረው። እንደሚመስለኝ ወንድሜ ተዋጊ ወታደር መስሏቸው ይሆናል። ነገር ግን እርሱ ተዋጊ ወታደር አይደለም።" ግሬስ ገበ ቁጥሩ 30 ሺህ የሚደርስ ስደተኛ በማስተናገድ ላይ በምትገኘው የድንበር ከተማ አባ ከተጠለሉ ደቡብ ሱዳናውያን አንዷ።
ዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲዋን ወደ እየሩሳሌም የማዛወር ዕቅዷን ይፋ ማድረግ ተከትሎ ከተቀሰቀሰው ቀውስና ግጭት ጋር በተያያዘ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን መታሰራቸው ተዘገበ።
የሳምንቱ የእረፍት ጊዜ የእሁድ ምሽት የቁም ነገርና መዝናኛ ምርጫችሁ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ።
ዛሬ ዕለቱ ከቀያቸው ተፈናቅለው፤ በዓለም ዙሪያ የተበተኑ ሚሊዮኖች የሚታሰቡበት ነው።
“.. ከዚህ በኋላ ከክላሽ ወደ ካርድ እንቀይረው የሥርዓት መለወጫ መንገዳችንን።” አቶ የሺ ዋስ አሰፋ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር። “ችግሩን መዘርዘር ብቻ ሳይሆን፣ መፍትሔውስ ምን መሆን አለበት? የሚለው ጥያቄ ነው ዋናው ነገር።” አቶ ግደይ ዘርዓ-ጽዮን የኢትጵያ ሕዝብ ብሔራዊ ሸንጎ ጸሃፊ። “የመጀመሪያው ድርድር ሆነ፥ ምን ሆነ፣ መዳረሻው ምንድ ነው? ነው፤ መጀመሪያ ምን ለማድረግ ነው የምንፈልገው?” ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች-ግንቦት 7 ሊቀመንበር
የሁለት ባሕሎች ውበትና ፈተና በአንድ ተጋምዶ ከሲኒማው ማሳያው ስክሪን የሚታይበት ፊልም ነው። 'Woven' ይሰኛል። ኢትዮጵያውያንና አሜሪካውያን ተዋናዮች እና የፊልም ሠሪዎች ተሳትፈውበታል።
“ይሄንን ነገር በፖለቲካ መልክ ማየት አንችልም። ለዚህ ችግር መፍትሔ የሚያመጣው ችግሩን የፈጠረው ሕወአት ነው።” ፕሮፌሰር ዳንኤል ተፈራ። “ሕወአት በዚህ ላይ መፍትሔ ሊያመጣ አይችልም። ኢሕአዲግ ውስጥ ያለውም አመራር ቢሆን እየደከመ ከመሄዱ ጋር በተያያዘ፤ ያን የሚመጣጠን ሚና እንዲቀበል ነው ግፊት መደረግ ያለበት።” አቶ ያሬድ ጥበቡ።
“በመሠረቱ እነኚህ ኢትዮጵያውያን ለምን ይሄን ለማድረግ ተነሳሱ የሚለው ዓላማቸው ነው መታየት ያለበት። ... የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረት ለመሳብ፤ በሕዝብ ዘንድ ትኩረት ለመሳብ የሚደረግ የተለመደ አሰራር ነው።” አቶ ከባዱ በላቸው።
“አገር ቤት እየተደረገ ባለው ጭቆና ብዙ ወገኖቻችን እየታሰሩ ባሉበት እኛም እዚህ ተካፋይ መሆናችንን ለማሳየት ሆን ብሎ ያደረገው ነው።” የዋሽንግተን ዲሲ “የጋራ ግብረ-ኃይል” ከአስተባባሪዎቹ አንዱ።
“የሰላሳ ሁለት ዓመቱ ልዑል አልጋ ወራሽ ቢን ሳልማን እየወሰዳቸው ያሉት እርምጃዎች አንዳንዶች የአገሪቱን መሠረታዊ የኢኮኖሚና የማሕበራዊ ሕይወት ለመለወጥ የታሰበ እርምጃ አካል አድርገው ሲወስዱት ሌሎች ደግሞ ስልጣንን ጠቅልሎ ለመያዝ የሚያደርገው አድርገው ይመለከቱታል።” ዶ/ር ሽመልስ ቦንሳ የታሪክና ፖለቲካ መምሕር። “የቀድሞዎቹ የሳውዲ አረቢያ መሪዎች እያረጁ ነው። አዲሶቹ ደግሞ ሥልጣን እየፈለጉ ነው። ከዚያ አልፎ ግን የሳውዲ አረቢያን ንጉሳዊ አገዛዝ ይቀይራል ብሎ መጠበቅ አይቻልም። ሌላው በየመን የያዙት ጦርነትና የተፈጠረው ውጥረት አለ። ይሄ በጣም አስጊ ነው።” ዶ/ር ዳንኤል ተፈራ በዊስኮንሰን ዩኒቨርሲቲ ዋይት ዋተርስ የምጣኔ ሃብት ኢሜሪተስ ፕሮፌሰር።
“bio-psycho social model ይሉታል። በተፈጥሮ በዘር የሚተላለፍ፣ ስነ ልቦናዊው እና ማሕበራዊ ይዘት ያለውም አለ። አንዳንድ ጊዜ ቤተሰብ ውስጥም ይሁን ጎረቤት ያንን ልጅ ክፉኛ እያዋከበ፥ ክብሩን እየናቀና እያዋረደና እያጥላላ የሚያድግበት ሁኔታ የሚፈጥር አዝማሚያ ወደማመጽና በሕብረተሰብ ላይ ከፍተኛ ቁርሾ ወደመያዝና ብሎም ሲብላላ ኖሮ ንጹሃንን በግፍ በማሰቃየት ወደሚደሰት ሥብዕና ሊያመራ ይችላል።” ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ ገዳ ልብ የነርቭና የአዕምሮ ሃኪም።
“በደርግ አባልነቴ ሰለባ ለሆኑት ሰዎች፥ በእነርሱም አማካኝነት ለመላው ኢትዮጵያውያን ተንበርክኬ ይቅርታ እጠይቃለሁ።” አቶ እሸቱ ዓለሙ። “አቶ እሸቱ፥ ዛሬም ‘ይህን በደል ፈጽሜያለሁ’ ሲሉ ወንጀሉን አላመኑም። በጸጸትም የተዋጡ ሰው አይደሉም።” አቶ ዓለሙ ጥሩነህ በጊዜው በእስር ቤት እንግልት ከደረሰባቸውና ከሞት የተረፉ ከዛሬው ሰባት ምሥክሮች አንዱ።
ውጥረት በነገሰበትና ግጭቶች ባየሉበት የፖለቲካ ምህዳር፥ የመገናኛ ብዙኋን ሚና፥ ኃላፊነት፥ ፈተና እና ለማሕበረሰብ ሁነኛ ፋይዳ ያላቸው ሥራዎች የመሥራት እድል። የመደበኛ መገናኛ ብዙኃንና ሌሎች የሚዲያ አውታሮች፤ ከታዋቂ የኢንተርኔት አምዶች እስከ አካባቢ ራዲዮኖችና ጋዜጦች፤ ብሎም የማሕበረሰብ መገናኛ ብዙኋን የተለያዩ ገጽታዎች የሚቃኝ ተከታታይ ውይይት ነው።
“የያዛችሁት የተሳሳተ ሰው ነው። “የእኔ ድርሻ የፕሮፖጋንዳ ሥራ ብቻ ነበር።” አቶ እሸቱ ዓለሙ። “ወንድሜና ሌሎች በጊዜው ታስረው የነበሩት ወጣቶች እንዲገደሉ ትዕዛዝ የሰጡት አቶ እሸቱ ስለመሆናቸው በፊርማቸው ያዘዙበትን ጨምሮ ብዙ ማስረጃ ተገኝቷል።” አቶ አብረሃም ብዙነህ ከከሳሽ አቃቤ ሕግ ምሥክሮች አንዱ።
“በገዢው ፓርቲ በኩል የሚሰሩትን ሥራዎች እንደ ጥሩ ነገር አይቼ ተቃዋሚው ላይ ግን ባለፉት ሁለት ዓመታት ከቆመበት የአክቲቪስት ፖለቲካ ወጥቶ፤ ማንኛውንም ብሶቶች በማራገብ ሰልፍ ግን ግብ አይደለም።” አቶ ኤልያስ ግደይ ከአዲስ አበባ። “የኢትዮጵያ ሕዝብ በያለበት ቦታ እያለ ያለው የምንፈልገው ነጻነት ነው። ስለዚህ ውስጥ ያለው መነሳሳት የሃያ ስድስት ዓመታት አገዛኣዝ አብቅቶ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መመሥረት ይችላል ነው።” አቶ ግዛው ለገሰ ከዋሽንግተን ዲሲ።
በሶል እና በዋሽንግተን መካከል ያለው የኒውክሌር ፍጥጫ እያደር እያየለ በመጣበት ባሁኑ ወቅት፤ ለሠላማዊ መፍትሔ ያለው ተስፋ እየተመናመነ እና ወታደራዊ ግጭት የመከተሉ አደጋ በአንጻሩ መሆኑን የሰሜን ኮሪያ ጉዳይ አጥኚዎች እየተናገሩ ነው ።
“ግራ ቀኙን ያለውን ሁኔታ ስከታተለው ነበር። አሁን አገሪቱ የጭንቅ አማላጅ የምትፈልግበት ሰዓት ነው። በፖለቲካውም ጎራ ከዚህ ቀደም ያልተለመዱ ሁኔታዎች እያየን ነው።” ዲያቆን ዳንኤል ክብረት። “ኢትዮጵያ በጣም ፈታች ሁኔታ ላይ እንዳለች ይሰማኛል። የአለቃ አያሌውን ግግግር ተውሼ፣ መልህቋን የምትጥልበት አጥታ ማዕበል ከወዲህ ወዲያ በሚያላጋት በውል ለመለየት ከሚቸግር አደገኛ ሁኔታ ላይ እንዳለች ይሰማኛል።” አቶ ሃብታሙ አያሌው።
ተጨማሪ ይጫኑ