“ተጠያቂነትን አልተማርንም። ለሞቱት ሰዎች የተጠየቀ ሰው የለም። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲህ ያሉት የጭፍን አሰራሮች ተቁዋሞቻችንን ይገድሏቸዋል።” አቶ የሺዋስ አሰፋ። “ሰው እኮ አንዴት ነው ያለመቀበሉን ሃሳቡን የሚገልጽበት መስመር መኖር አለበት። ሰው በተናገረ ቁጥር እንደ ጠላት ማየት የመንግስትነት አያያዝ ነው ብዬ አላምንም ።” ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግስቱ። “የመንግስት ተቀባይነት በምን ላይ ነው የሚመሰረተው? እነኝህን ችግሮች ፖለቲካዊ ገፅታ በዚህ መንገድ እፈታቸዋለሁ’ ማለት አልቻለም።” አቶ ሙልጌታ አረጋዊ።
አሜሪካዊው ባለ መሲንቆ ቻርልስ ሳተን እና ማርታ ቀጸላ .. ማሚቴ እና ከብዬ ናቸው።
ድምፃዊ ተሾመ ምትኩ በአንድ ወቅት ከቪኦኤ ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ ቆይታ ከድምፃዊ ተሾመ ምትኩ ጋር አሉላ ከበደ፣ አዲሱ አበበ እና ይኄይስ ውሂብ
“የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አገሪቱን ወደባሰ ችግር እየከተታት መሆኑን እያየን ዝም ማለት ስለማንችል ነው ይህን መግለጫ ያወጣነው።” በቀለ ገርባ የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግሬስ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት።
“..በሽብር እንቅስቃሴ ያሉ ቡድኖችንና አካላትን በማቀፍ፣ በማሰልጠንና በማሰማራት ጭምር ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ከፍተኛ ሙከራ አድርጉዋል።” የፈድራል ፖሊስ ኮምሽነር አቶ አሠፋ አብዩ። “አዋጁን ሕጋዊ ለማስመሰል የተሰጠ መግለጫ ነው።”የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ። “ሽብር እየተፈጠረ ያለው በመንግስት በራሱ ነው። ሥራቸውን በሚያጋልጡ የመገናኛ ብዙኃንም ሆነ የማሕበራዊ መገናኛ ብዙኃን የሚቀርቡት መረጃዎች አይደለም።” አቶ ነዓምን ዘለቀ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ።
“የኤርትራ መንግስት ካለፉት ዓመታት ጀምሮ የወጠነው ውጥን አለው፤ ሀገራችንን የማትራመስ። ይሄን ብቻውን ሳይሆን ከአገራችን አብራክ የወጡ የሽብር አካልላትን በማስተባበር ነው።” የፈድራል ፖሊስ ኮምሽነሩ አቶ አሠፋ አብዩ። “የኢትዮጵያ መንግስት ሥር ለሰደደው የውስጥ ችግሩ ሰበብ ፍለጋ ወደ ውጭ ከማየት ይልቅ ሁነኛ መልስ ወደ መስጠቱ ቢያቀና ይሻለዋል።” የኤርትራ የማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረመስቀል።
“የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ ቆስለው ወደ ሆስፒታላችን የመጡና እየታከሙ ያሉ አሥር ሰዎች አይተናል። ሌሎች ቁጥራቸው ዘጠኝ የሚደርስ ሰዎች የሞቱ አይተናል።” የሞያሌ ሆስፒታል ሥራ አሥኪያጅ አቶ አሬሮ ቢቂቻ
“አሳሳቢውን የአገሪቱን ሁኔታ እየተከታተልን ነው። አሁን ላለው ችግር መብትን ይበልጥ መገደብ አይደለም መልሱ።” ሳሊ ሼቲ የአምነስቲ የሥራ አስፈጻሚ ዲሬክተር።
“የአሁኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከቀደመው የሚለየው፤ አሁን ውስጥ የተፈጠረውን ችግር በዋናነት ለመጨፍለቅ ጭምር የታሰበ አርጌ ስለማየው፤ መጭውን በዚህ ሁኔታ ነው የምገነዘበው።” ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና “በስልጣን ላይ (ሳለ) ሰው ሲታሰር የማውቀው እርሳቸውን ነው። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከስልጣን መልቀቃቸውን የማየው ሌሎች ከእስር እንደተፈቱት ነው .. የችግሩ ሰበብም አይመስሉኝም። በመልቀቃቸውም ደግሞ ችግሮቹ ይቃለላሉ ብዬ ለማሰብ እቸገራለሁ።” ቴዎድሮስ ጸጋዬ
“የኮማንድ ፖስት ያዘዘው ነው፣ አስተዳደሩ ሥራ ላይ ያዋለው። ከዓዋጁ ጋር አይሄድም። በመሆኑም ለሌላ ጊዜ ሁኔታዎችን አመቻችተን እንቀበላቸዋለን፤ ለአሁኑ ይመለሱ ነው የተባለው።” - አቶ ሞገስ ኤዴኤ የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ
"አሁን ከተፈቱት ይልቅ እስር ላይ ያሉት ቁጥር በጣም ይበልጣሉ። በርካቶች ናቸው። አገር ውስጥ ያለው ሜዲያ መንግስት ሲፈቅድ ሰው ከተፈታ በኋላ ነው የሚያውቃቸው። አብዛኞቹም እስካሁን በእስር ላይ ሳሉ የደረሰባቸውን በደል እና ሰቆቃ አንድም ቀን ሳይገልጹ አሁን ሲፈቱ ነው፤ ለዜና ግብዓት ብቻ የሚያናገሩት።" ጌታቸው ሽፈራው የቀድሞዋ ነገረ-ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዘጋቢ።
የካቲት 12 ቀን፣ የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን ዛሬ እንደ ኢትዮጵያው ሁሉ በዓለም ዙሪያ በተለያዩ አገሮች በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድም በመታሰብ ላይ ነው።
"ሜነሶታ ውስጥ ስብሰባ ከማድረጋችን በፊት የክልሉ አስተዳዳር በዚያ ወደሚገኙ የቤተሰቦቻቸው አባላት ሄደው ለልጆቻችሁ ደውላችሁ በስብሰባው እንዳይሳተፉ ንገሯቸው። ካልሆነ ግን እስር ቤት እንደምትገቡ፤ ቤትና ንብረታችሁን እንደምታጡ ንገሯቸው ብለው አስጠነቀቋቸው። እነርሱ ግን እሺ አላሉም። ከዚህ በፊት አድርጋችሁ ታውቁ የለ፤ የምታደርጉትን አድርጉ፤ አሏቸው። ከዚያም የአሥራ ሁለት ዓመት ልጆች ሳይቀሩ ብዙ ሰዎች ታሰሩ።"
“የዚህ ሕግ ማለፍ መጽደቅ ለጉዳዩ ባለቤቶች ለኢትዮጵያውያን ምን ማለት ነው? የሚለው እና ባሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ የእየተካሄደ ያውን፣ በሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ሥቃይ ለማሳየት ይህንን ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ወደ ድምጽ አሰጣጥ በአስቸኳይ እንዲሄድ ግፊት ለማድረግ ነው።” አምሳሉ ካሳው የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ግብረ-ኃይል ቃል አቀባይ።
“ዩናይትድ ስቴትስ በክልሉ ላላት በብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ላተኮረ ግንኙነቷ ቅድሚያ በመስጠት ለረዥም ጊዜ በኢትዮጵያ መንግስት የሚፈጽሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አይታ እንዳላየች ስታደርግ ቆይታለች። ያ ፍጹም የተሳሳተ ነገር ነው። በመሆኑም ይሄ ያን ስህተት የማመን የመጀመሪያ እርምጃ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት በገዛ ዜጎቹ ላይ የሚፈጽመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም።” ኮንግሬስማን ማይክል ሃዋርድ ኮፍማን የUS የተወካዮች ምክር ቤት አባል።
"በክልሉ አምባገነንነት ሰፍኗል፣ ሥጋት ነግሷል። ወጣቶች ከዚያ ለመቆየት የሚያስችል ተሥፋ በማጣታቸው በአደጋ ለተመላ ስደት ተዳርገዋል። መልስ ያልተገኘላቸው ብዙ ጥያቄዎች አሉን።" ዑመር ዶል የድርጅቱ ሊቀመንበር ናቸው።
“እነኚያ ሬሲ ቴይለር’ን ሊያጠፉ የሞከሩ ሰዎች በሕግ ሳይጠየቁ ቀርተዋል። ሬሲ ቴይለር ዘጠና ስምንተኛውን የልደት በዓሏን ለማክበር ጥቂት ሲቀራት ከአሥር ቀናት በፊት ነው ያረፈችው። አይደፈሬ ነገር ግን ርሕራሄ በሌላቸው ወንዶች በተደፈረ ባሕል ውስጥ አያሌ ዓመታት ኖራ አለፈች። በእነኚያ አይጠየቄ ወንዶች የደረሰባቸውን ጥቃት ለመናገር የደፈሩ ቁጥራቸው የበዛ ሴቶችም ሰሚ ሳይኖራቸው ለረዥም ዘመናት ዘለቁ። ዛሬ ግን ያ ሰዓት ያበቃ ይመስላል።” ኦፕራ ዊንፍሬ።
"ፕሮፌሰር እደማሪያም በግል ጥረታቸው የድሕረ ምረቃ የሕክምና ትምሕርት ፕሮግራሞች እንዲከፈት ያደረጉ ናቸው።" ከቀድሞ ተማሪዎቻቸው አንዱ ፕሮፌሰር ጌታቸው አደራዬ። “ለሕመምተኛና ለተማሪ ከፍ ያለ ክብር የሚሰጥ፤ ጥሩ ተማሪ የሚያፈራና ከእርሱ የተሻሉ እንዲሆኑ የሚያደርግ፤ ተማሪ ሆነን 'ተሳስተሃል' ብለን ደፍረን እንድናገረው የሚያበረታታን ፕሮፌሰር፤ ለሞያው የረቀቀ ክብር ያለው ‘ሃኪም’ የሚለው መጠሪያ ለእርሱ የተጻፈ የሚመስል ባለሞያ ነበር።” ዶ/ር አሰፋ ጄጃው።
“ለመቀራረብ የሚረዱት ነገሮች በአገዛዙ እጅ ነው ያሉት። አንደኛ የመወያያ መስመሮችን በሙሉ ነጻነት እንዲኖሩ ማድረግ። ሁለተኛ ምንም ተጨባጭ ወንጀል ሳይኖርባቸው፤ በፖለቲካ ምክንያት ሃሳባቸውን በነጻ በመግለጻቸው ብቻ የታሰሩ ሰዎችን መልቀቅ። እነኚህ ለዜጎች በሙሉ እንደ አዲስ እንድንጀምር፤ ቂምንና ጥላቻን እንድንሰርዝ ይረዱናል። በእነኚህ በትንንሽ ነገሮች ብንጀምር ጥሩ ነው እላለሁ።” ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም
ተጨማሪ ይጫኑ