የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ መፍትሔ ታጥቶለት ሳይገኝለት ዓመታት ለዘለቀው የሁለቱ ሀገሮች የድንበር ውዝግብ ሁነኛ መፍትኄ ተስፋ ባንሰራራ በተባለ ውሳኔያቸው አንድ የልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ ሊልኩ ማቀዳቸውን ይፋ አደረጉ።
"ኢህአዴግ እንደ ድርጅት አራቱ ድርጅቶች የራሳቸውን ድርሻ በመንግስት የሥራ ኃላፊነት ላይ አስቀምጠው ተግባብተው ወጥተዋል።.. ለኢህአዴግ ተገዥ እንሁን ነው በአጭሩ።" አቶ አሉላ ሰለሞን በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ማሕበር ዳይሬክተር። ይሄ መግለጫ ወዲያ ወዲህ መያዝ አያስፈልገውም። በጠቅላይ ሚንስትሩ ላይ የተደረገ ተግሳጽ፤ ከፍ ካለ ደግሞ እንደ ዛቻ ነው መታየት ያለበት።” አቶ ጀዋርን ማሃመድ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ዳይሬክተር።
የአሥራ ሰባት ቀን ስብሰባ ነበር። አሥራ ሰባት መጻህፍት ተሰጥተውን ነበር። .. አስራ ሰባት ቀን በሙሉ እንዴት እንዴት ሊሆን ይችላል በሚል .. ፍርሃቱም ቢኖር .. ምን እንደምልም በደንብ ሳላብላላው በበስጭት ብቻ ለጥያቄ እጄን አነሳሁ። ” ዶ/ር አንማው አንተነህ።
“..አጠቃላይ የፖለቲካ መንፈሱን ለመቀየር .. ሁላችንንም በሰለጠነ መንገድ እየተነጋገርን ወደምንሄድበት የፖለቲካ ሂደት ለመክተት መጀመሪያ መቀየር ያለበት ይሄ ከእልህና ከቁጭት የወጣ መንፈስ ነው።..” ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች ግንቦት ሰባቱ ሊቀ መንበር። "በአገራችን ያለንመሸማቀቅ ፖለቲካ እንድናራምድ፣ የአገርነት ስሜቱም እንዲኖረን አንድ እርምጃ ስለሆነ፤ እስረኞችን የመፍታቱን ሂደት እደግፈዋለው። ኢሐዴግ ሁለት ፓርቲ ነው፣ ሦሥት፣ አራት ወይም አንድ? አይገባኝም። የአረና እስረኞች እስካሁን አልተፈቱም። በዚህ አዝናለሁ።” አቶ ገብሩ አሥራት፤ የአረና ትግራይ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል።
“.. አሁን ያለው ነፋስ .. ከአርባ ዓመታት በኋላ ሥለ ፍቅር፣ ሥለ አንድነት፣ ሥለ ፈሪሃ እግዜብሔር፣ ሥለ ሰላም፣ ሥለ አብሮ መኖር መሆኑ በጣም ነው ደስ ያለኝ።.. ‘ጸረ’ የለም። ሲያደክሙን የቆዩት ይህን የመሳሰሉ ነገሮች መቅረታቸው ያስደስታል። ..” ልዑል በዕደማሪያም ሳህለሥላሴ ኃይለሥላሴ።
“.. በአንድ በኩል ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ከባሕር ማዶ በአካል ብኖርም በመንፈሴ በሕልሜና በመንፈሴ ግን ሁሌም አገሬ ውስጥ መሆኔን .. ብዙ ዓመት የነበርኩበት የሰሜን ተራሮች፤ የትጥቅ ትግል የሚያሳዩ ስዕሎች አሉ። .. ያደግኩብትን ሠፈሬን አራዳን፣ የጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እና የአጼ ሚኒሊክ ሃውልትየሚያሳዩ ስዕሎች ናቸው።” የመጽሃፉ ደራሲ አቶ ያሬድ ጥበቡ።
“..በነጻነት ወደ ፊት ለመገስገስ እና ብሔራዊ አንድነትና ታሪካችንን ለማንጸባረቅ የሚያስችለንን እድል ይፈጥርናል። እናም ዘንድሮ ሙሉ ትኩረታችንን፤ ኢትዮጵያ የሀገር ነጻነትንና አንድነትን፣ እንዲሁም ሰላምን በማስጠበቅ በራስ የመተማመን ልባዊ የኩራት ሥሜት በመላው አሕጉሪቱ እንዲስፋፋ ላደረገችው አስተዋጾ አዘከሪያነት ልናውለው መርጠናል።..” ዶ/ር መና አክሊሉ ደምሴ።
”ታይቶ የማይታወቅ ነገር ነው የሆነው። ታሰረች ከአርባ ደቂቃ በኋላ ተገደለች።”
“ .. አንዴ ብቻ የምናገኛትን ሕይወትን መውደድ ያስፈልጋል። .. ይህን መጽሃፍ መጻፍ የሕይወትን ዋጋ ያጠናሁበት ነው። .. እያንዳንዷ ሰከንድ ብዙ ዋጋ ያላት ነገር ናት። ..”ዶ/ር ዋልተንጉስ ዳርጌ
“የጥናቱ ዓላማ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በትውልድ አገራቸው በሚያኪያሂዷቸው የየግል ፕሮዤዎቻቸው መተባበር የሚቻልባቸውን ዕድሎች ማየት ነው።” Gillian Williams የዓለም አቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት IOM አማካሪ እና የጥናቱ አስተባባሪ።
“በአንድ በኩል ሙሉ በሙሉ ኢሐዲግ፤ በሌላ በኩል ወደ ሥልጣኔ የመጡበት ታሪካዊና ፖለቲካዊ ድባብ ለየት ያሉ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይጠቁማል። ኢሕአዲግን ካየን እስካሁን ለመላዋጥ መፈለጉን አላየሁም።” መስፍን ነጋሽ - ዋዜማ ራዲዮ። “ኢሕአዲግ የፓርቲውና የአገሪቷ መጻኢ ዕድል ተለያይቶ እንዳይታይ ተደርጎ ስለሆነ ፖለቲካው የተሸረበው በፓርቲው ውስጥ የሚፈጠር ኮሽታ ትልቅ ተጽዕኖ ያለው። እዛ ሁነት ውስጥ ሆነን ነው የምንመለከተው።” ጸዳለ ለማ - አዲስ ስታንዳርድ መጽሔት ፍን ነጋሽ። “ግለሰቡ አብይ አሉ። ምናልባትም የኦሮሞ ብሔርተኛው አብይ አለ። የኦሕዲድ መሪ ሆኖ ኢሕአዲግ ውስጥ ባለው ትግል ራሱን አጉልቶ ለማውጣት የሚሞክረው ኢትዮጵያዊው አብይም አለ። .. የገመድ ላይ ጉዞ ነው። በጥሩ ጀምረውታል።” ሄኖክ የማነ - ከስቴት ኦፍ ኒው ዮርክ ዩኒቨርሲቲ።
“በአንድ በኩል ሙሉ በሙሉ ኢሐዲግ፤ በሌላ በኩል ወደ ሥልጣኔ የመጡበት ታሪካዊና ፖለቲካዊ ድባብ ለየት ያሉ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይጠቁማል። ኢሕአዲግን ካየን እስካሁን ለመላዋጥ መፈለጉን አላየሁም።” መስፍን ነጋሽ - ዋዜማ ራዲዮ። “ኢሕአዲግ የፓርቲውና የአገሪቷ መጻኢ ዕድል ተለያይቶ እንዳይታይ ተደርጎ ስለሆነ ፖለቲካው የተሸረበው በፓርቲው ውስጥ የሚፈጠር ኮሽታ ትልቅ ተጽዕኖ ያለው። እዛ ሁነት ውስጥ ሆነን ነው የምንመልለከተው።” ጸዳለ ለማ - አዲስ ስታንዳርድ መጽሔት ፍን ነጋሽ። “ግለሰቡ አብይ አሉ። ምናልባትም የኦሮሞ ብሔርተኛው አብይ አለ። የኦሕዲድ መሪ ሆኖ ኢሕአዲግ ውስጥ ባለው ትግል ራሱን አጉልቶ ለማውጣት የሚሞክረው ኢትዮጵያዊው አብይም አለ። .. የገመድ ላይ ጉዞ ነው። በጥሩ ጀምረውታል።” ሄኖክ የማነ - ከስቴት ኦፍ ኒው ዮርክ ዩኒቨርሲቲ።
“በእኔ ዓይን .. የወደፊቷ ኢትዮጵያችን የፖለቲካ እስረኞች የሌሉባት እንድትሆን ማሰብ ብዙዎች ይስማሙበታል ባይ ነኝ።” ጌብ ሃምዳ (ዶ/ር) “ይሄ መንግስት አዋላጅ መንግስት ከመሆኑ በፊት .. አዋላጅ ባለ ሥልጣናት አንዲመጡ ያስፈልጉታል። ዶ/ር አብይ የመጡበትም ይሄው የአዋላጅ ባለ ሥልጣን አካሄድ ነው።” ዘላለም እሸቴ (ዶ/ር)
“ዶ/ር አብይ እንዲያውም H. Res. 128 ያነበቡ እኮ ነው የሚመስሉት እዛ ላይ። ስለዚህ H. Res. 128 ምንድን ነው? ብሎ አንድ ሰው ድንገት መንገድ ላይ አስቁሞ ቢጠይቀኝ፤ የመልካም አስተዳደር የጀርባ አጥንት ነው፤ ብዬ ነው የምመልሰው።” የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ከትላንት በስቲያ ያፀደቀው።”ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ የኮሎራዶው የኢትዮ-አሜሪካውያን ሲቪክ ምክር ቤት (ካውንስል) ሊቀ መንበር።
“በመጀመሪያ ደረጃ የምክር ቤቱን ተቆርቋሪነት ያሳያል። እና ይሄ ሕገ-ውሳኔ የአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄደው የሰብዓዊ መብት ረገጣ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን፣ የሕዝብን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላው በግዴታ መባረርን፣ እናም የሕግ አልባነትን በመቃወም የወጣ ውሳኔ ነው።” ፍጹም አቻምየለህ ሂደቱን የተከታተሉ እና በዋሽንግተን ዲሲና በአካባቢው በጥብቅና ሥራ የተሰማሩ የሕግ ባለ ሞያ
“የአገሪቱን ውስብስብ ችግሮች ለመፍታት ውሉን መጨበጥ ያስፈልጋል። ለዚህም የሕዝብን አመኔታ ማግኘት ነው። ዶ/ር አብይ ዛሬ ባደረጉት ንግግር .. ተስፋ ሰጪ ነገሮችን ተናግረዋል። በተስፋ ብቻ ሳይሆን ታዲያ በተግባር መጀመር አለባቸው።” ዶ/ር ታዬ ዘገየ የተቃዋሚው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ሸንጎ ፕሬዝዳንት። “አንድ ሃሳብ የበላይነት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ሃሳብ የሚንሸራሸርበት፤ ታቃዋሚ ሳይሆን ተፎካካሪ የምንሆንበት የሚል ዓይነት መሳጭ ንግግሮችን ስለሰማሁ ይህንን ኃላፊነት .. ጊዜው የሚጠይቀውን ፖለቲካ የተረዱት ይመስለኛል።” አቶ ጃዋር መሃመድ የኦሮሞ ሚድያ ኔት-ወርክ ሥራ አስኪያጅ።
“ያ መስመር እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመፍጠር የሚደረግ እንቅስቃሴ መሆኑን ካየን ይን ደግሞ እነ ዶ/ር አብይ በተግባር ማሳየት እስከቻሉ ድረስ፤ እንደዛ ዓይነት በሰላማዊ መንገድ የሚደረግ ሽግግር የሚፈጠርበት ሁኔታ እስካለ ድረስ፤ በምንም መልኩ ይሄንን አዲስ ሥርዓት የማዋለድ ሥራ የማዋልድ ሥራ አብራን ለሥራት ዝግጁዎች ነን።” የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀ መንብር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ “ዶ/ር ብርሃኑም እንዳነሳው ይሄ ፤ኣላፊነታቸው የሚያስቀና አይደለም። ሃገሪቱን ከቀውስ አውጥቶ ወደ አንድነት እና ቀና የሆነ መንገድ ማስያዝ በጣም ትልቅ ትዕግስት የሚጠይቅ ትልቅ መተባበርን የሚጠይቅ ስለሆነ የሚጠበቅብንን ኃላፊነት ዝግጁ መሆናችንን በመግለጫው ውስጥ አካተናል።” የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ሀሰን ሁሴን
“የሚጠብቃቸው ፈታኝና አስቸጋሪ ሁኔታ ነው። የሕዝብን አመኔታ ለማግኘትም የመጀመሪያ ሊደርጉት የሚገባው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚነሳበትን መንገድ እና …” የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግሬስ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ፤ “አጠቃላይ ችግሮቹን እየፈጠረ ያለው እንደ ድርጅት ራሱ ኢሕአዴግ ስለሆነ ድርጅቱ ራሱ መለውጥ አለበት። ነገር ግን አንድ ሰው ለለውጥ ዝግጁ ከሆነ፣ ቁርጠኝነት ካለው፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለአገረ ኢትዮጵያ የሚያስብ መሪ ከሆነ የፖለቲክካ ቀውሱን የመፍታት ዕድል አለው።…” የአረና ትግራይ ሊቀ መንበር አቶ አብረሃ ደስታ “የዚህ ሁሉ መሰረቱ ለአገዛዝ እምቢ ያለ ሕዝባ መፈጠሩ ነው። .. ከአገዛዝ ወደ ዲሞክራሲ የተሸጋገሩ አገሮች ብዙ አገሮች አሉ። .. በእዚህ መንገድ እንሻገረዋለን አማራጮቹን ማሳየት፡ ዋናው አስፈላጊ ጉዳይ ነው።” የሰማያዊ ሊቀ-መንበር አቶ የሺ ዋስ አሰፋ
ተጨማሪ ይጫኑ