በፕሬዚዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ ሥያሜ አንድምታ፣ በሃገሪቱ ፓርላማ አሠራርና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ዙሪያ የሚያጠነጥን ውይይት ነው።
“የመዋዕለ ንዋይ ፍሰቱ እንዳይቋረጥ” ሲሉ አንዳንድ የምክር ቤት አባላት አሳስበውኛል። ያ ማለት ግን፤ ጉዳዩን በሚመለከት ምንም አያደርጉም ማለት አይደለም። ለወንጀሉ ተጠያቂ የሚያደርግ .. ምንም ይሁን ምን .. የሆነ ቅጣት መኖር አለበት።
አዲስ አበባ ላይ በተካሄደው የአሜሪካ ድምጽ የጋዜጠኞች ስልጠና መገባደጂያ ከባልደረቦቻችን ጋር ያደረግነው ቆይታ ነው።
“ሴቶች በነበረው ነውጥ ውስጥ ሀገር ተረጋግታ እንድትራመድ አስተዋፅዖ ያበረከቱ በንፅፅር በሌብነት ባነሰ ደረጃ የሚታሙ ናቸውና” ጠ/ሚ አብይ አሕመድ። “በሴቶቻችን ዕምነት ሊኖረን ይገባል። አጋጣሚ ሆኖ በታሪካችን ብዙ ትልልቅ ሥፍራ ሳያገኙ ቀርቷል። የወንድ ተፅዕኖና የወንድ ዓለም አንደመሆኑ።” የአፍሪካ ኢንሽዪቲቭ ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር አቶ ክቡር ገና።
እንደታጠቁ ወደ ቤተ መንግሥት ያቀኑት ወታደሮች ጉዳይ እና የጠቅላይ ሚንስትሩ ምላሽ።
“.. የመሪዎች ብቃት የሚለካው ይበልጡን በቀውስ ውስጥ በሚያሳዩት የመሪነት ችሎታ ነው። .. የአብረሃም ሊንከን ዘመን የሃገር አንድነት ጥያቄ ላይ የወደቀበት ጊዜ ነበር .. አሜሪካን ከጥፋት ያዳናት ብቃት ካላቸው ተቀናቃኞቹ ጋር ጭምር ለመሥራት ባሳየው የመሪነት ብቃት ነው። .. ”
“ጠቅላይ ሚንስትሩ የጠቅላይ ጦር ዋና አዛዥ ነው። የጠቅላይ ጦሩ ዋና አዛዥ እንደ መሆኑ ነው ሕገ መንግሥቱን የማክበር እና የማስከበር ግዴታ አለበት ይላል።” አቶ ሙልጌታ አረጋዊ፤ የሕግ ባለ ሞያ።
"ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የባሕር በር ጉዳይ መጠየቅ በጦርነት ናፍቆት ይመሰላል። የተሳሳተ አተያይ።.መጀመሪያ የሕግ የተፈጥሮና የታሪክ መብት ያለን መሆኑን የሚቀበል አስተዳደር ይኑረን ነው። ከመቀበል ነው የሚጀምረው።"- ቴዎድሮስ ጸጋዬ "በሃሳቡ ብስማማም። ይሄ ጥያቄ ግን አሁን አንገብጋቢው ጥያቄ አይደለም። ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የተፈጸሙና ብዙ መስተካከል ያለባቸው፤ ለኢትዮጵያ ሕልውናም አንገብጋቢ የሆኑ ጉዳዮች አሉ።" - ሼስፒር ፈይሳ
“.. ዲሞክራሲያዊ ምርጫ በሌለበት የማገልገል ፍላጎት የለንም። .. በግድ ማስተዳደር ምን እንደሚመስል ግን አይተናል።..” ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ።
“መሆን አለመሆን የሚለውን የሼክስፒርን ሃምሌት አልኩለት። በጣም በጣም ደስ አለው። የመጀመሪያውን ስክሪፕት ሰጠኝ። መሪ ተዋናይ ሆኜ እንድጫወት መረጠኝ፤ ሺ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ስምንት። መድረኩ ላይ እንደ ሌላ ሰው፤ እንደ ወጋየሁ ለመሆን በምሞክርበት ጊዜ ተናገረኝ። ያኔ ነው ያቃናኝ። ወደ ራሴ የመለሰኝ።” ሟቹ አንጋፋው ተዋናይ ፍቃዱ ተክለማሪያም።
“የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ የዩናይትድ ስቴትስ ጉብኝት፣ ግዙፉ የዋሽንግተን ዲሲው ስብሰባና ሌሎች ቀለመ ብዙው ሥነ ሥርዓቶችና የዝግጅት ሂደት ከዝግጅቱ አስተባባሪዎች ጋር በሚደረግ ውይይት ይቃኛሉ።”
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ ባለፈው ሳምንት መገባደጂያ በሀገሪቱ ያሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች መሪዎችን ወደ ጽ/ቤታቸው ጋብዘው በልዩ-ልዩ ወቅታዊ ርዕሰ-ጉዳዮች ዙሪያ አወያይተዋል።
“የሁለቱ አገሮች የሰላም ስምምነት ለአካባቢው አገሮች፣ በአጠቃላይም ለአፍሪካ ቀንድና ለመካከለኛው ምሥራቅ ያለው ፋይዳ ትልቅ ስለሆነ፤ምሳሌም ስለሆነ፣ በዚህም የተነሳ የተባበሩት አረብ ኤሜሬት የሁለቱ አገሮች መሪዎች ባደረጉት አስተዋጾ ይህን ሽልማት ማበርከታቸውን በሽልማቱ ወቅት ገልጠዋል።”የጠቅላይ ሚንስትሩን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ።
“እንደ እኔ አስተያየት አሁን ዋናው መመለስ ያለበት ጥያቄ በምን መልክ በኤርትራና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ውሕደት ሊፈጠር ይችላል የሚለው ነው። ቁልፉ ኢትዮጵያ እጅ ነው ያለው።” ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ። “አሁን ለተጀመረው ቁልፉን የያዘችው ኢትዮጵያ ናት" በሚለው አልስማም። አሁን የሚደረገው የእርቅ ምመንገድ የተጀመረው በሁለት ብሔረ መንግስታት ልንለው እንችላለን ነው። ስለዚህ ሰጥቶ መቀበልን ከግንዛቤ የሚያስገባ ነው የሚሆነው።”ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀኝ። “ይህ ሁኔታ ዳር እንዲደርስ ሁሉም በየበኩሉ ቀና ለሆነው ለውጥ ራሱን ማዘጋጀት አለበት። 'ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ያደርጉልናል' ብለን ቁጭ ብንል ለስኬት የመብቃት ዕድሉ አናሳ ነው የሚሆን።” ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ።
"ባለፈው ሃያ ሰባት ዓመታት ውስጥ ካየነው ሂደት አንፃር ሲታይ: ይቅርታን መሰረት ያደረገው የሕዝቡን በደል የተረዱት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ የጀመሩት የለውጥ እርምጃ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ተስፋ ያጫረ ነው::" ዶ/ር አፈወርቅ ተሾመ የመዐሕድ ሊቀ መንበር::
"ድንገት "ቷ" የሚል ድምፅ ሰማሁ። እጄ ተንቀጠቀጠ። ጮኹኩ። .. "መቱት፣ መቱት!" እል እንደነበረ ትዝ ይለኛል።.. ዜና አንባቢው ተመልሶ መጥቶ በቦንብ ፍንዳታ የተጎዱ ጥቂት ሰዎች መኖራቸውን ሲናገር መሬት ላይ ተጣጥፌ ቁጭ አልኩ።..”የቅዳሜው ድንገት በአድማጭ ማስታወሻ። “በሥልጣን ላይ ያሉትና ለሥልጣን የሚዘጋጁ መሪዎቻችን ይህን መጽሐፍ በጥሞና ቢያነቡ ምን ያህል ትምህርት ባገኙበት?” አልሁ። 'ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይና በበጎም በጥርጣሬም ዙሪያቸውን ለተሰለፉ ሁሉ ቀበቶዬን አስሬም ቢሆን መጽሐፉን ገዝቼ ልላክላቸው?' የሚል ነገርም ዳዳኝ።” ይልማ አዳሙ።
ተጨማሪ ይጫኑ