በሚሰሩት ሥራም ይሁን በደረሱበት ሥፍራ የሌሎችን ሕይወት ለማሻሻል ይበጃል ያሉትን በማድረግ የተጠመዱ፣ ጊዜና ቀልባቸውንም ለዚሁ መስጠት የመረጡ፤ መንገዳቸውን ማሳመር ብቻ ሳይሆን አነቃቂነቱም ያንኑ ያህል ነው። ከዚያ የሚመደቡ ናቸው እንግዳችን። የትናየት እሳቱ ይባላሉ። ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብላ ከምትገኘው የአሌግዛንድሪያ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ው/ሮ የትናየት በሞያቸው የቤት ግዥና ሽያጭ እንዲሁም የገንዘብ አያያዝ አማካሪ ባለ ሞያ ናቸው።
“አንድ ዶላር በቀን” የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ በውጭ አገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ያቀረቡት ጥሪ “ወገንዎን በተግባር ለመርዳት ባገኙት መልካም ዕድል የአገርዎን ዕጣ ያሳምሩ።” ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማሪያም የኢትዮጵያውያን ተራድዖ ባለ አደራ ቦርድ ሊቀ መንበር
"እፎይታ ተሰምቶኛል። እኝህ ሰው በኢትዮጵያ በተፈጸመው የመብት ረገጣ እጅግ የከፋ የመብት ጥሰትና የተዛባ መረጃ በማሠራጨት ሚና ነበራቸው ብዬ ስለማምን በኃላፊነት በመጠየቃቸው ትልቅ እፎይታ ነው የተሰማኝ።" አና ጎሜሽ የአውሮፓ ፓርላማ አባል።
በሕክምናው የእንግሊዝኛ አጠራር ከለር ብላይንድነስ በመባል በሚታወቀውና ቀለምን የመለየት የተፈጥሮ ችሎታ ማጣት በሚያስከትል የዓይን ጤና ችግር ምንነት ዙሪያ ትኩረት ያደርጋል።
“ዛሬም አፍሪካን ጥለው የሚሰደዱ ሰዎች ካሉ፤ በበርካታ የአፍሪካ አገሮች ሳቢያ ነው። የመጀመሪያዋም አፍሪካን ቅኝ መግዛቷን ያላቆመችው ፈረንሳይ ናት።” የጣሊያኑ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ሉዊ ጂ ዲሜዮ። “የሕብረቱን ፋይዳ በጥርጣሬ የሚመለከቱና ግለኝነት የሚያቀቅኑ ብሔርተኞች የአውሮፓ ሕዝብ ከሚሰማው ስጋት ለማትረፍ ይጥራሉ። “ለሥጋትህም መልሱ ብሔርተኝነት ነው ይሉታል።” የፈረንሳዩ ጠቅላይ ሚንስትር ኢማኑኤል ማክሮን።
".. ሕልም አለኝ! አራቱ ትንንሽ ልጆቼ አንድ ቀን በቆዳቸው ቀለም ሳይሆን፤ በምግባራቸው የሚለኩባት አገር ውስጥ እንደሚኖሩ .. ዛሬ ሕልም አለኝ! .." ማርቲን ሉተር ኪንግ - እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ነሃሴ 28, 1963 ዋሽንግተን ዲሲ።
በሃገር ደረጃ ከዚህ ቀደም የነበሩና ዛሬ ያሉ አሠራሮች እና አነጋጋሪ ርዕሶች የሚቃኙ ቅንብሮች አካል ነው።
".. ሕልማችንን ዕውን ለማድረግ በምናደርገው ትግል .. አሳካዋለሁ ብለን መነሳት መቻል፣ በግል ሕይወታችን እርካታ መጎናጸፍ አለብን።..” 'The Wife' በተሰኘው ፊልም ላይ ዋናዋን ገጸ ባሕሪ ጆአን ካስልማን’ን ሆና ባሳየችው ድንቅ አጨዋወት በዘንድሮው ጎልደን ግሎብ ከሴት ተዋናዮች የዓመቷ ምርጥ ተዋናይ ግሌን ክሎዝ።
“የምንሠራውን ነገር በሙሉ በግልጽና በተጠያቂነት ነው የምናደርገው ብለናል። ገንዘብ እንዴት እንደምንሰበስብ፣ ማን እንደሰጠ ማን እንዳልሰጠ ሁሉ ነገር ግልጽ ነው። እኛ ብቻ የምናወራውን ሳይሆን .. የተሰበሰበውን መረጃ ተመልክቶ ከየት እንደመጣ .. ራሱ አይቶ እንዲገነዘብ ነው።” ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማሪያም የኢትዮጵያውያን ተራድዖ ባለ አደራ የአማካሪ ቦርዱን ሊቀ መንበር።
"ውቭን" ይሰኛል - የሁለት ዓለም ባሕል፣ የኑሮ መስተጋብር ዘይቤና ፈተናዎቹን ከግዙፉ የፊልም ሰሌዳ የከሰተው፤ ኢትዮጵያውያንና አሜሪካውያን ተዋናዮች የተሳተፉበት የሶሎሜ ሙልጌታና የናግዋ ኢብራሂም ፊልም።
”እያገባደድን ባለነው 2018ዓም ብቻ ቁጥራቸው ከሦሥት ሺህ አራት መቶ በላይ የሚደርስ ሰዎች ለሕልፈት ተዳርገዋል።” ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት IOM
"ይህ የTrust Fund ይህ ውጥን ገንዘብ ስለ ማሰባሰብ ብቻ አይደለም። ያሉንን የተለያዩ የሃይማኖት፣ የባሕልና የዘውግ መሠረቶቻችንን በመጠቀም፤ ልዩ-ልዩ ተሞክሮዎቻችንን ለላቀ ጥቅም ማዋል የምንችልበትን መንገድ መፍጠር ጭምር እንጂ" ዶ/ር መና አክሊሉ ደምሴ የመማክርት ጉባኤው ዋና ጸሃፊ።
በልማድ የስኳር በሽታ በሕክምናው የእንግሊዝኛ አጠራር /Diabetes/ በመባል በሚታወቀው በሽታ ዙሪያ ትኩረት የሚያደርግ ቅንብር ነው።
ከዋሺንግተን አዲስ አበባ ደርሶ መልስ
“ዶ/ር አብይ ‘እንዲህ ማድረግ አለበት፣ እንዲህ ማድረግ አለበት’ የሚለውን ሳይ፤ የችግሩን መጠን የተረዳን አይመስለኝም።” ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ። “.. የተወሰኑ በዝርዝር ሊነግረን የማችልም የማይገቡም ነገሮች መኖራቸውን እረዳለሁ። .. ወደ ፊት መሄድ አለብን እያልን ነው። ነገር ግን ወደ ፊት መሄዳችንን በምንድን ነው የምንረዳው?” መስፍን ነጋሽ። “ኢሐዴግ እንደ ፓርቲ ሁለት ዛፍ ላይ ለመውጣት የተገደደ ይመስለኛል።” ሄኖክ የማነ።
በሕክምናው የእንግሊዝኛ አጠራር Post Traumatic Stress Disorder በመባል በሚታወቀው የአእምሮ ሁከት ዙሪያ ትኩረት የሚያደርግ ዝግጅት ነው።
“ማዕቀቡ ከአሁን በኋላ አያስፈልግም” የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ። “ቀድሞውንም መሆን ያልነበረበት” የኤርትራ መንግሥት መግለጫ።
"ከመንገድ ተይዛ እንደ ትልቅ የጦር ምርኮኛ እየተንገላታች ነበር ወደ እስር የተወደችው። .. የዛን ጊዜ ይህንኑ ካሜራ የያዙ ጋዜጠኞች ሰለ እርሷ ወንጀል ነበር ዘገባ ለማቅቅረብ ይሯሯጡ የነበረው።" አንጋፋው የመድረክ ሰው ደበበ እሸቱ። "በመጻፍ እና ጥያቄዎች በማንሳታቸው ብቻ አንዳንዶች ለእስር ተዳርገዋል። አሁን ሳይ እናነትም በነጻ ልታናግሩኝ እኔም በነጻ ልናገር ነው፡፡ አዲስ ሆኖብኛል፡፡ ስዕል ብችል ኖሮ በቀለማት ነበር የምገልጸው።" ብርቱካን ሚደቅሳ።
የቀድሞዋ የተቃዋሚ መሪ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ። ነገ ጠዋት አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
“..እኛ እንደ ባለ ሞያ እንደ ወጣት ለሚፈጸሙ ነገሮች ቲፎዞ ልንሆን አንችልም። እገሌን እደግፋለሁ፣ እገሌን አስቀድማለሁ ሳይሆን .. የምናየው የኛ አገር ነው። ካፌው አገርን ነው የሚመስለው።..” መሪ ተዋናዩ ሚካኤል ታምሬ። “..ካፌ በተፈጥሮ ብዙ ሃሳብ ማስገባትና ማስወጣት ይፈቅዳል። እናም እንዲያ ማድረግ እፈልግ ነበር።” የትዕይንቱ ፀኃፊና ዳይሬክተር በኃይሉ ዋሴ።
ተጨማሪ ይጫኑ