"አሁን የተከተለውን ችግር ተከትሎ የሚናፈስ ሰፊ የሽብር ወሬ አለ። እነዚህን ለማሸበርና ለማወናበድ የሚነሱ የሽብር ወሬዎችን ንቆ አካባቢውን ነቅቶ መጠበቅ መቻል አለበት። አብንም በዚህ ችግር ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ያለው በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ነው።”ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን/ ሊቀመንበር
“ሁለት አቅጣጫ የያዘ ጥቃት ነው። አንደኛው .. በጀነራል ሰዓረ ላይ የተቃጣው .. በኢትዮጵያዊነት ላይ። ሁለተኛው ዶ/ር አምባቸው መኮንን የደረሰው .. በማዕከላዊነት ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው።” ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ። “ይሄ ጥቃት ኢትዮጵያዊነትን ይበልጥ አጠናክሮ መሄድ አለበት ብዬ ነው የማነው። .. ‘ከዚህ ምን እንማራለን?’ .. ‘እንዳይደገምስ ምን መደረግ አለበት?’ የሚለው ተጠናቅሮ መቀጠል አለበት የሚል ዕምነት አለኝ።” አቶ ክቡር ገና።
"የቀደሙት" በሚል ርዕስ ያስተዋወቅነውና በቱባ-ቱባ ሥራዎቻቸው የሚወደሱ የኪነ ጥበብ ሠዎች የሚታወሱበት አዲሱ ቅንብራችን ነው።
መሰንበቻውን ኢትዮጵያ ውስጥ ተቋርጦ የነበረውና (ሲያነጋግርም የነበረው) የኢንተርኔት አገልግሎት ዛሬ ከሰዓት በኋላ አንስቶ ተመልሷል።
በኢትዮጵያ ሰሞኑን የታየው የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ጉዳይ እያነጋገረ ነው።
ቆይታ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ጋር
"አንድን ኅብረተሰብ በወጉ ለማቆም የፍ/ቤት ሚና የቱን ያህል ጥልቅ መሆኑን ዜጎች ብቻ ሳይሆኑ ሁሉስ ምን ያህል ግንዛቤ አለው የሚለው ዳግም መታየት መታሰብ አለበት።" ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት።
የዩናይትድ ስቴትሱ የኢትዮጵያውያን የሽልማት ድርጅት - ማሕበረ ግዩራን ዘረ-ኢትዮጵያ በሃያ ሰባተኛው ዓመታዊ ሥነ ሥርዓቱ ዘጠኝ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ አሜሪካውያን ሴቶችን አከበረ።
”…ጥላሁን ገሰሰ ‘ልብ ላይ ነው ወይስ ጉበት .. ፍቅር ሲይዝ የሚያድርበት?’ ብሎ ድሮ ሥሜት የሚመነጨው ከልብ ውስጥ ነው የሚል ግምት ነበር። አሁን በእርግጥ ይታወቃል። ሥሜትና ሃሳብ የማመንጨት ሥራ የአንጎል ነው።” ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ ገዳ የሥነ ልቦና፣ የነርቭና የአዕምሮ ህክምና ልዩ ባለሞያና ተመራማሪ።
“..ኢትዮጵያ ዛሬ በጠርዝ ያለች አገርናት::.." ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ:: ".. እርግጥምክኒያተ-ብዙ ፈተናዎች የተደቀኑባት አገር ብትሆንም የሚያስፈልጋት ግን የሂደት ማስተካከያ ነው::" ዶ/ር ዮናስ ብሩ::
“ሃገራችን ውስጥ የተፈጠረው የፖለቲካ ዓየር ውጥረት ይታይበታል። በዚህ ውስጥ አንድ ሰው አስርም ቢሆን ተከታይ ያለው፤ ቤተሰቡን ብቻ የሚመራ ቢሆን በጣም በጥንቃቄ መራመድ አለበት። እያንዳንዳችን ከአንደበታችን የሚወጣው ነገር እሳት እየጫረ እንደሆነ መረዳት አለብን። እያንዳንዳችን በምንጽፈውና በምንናገረው ነገር ሳቢያ በሃገራችን ላይ ለሚመጣው ጥፋት አስተዋጾ እንዳለን ማወቅ አለብን እላለሁ።” አርቲስት ታማኝ በየነ የዲሲ ግብረ ኃይል ሊቀ መንበር።
"እንደ እምነቴ ይሄ የሆነው በእግዚአብሔር ነው። በዚህ ደረጃ ሕዝብ ይንቀሳቀሳል ብዬ የሚል ግምት አልነበረኝም። በፍቅር - በሕብረት መቆም ሲቻል ውጤቱ ምን መሆን እንደሚቻል ያሳየንበት ነው። እስካሁን አንድ ሚልዮን ሁለት መቶ ሃምሣ ሺህ ዶላር ደርሷል።"
የፊታችን አርብ ይጀመራል።
የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ፣ የኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ፣ ቦይንግና የዩናይትድ ስቴትሱ የፌዴራል አቭዬሽን አስተዳደር
"መንግሥቱ ሊጠየቅባቸው የሚችሉ .. ያለ ሕግ የፍየል ወጠጤ እያለ በራሱ በደርግ የተነገረው .. በግንቦት 81 የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በተገደሉት ጀነራሎች ሁሉ ሊጠየቅ ይችላል።" አቶ ነሲቡ ስብሃት ከካሊፎርኒያ "ማነው ጠያቂው .. ይህን የመጠየቅ መብት ያለው .. ከደሙ የነፃ ወገን ማን ነው?” የመቶ አለቃ መስፍን ከበደ ከላስቬጋስ
"ባየሁት በእጅጉ ነው የተደመምኩት። እጅግ የዘመነ የሥልጠና ማዕከል፣ ምሥለ በረራ ማሳሪያዎች ብቻ ሳይሆን ባለሞያዎቻቸውም በጣም ብቁና የተዋጣላቸው መሆናቸውን ነው ያየሁት።" የበረራ ጉዳዮች አዋቂው ፕሮፌሰር ነባል ተናጂ ናቸው የኢትዮጵያ ዓየር መንገድን ጎብኝተው ይህን ያሉት።
"…በአንድ በኩል ለለውጡ አልገዛ ያለ ኃይል፣ በሌላ በኩል ለውጡን እኔ ባልኩት መንገድ ብቻ ከፈለጋችሁ ተከተሉኝ የሚል አክራሪ ኃይል፤ ሦሥተኛው ደግሞ በቀደመው ሥርዓት ተጠቃሚ የነበረ ወይም በሠራው ሥራ እንዳይጠየቅ የሚፈልግ ሌላ ኃይል አለ።.." - የአርበኞች ግንቦት ሰባት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ
“Black Panther በምርጥ ፊልሞች ዘርፍ የዓመቱ ኦስካር አሸናፊ ቢሆን ቅር አልሰኝም።” Murray Horwitz .. ዕውቅ ፀኃፊ-ተውኔትና የፊልም ዳይሬክተር አንድን ፊልም ምርጥ የሚያደርገው ምንድነው?
"በዓለም ዙሪያ ሴቶችን ያቀፉ ሀገሮች በዕድገት ቅልጥፍና ለመቆናጠጥ የተሻለ ዕድል እንዳላቸው በምርምር ወይንም በጥናትም ተገጋግጧል፡፡" ቤተልሄም አበራ ግሮነበርግ
"የዛሬ ሰባት ዓመት በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሃውልት ላይ ጥያቄ መነሳቱ ራሱ ሌሎችን ሳይሆን ቢኖሩ ኖሮ ኩዋሜ ንኩርማን ነበር የሚያስገርመው። ምክኒያቱም እነ ክውዋሜ ንኩርማ ወደ አፍሪቃ አንድነት፣ ወደ አፍሪቃ ነጻነት መጣን የሚሉት በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አረዓያነት ነው።" ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ አንጋፋ የታሪክ መምሕር።
ተጨማሪ ይጫኑ