“..ኢትዮጵያን ሲያማት ያመናል የምንልበት ጊዜ ነውና .. ከምንግዜውም በላይ ጸሎት የሚያስፈለገን ጊዜ ነው እላለሁ ..”
በመቀሌው ጉባኤ እንድንሳተፍ ብንጋበዝም ላለመሳተፍ በመወሰናችን "አልተሳተፍንም" ይላሉ።
“እውነት ለራሱ ሲባል አይዘገብም ይባላል። ጋዜጠኛው እንደ ሃኪሙ የሚያደርገው ነገር፣ የሚሠራው ሥራ የሚወስነው ውሳኔ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ስላለ ያንን ተጽዕኖ እየተከተለ ነው መዘገብ ያለበት።” ዶ/ር ተሻገር ሽፈራው። “...የዜናው አዘጋገብ ግጭቱን ይፈታል፣ ግጭቱን ይቀንሳል ወይንስ ባለበት ያቆየዋል የሚሉት ሁሉም ሊከተሰቱ የሚችሉ ውጤቶች በመሆናቸው ነው ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቀው።” ዶ/ር ቴዎድሮስ ወርቅአለማሁ ወርቅነህ።
“ሁላችንንም ተሸክማን የምታድር አገራችንን እንዳናጣት አንዱ አንዱ ላይ ነግሶ ለመታየት ከሚደረግ ሩጫ ተቆጥበን፤ ሁላችንም ዝቅ ብለን አገራችንን ከፍ ማድረግ የምንችልበት፤ የጋራ ታሪክ የምንጽፍበት፤ የጋራ ሃዘን ታሪካችንን ምዕራፎች የምንዘጋባቸው መንገዶች መጀመር አለብን።” የትነበርሽ ንጉሴ - የእርቀ ሰላም ኮምሽን ምክትል ሰብሳቢ።ኮምሽን ምክትል ሰብሳቢ።
"የአሜሪካ ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ኃይሎች ትላንት ለሊት በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ቆራጥንነት የተመላና እጅግ አደገኛ ወታደራዊ ኦፕሬሽን አካሂደው ተልዕኳቸውን በድል አጠናቀዋል።” የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ።
“እንደ ራሳችሁ ሰው እንደተቀበላችሁኝ ‘አገሬ’ አድርጌ የተቀበልኩዋትን አገር ወክዬ ስቀርብ ታላቅ ኩራት ነው የተሰማኝ። .. ለአሕጉረ-አፍሪቃ የመጀመሪያ የሚሆነውን የኢትዮጵያን ‘የባሕል መስክ’ ለመሰየም ስንበቃም የሰው ልጆች ምንጭ ከሆነችው አገር ታሪካችን እንደ መተሳሳር የሚቆጠር ነው።”
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የዘንድሮው የሰላም ኖቤል የመሸለማቸውን ዜና ተከትሎ የሽልማቱን ምንነት፣ አንድምታና ፋይዳ መልከት የሚያደርግ ቅንብር ነው።
"ከደረት በስተጀርባ የሚያቃጥል፣ ከጨጏራ ወደ ላይ የሚፈላ የሕመም ሥሜት ነው" ዶ/ር እንዳለ ካሳ የውስጥ ደዌና እንዲሁም የጨጏራ እና የጉበት በሽታዎች ሃኪም ናቸው።
"ችግሮችን ስናስብ ወደ መቆም ነው የምንሄደው። .. መቆም መልስ አይደለም። ሁልግዜ ችግሮች አሉ። ችግሮችን ለመፍታት መሞከር ነው። አንዴ ተፈጥረናል በዚህ ምድር ላይ ባየነው ነገር ላይ በሁለት እግር ቆመን .. እንፈታዋለን ብለን መሞከር" አቶ ክብረት አበበ የኢትዮጵያ ማሕበራዊ ሥራ ፈጣሪዎች ማሕበር የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት።
"ትምሕርት ጨርሶ ሥራ የሚፈልግ ሳይሆን ሥራ ፈጣሪ የሚሆን ተማሪ ለማፍራት ልዩ ሥልጠና ይፈልጋል። ያን ነው ለማድረግ እየሰራን ያለነው።" ዶ/ር ያቆብ አስታጥቄ “አንድ መሥራች አባላችን እንደሚለው‘በገበሬው ግብር ክፍያ ተምረን ይህችን ያህል ለሃራችን መልሰን የመስጠት ኃላፊነት አለብን’ የሚለው ዓላማ ትልቁ ሆኖ ስላየነው ፈተናዎቹን ለማለፍ ረድቶናል። ቶሎ ተቀባይነት ማግኘት ያለመቻል ተስፋ ሊያስቆርጥ ይችላል.." አቶ ሳምሶን ደምሴ ተፈራ
"በእኔ አስተያየት ምክኒያቱ ዝነኛው ምሁር /Peter Drucker/ የነገሩን ነው። ማኔጅመንት ዋናው፣ የቀረው ነገር ሁሉም የእርሱ ውጤት ነው። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ እንደሚገባት ያላደገችው እንደሚገባት ስላልተመራች ነው። ይሄም አባባል ድህነትን ከአመራር ግድፈት የመነጨ ችግር ያደርገዋል።” አቶ አባተ ካሳ የሥራ አመራር ሞያ አማካሪ።
“አንድ ሰው ስለ ራሱ፣ ስለ ሌሎችና ስለ ዓለም ያለው አስተሳሰብ ሁሉን ነገር ከመጠን በላይ በችኮነት የሚያይ ከሆነ፣ ሰዎች ተነስተውብኛል ሊያጠፉኝ ነው ካለ ከፍተኛ የንዴትና የስጋት ስሜት ሊፈጥርበት ይችላል።" ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ። “.. ድንገት እንዲህ ባለ ቁጣ የሚዋጥን ሰው የሚተነኩ ነገሮች የትየለሌ ናቸው። ምክኒያታዊነት የለውም። ያን ስሜት እንደ ሱስ ማረቅ ነው የሚሻለው።..” ዶ/ር ዋልተንጉስ ዳርጌ።
“ሕግ አውጭዎቹ ያንን ዕድል .. የአደጋው ሰለባዎች ቤተሰብ አባላት የምስከርነት ቃል ለመስማት መፍቀዳቸው .. ስለተፈጠረው አደጋ ምንነትና የተጎጂው ቤተሰቦች ስላሉበት ሁኔታ እንዲያውቁ ይረዳቸዋል፤ ብዬ አምናለሁ።” አቶ ዘካሪያስ አስፋው - በአደጋው ወንድማቸውን ያጡ። “..ዳግም ይህን መሰል አደጋ እንዳይከሰት ለሚደረጉ ጥረቶች ያግዛል።..” አቶ ሼክስፒር ፈይሳ - የሕግ ባለሞያ
“..የክልልን ጥያቄ የሚቃወሙ ግለሰቦች ናቸው ባሏቸው እና አልፎ አልፎም ከሌላ አካባቢ መጡ በሚሏቸው ለ’ጀነሬሽን’ በኖሩ ሰዎች ላይ የተፈጸመው እጅግ አሳዛኝ (ድርጊት) ነው። “ አቶ ደጀኔ ወልደ አማኑኤል። “.. ጥያቄው ሰፊ መሠረት ያለው ነው። ነገር ግን የመናበብ ችግር ነው የሚታየኝ።..” አቶ ሽመልስ ኪታንቾ።
"እኔ ጋሽ ማሕሙድን የማውቀውም የቀረብኩትም ያው በሙዚቃው ዘርፍ ነው። .. ከድሮ ጀምሮ .. ሁሌም ለአዲስ ነገር ቅርብ ሆኖ የማውቀው ጋሽ ማሕሙድ ነው። በዓለም ደረጃ የኢትዮጵያን ሙዚቃ በመወከል የሰራና አሁንም እየሰራ ያለ የሙዚቃ ሰው ነው።” ሙዚቀኛው ቶማስ ጎበና።
የኢትዮጵያው ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ ጄኔራል ዐደም መሃመድን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አድረገው ሾመዋል፡፡
“..ቅዳሜ ባሕር ዳር እና አዲስ አበባ በተከሰተው ድርጊትና ከዚያም በኋላ የሚወጡት መረጃዎችና ከዚህም ከዚያም የሚሰሙት ነገሮች እነኝህ ሁሉ ስሜቶች ባንዴ እንዲሰሙን አድርገውናል። ለተጎዱና ልባቸው ለተሰበረ ወገኖቻችንን መጽናናትን ለማጋራት ነው።..” አቶ ተመስገን መንግስቱ የአማራ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ የሕዝብ ግንኙነት ተጠሪ።
ተጨማሪ ይጫኑ