በየዓመቱ በሚያዝያ ወር ሁለት በዓለማችን የተፈፀሙ ሁለት ዋና ዋና የዘር ፍጅቶች ይዘከራሉ። አንደኛው እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1994 የተፈፀመው የሩዋንዳው የዘር ማፅዳት ዘመቻ ሲሆን ሌላኛው ከአንድ ምዕተ ዓመት በፊት በአርሜኒያ የተፈፀመው ነው። የሩዋንዳውን ዕልቂት አስመልክቶ የተነገሩ የምስክርነት ቃሎች ያጠኑ ሁለት ባልና ሚስት የታሪክ አጥኚዎች የጻፉትን መፅሃፍ ለንባብ አብቅተዋል።
“..ሁለት ዓመት አንድ ዓመት የለንም። ወራትም የለንም። ቀናት ናቸው ያሉን። አሁኑኑ ማድረግ ያሉብንን ሥራ ካላደረግን በቀላሉ ሊረፍድብን ይችላል?” ዶ/ር ሶስና ከበደ። “ኢትዮጵያም አሁን ዕድል የሚሰጠው መስኮት አልተዘጋም። ..ከውጭ ጋር ምንም ግንኙነት ሳይኖረው ከየት እንደመጣ ያልታወቀ ኢንፌክሽን መታየት ሲጀምር፤ ሁለተኛው ደረጃ ላይ ሲደርስ? ያኔ ነው አስደንጋጭ የሚሆነው።” ዶ/ር ዳውድ ሰይድ ሲራጅ።
“..ሕዝባችንን ከአደጋ ለመጠበቅ፣ በሽታውን ለመቆጣጠር የሚያግዙ እና የቫይረሱ መዛመት በማሕበረሰብ ና በምጣኔ ሃብት ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ አስቸኳይ እና ጥብቅ ዕርምጃዎች ለመውሰድ ወስነናል። አደጋን ለመቆጣጠር በወጣው ድንጋጌ መሠረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀናል። ይህም ወረርሽኙን በመከላከል እና ሥርጭቱን በመቀነስ ላይ የሚያተኩር የተቀናጀ የአደጋ አመራር ዘዴ እንዲኖረን ያስችለናል፡፡ ..” የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዝዳንት ሲረል ራማፎሳ።
ለማሕበረሰብ ደህንነት አስተዋጾ ያበረከቱ ተከበሩ።
ውጥረት በበዛበት እና አሳሳቢ ነገሮች በተበራከቱበት ዓለም በሙዚቃ መታደስ አንድ ነገር ነው። ከዚያ ሻገር ብሎ ሙዚቃ ለዕለት-ተዕለት ሕይወታችን ያለውን ፋይዳ በማወቅ እና በመረዳት ትሩፋቱን መቋደስ መቻል ነው የዚህ ፕሮግራም ዓላማ።
“..እንደዚህ ዓይነት ሕመም እየተዛመተ ባለበት (መደበኛ) ሥራ እንደ ቀድሞ መቀጠል ይቻላል ወይ? ውይይት መጀመር አለበት። ትምሕርት ቤትሮች መዝጋት ቢያስፈልግ .. ሆስፒታሎች (አስፈላጎጊ ቢሆን) ሌላውን የሕክምና አገልግሎት ትተው ወደ ዚህ ሊዞሩ ስለሚችሉበት ሁኔታ ውስጣቸውን ፈትሸዋል ወይ? .. ይሄ ነው መሠራት ያለበት።” ዶ/ር ዳውድ ሰይድ ሲራጅ በዊስኮንሰን ዩኒቨርሲቲ የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና መምሕር።
: “...ወዲያውኑ አሸናፊ የሚያደርገውን የ1991 ድምጽ አንዳቸው ካላገኙ፤ ያኔ ነው ፈተናው የሚመጣው። ከዚያ በመለስ ግን ሁለቱ ተፎካካሪዎች በደንብ እስከ መጨረሻው መፋተጋቸው በተለይ ለዲሞክራት ፓርቲው መራጮች በጣም ጥሩ ነገር ነው።...” ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማሪያም።
“እኔ እንደሚመስለኝ ሙዚቃ ምናልባት እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠው አንድ ምትሃታዊ ጥበብ ነው የሚመስለኝ።” ሄኖክ ተመስገን - ሙዚቀኛ። “... መንፈስ የሚያጥብ ነው ሙዚቃ። ... እርግጥ እንደ ሙዚቃው ዓይነት ነው።.. ለምሳሌ ትዝ ይለኛል በ1970ዎቹ የአስቴርን ሙዚቃ በምንሰማበት ጊዜ ፍቅር ያልያዘው ሰው እንኳን ፍቅር እንደ ያዘው እንዲሰማው ያደርጋል የአስቴር ሙዚቃ። ...” ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ ገዳ - የአንጎል ሃኪም።
“.. ሁሌም የምታሰበው ያንን ሥራ ሰርቼ ሕዝብ ጋ ደርሶ እያልክ ነው። .. ከተሠራ ለዕይታ ከበቃም በላ ቢሆን ‘መሻሻል አለበት’ በሚል እኔ አልረካም። .. ሰው ተመልክቶ ሲደሰት ሳይ ደግሞ ለራሴም ይገርመኛል።” መራሔ ጥበብ ታደሰ ወርቁ።
“አንድ ዕድል ነው ያለን! በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይገባ መከላከል ካልቻልን፤ አንዴ ይሄ ሕመም ኢትዮጵያ ውስጥ ከገባ የጤና ተቋማቱ አቅቅም የተሟላ ባለመሆኑ - ‘ከገባ በኋላ እንሰራለን’ የሚል ሃሳብ እዚህ ላይ የሚሰራ አይደለም።” ዶ/ር ዳውድ ሰይድ ሲራጅ። “ይሄ በሽታ እየጨመረ መሄዱና የአንዳንድ አገሮች ደግሞ ያን የመቋቋም አቅም ጠንካራ አለመሆን በተለይ ለእንደ እኛ ዓይነት አገሮች አሳሳቢ ነው።” ዶ/ር ሊያ ታደሰ።
“..የመንግስት ደጋፊ ወይም የተቃዋሚ ደጋፊ .. የዚህ ሃይማኖት አለያም የዚያ ሃይማኖት ደጋፊ ልንሆን አንችልም። ለሃገሬ አልቆረቆርም ማለት አይደለም .. ጋዜጠኝነት .. የእኛ ታማኝነት ግን ሃቅ ላይ ለተመረኮዘ ጋዜጠኝነት ነው።” ንጉሴ መንገሻ የአሜሪካ ድምጽ የአፍሪቃ ዋና ክፍል ዲሬክተር።
“አደንጋጭ ከሆኑት የኮሮናቫይረስ ይሄ ሶስተኛው ነው። በተፈጥሮው ከአእዋፋት ወደ ሰው የሚተላለፍ ቫይረስ አደገኛ የሚሆነው ከሰው ወደ ሰው መተላለፍ ሲጀምር ነው። አሁን ከዚያ የደረሰ ይመስላል። አሳሳቢ ያደረገውም ያ ነው።” ዶ/ር ዳውድ ሰይድ ሲራጅ በዊስኮንሰን ዩኒቨርሲቲ የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና ክፍል ፕሮፌሰር።
“ኢትዮጵያን በሚመለከት በአንድ በኩል ብዙ ተሥፋ የሚሰጥ በሌላ በኩል ደግሞ ተሥፋ የሚያስቆርጥ ሁኔታ ባይም፤ ይሁንና የእኔ መንገድና የእኔ እምነት - ትኩረቴ ተሥፋ ሰጭ በሆኑ ነገሮች ላይ ብናተኩር እንሻገራለን በሚል ስለሆነ የምጽፈውም የምናገረውም ተሥፋ በሚሰጡ ነገሮች ላይ ነው።”ዶ/ር ጌብ ሃምዳ።
"የህይወት ፍልስፍና የምለው አንድ ነገር አለኝ። ከደቡብ አፍሪቃውያን አባባል ነው። በጣ ስለምወደው እንደራሴ ነው የማየው። 'ኡቡንቱ' .. 'የኔ መኖር በአንተም ነው' እንደማለት። የአንዳችን ለሌላችን ስለመፈጠራችን በጣም እርግጠኛ ነኝ።” ዶ/ር ሰላም አክሊሉ።
ቆይታ ከ”አሥር ለጤና “ እና “ቀጥ ከልጅነት” ዘመቻዎች መሪ ዶ/ር ሰላም አክሊሉ ጋር Words of Wisdom: A New Year’s Perspective
“ቀኑ መልስ ይሁን!” የሚለው ዜማ ኤሊዛቤጥ ፓተርሰን የምትባል አንዲት የማውቃት በእጅጉ መንፈሳዊ የሆነች ሴት ናት መነሻዋ። የአምላክን አመላካችነት ከልቧ በመሻት በምታደርሰው የማለዳ ፀሎቷ እና ቀኑን በምትቀበልበት ዕምነቷ ትታወቃለች።..”
“አማርኛ ዘፈን መጫወት ስጀምር በማሕሙድ አህሙድ ‘ከአንች በቀር ሌላ’ እና ቴዎድሮስ ታደሰ ‘ግርማ ሞገስ’ ነበር የጀመርኩት።”ድምጻዊት ቤቲ ጂ።
"ከአርባ ዓመታት በፊት ከሆነው የተማርን አይመስለኝም። ተስፋ መቁረጤ አይደለም። አንዳንድ ጊዜ ግን አንድ እርምጃ ወደፊት ሄደን አራት ወደ ሁዋላ የምንል ይመስለኛል። ምን ዓይነት ሕዝብ ነን? ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን።"ዶ/ር ሞገስ ገብረማሪያም። "ከዛ ትውልድ የምንማርው ከፍተኛ የአገር ፍቅር የነበረው ራሱን የሰጠ መሆኑን ነው። የትኛውም ቢሆን ታዲያ ምን ዓይነት የአንድ ወገን ዕውቀት ርዕዮተ ዓለም የሃገሪቷን ችግር በብቻው ሊፈታ ያለመቻሉን ነው።"አቶ ነዓምን ዘለቀ።
ተጨማሪ ይጫኑ