የአውሮፓ ፓርላማ ትናንት ባቀረበው የውሣኔ ሃሳብ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሁኔታ የገመገመ፣ የተከናወኑ እንቅስቃሴዎችን ያጣቀሰና ግምት ውስጥ ያስገባ፣ የአውሮፓ ፓርላማ ኢንዲወስዳቸው እና የአውሮፓ ኮምሽንም ተፈፃሚ እንድያደርጋቸው የሚጠይቃቸውን እርምጃዎች ያካተተ ነው።
የኦሮሞ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ኅብረት መሪዎች ሰሞኑን ዋሺንግተን ዲሲ ተገኝተው ከኢትዮጵያ አምባሣደር አቶ ግርማ ብሩና ከዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤትና ከውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተዋል፡፡
የኢትዮጵያ የልማትና ዓለምአቀፍ አጋሮች ኦሮምያ ውስጥ ተገድለዋል ያሏቸውን 140 ሰዎች ጉዳይ በቅርበት እንዲፈትሹ ሲቪከስ ተብሎ የሚጠራው የዜጎች ተሣትፎ ዓለምአቀፍ ጥምረት ጥሪ አሰምቷል፡፡
ኒው ዮርከ ከተማ ውስጥ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላይ ፅ/ቤት ደጅ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ኦሮምያ ውስጥ እየፈፀመ ናቸው ያሏቸውን አድራጎቶች በመቃወም ከተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ከተሞች የተጠራሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሰልፍ አድርገዋል፡፡
ሰሞኑን ኦሮምያና አማራ ክልሎች ውስጥ በታዩት ያለመረጋጋት ሁኔታዎች ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት በወሰዳቸው እርምጃዎች ላይ የአውሮፓ ኅብረት ምክትል ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተወያዩ፡፡
ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ ሰሞኑን ኦሮሚያ ውስጥ በተፈጠረው ተቃውሞና አለመረጋጋት ምክንያት “ተገደለ” ያሉት ሰው ቁጥር ሰማንያ ዘጠኝ መድረሱን የመድረክ ምክትል ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊው አቶ ጥላሁን እንደሻው ገልፀዋል።
ሰሞኑን የወጣ የአሜሪካ መንግሥት መመሪያ “እንቁላል ብሉ፤ ቡናም እስከ ስድስት ኩባያ ብትጠጡ የጤና ሥጋት ሊያድርባችሁ አይገባም”ብሏል። ለጤናዎ ያዳምጡት።
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ዛሬ ባለአምስት ጥያቄ መግለጫ አውጥቷል፡፡
በሳዑዲ ኤምባሲ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ኤርትራ አውግዛለች።
በሳዑዲ አረቢያና በኢራን መካከል የተካረረው ውዝግብ የፖለቲካ እንጂ የዕምነት ጉዳይ አይደለም ሲሉ ሁለት ምሁራን ለቪኦኤ ገልፀዋል። ማረሚያ፡- በቀደመ ዘገባ "ሱዳን የሳዑዲ አረቢያን አምባሣደር አባርራለች" የተባለው፤ "የኢራንን አምባሣደር አባርራለች" በሚል እንዲታረም ከይቅርታ ጋር እናሳስባለን፡፡
ዲላ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ትናንት፤ ሐሙስ ምሽት ላይ በተጣለ አደጋ የሁለት ተማሪዎች ሕይወት መጥፋቱ ተዘገበ፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ቀድሞም በሴፍቲ ኔት ታቅፈው ምግብ በቋሚነት የሚረዱትን ጨምሮ በመጭዎቹ ወራት የተረጂው ቁጥር 18 ሚሊየን መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በእሥር ላይ የሚገኙትን ጋዜጠኞችን እና ሃሳብን በመግለፅ ነፃነታቸው በመጠቀማቸው ምክንያት የታሠሩትን ሌሎች ሰዎች በሙሉ እንዲፈታ፤ ፀረ-ሽብር አዋጁንም የተቃውሞ ድምፅ ማፈኛ አድርጎ ከመጠቀም እንዲቆጠብ ዩናይትድ ስቴትስ አሳሰበች።
ኦሮሚያ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ዩኒቨርሲቲዎችና ወለጋ ሆሮ ጉዱሩ ውስጥ ዛሬም ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ግጭቶች እንደነበሩ፣ ጉዳቶች መድረሣቸው ተሰምቷል፡፡
እንኳን ለ1490ኛው የነብዩ መሐመድ የልደት ቀን - መውሊድ አደረሣችሁ።
ቡሩንዲ ውስጥ አሕጉራዊ አቃቤ ሰላም ኃይል እንዲሠማራ የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት ከትናንት በስተያ ቅዳሜ ወስኗል።
አሜሪካና ሩሲያ አብረው ከሠሩ ሦሪያ ውስጥ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃን ኬሪ አስታወቁ፡፡
ጋዜጠኞችን በማሰር ቻይና በዓለም አንደኛ ሃገር መሆኗን ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች ደኅንነት ተሟጋች ቡድን - ሲፒጄ አስታወቀ። ቡድኑ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት በዓለም ዙሪያ የጋዜጠኞች እሥራት በመጠኑ መቀነሱንም አክሎ አመልክቷል።
ተጨማሪ ይጫኑ