ኤችዋንኤንዋን ኢንፍሉዌንዛ ወይም የበረታው ጉንፋን ኢትዮጵያ ውስጥ ከተከሰት ባለፉት ወደ ሦስት በሚሆኑ ሣምንታት ጊዜ ውስጥ አራት ሰዎች መሞታቸውን የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባለሙያ አስታወቁ።
የአፕል ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቲም ኩክ የአሜሪካ መንግሥት ጥያቄና አቋም’ኮ “አስደንጋጭ ነው” ብለውታል።
እማኞች እንዳሉት የዴሞክራሲያዊ ለውጥ መድረክ የሚባለው ቤሲጄ የሚመሩትን ተቃዋሚ ድርጅት ሌሎችም የአመራር አባላት ፖሊስ ይዞ መውሰዱን እማኞች ተናግረዋል።
ኦሮምያ ውስጥ በምሥራቅ ሐረርጌና በምዕራብ አርሲ አካባቢዎች ሰሞኑን የታየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ዛሬም ቀጥሎ በተለይ በምሥራቅ ሃረርጌ ጉራዋ ሕይወት መጥፋቱ ተሰምቷል።
ምዕራብ አርሲ ውስጥም ከከትናንት በስተያ አንስቶ ግጭቶች መኖራቸው ተሰምቷል።
ፖሊስ እየጠራ እንደሚያስፈራራቸው የወልቃይት - ማይ ካድራ ሰዎች ተናገሩ።
ባለፈው የአውሮፓ 2015 ዓ.ም ውስጥ ለደረሱት የተፈጥሮ አደጋዎች የአየር ንብረት ለውጥ እና የኤል-ኒኞ ክስተት አስተዋፅዖ ማበርከታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያወጣው አዲስ የጥናት ሪፖርት አስታወቀ።
የምግብ እጥረቱ ቀውስ እንዲሁ ከቀጠለ ደግሞ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናዊያን እጅግ ለበረታ ረሃብ ሊጋለጡ እንሚችሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የረድዔት ተቋማት እያስጠነቀቁ ነው።
የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይል ትጥቅ ፈትቶ ወደ ሥልጠና እንዲገባ መደረጉን ያነጋገርናቸው የአካባቢው ነዋሪዎችና አንድ የወረዳ ምክር ቤት አባል አረጋግጠውልናል፡፡
ከተሣፋሪዎቹ አንድ ሰው መሞቱ ከመነገሩ በስተቀር ሌላ የደረሰ ጉዳት ይኑር አይኑር አልተገለፀም።
ሰሞኑን ጋምቤላ ውስጥ እየታየ ያለው ችግር ለብዙ ሕይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።
ብራዚል በዚህ ካለፈው ግንቦት አንስቶ እያስጨነቃት ባለውና አሁን ከቁጥጥር ውጭ የሆነ በሚመስለው ዚካ ቫይረስ ተቀስፈው ከተያዙት የላቲን አሜሪካ ሃገሮች አንዷ ነች።
ጋምቤላ ክልል ውስጥ ሰሞኑን እየተፈጠሩ ባሉ ግጭቶች ብዙ ህይወት መጥፋቱ እየተዘገበ ነው።
እሥላማዊያኑ ፅንፈኞች በተወሰኑ የማሊ አካባቢዎች ሙዚቃ የሚባል እንዳይሠራ፣ እንዳይሠማ ከከለከሉ ከሦስት ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የዚህችን የምዕራብ አፍሪካ ሃገር የአካባቢዋ የባሕል መናኸሪያነት መልሶ ያፀናል የተባለ የሙዚቃ ድግስ በዋና ከተማይቱ ባማኮ እየተሠናዳ ነው።
ዓለም ከፊቷ በተደቀኑ አደገኛ በሽታዎች ሥጋት እየተዋጠች መሆኗን በመግለፅ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ማርጋሬት ቻን አሳስበዋል፡፡
በዓለም ዙሪያ የሚሰማው የምጣኔ ኃብት ድቀት እና የማኅበራዊ ነውጥ ፍራቻ አምባገነን መንግሥታት በአውሮፓ አቆጣጠር ባለፈው 2015 ዓ.ም ይበልጥ አፋኝና ጨቋኝ እንዲሆኑ ሰበብ ሳይሰጣቸው እንዳልቀረ ዛሬ የወጣ የዓለም የነፃነት ሁኔታ ሪፖርት አስታውቋል፡፡
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደርሳማንታ ፓወር ባለፈው ቅዳሜ አዲስ አበባ ተገኝተው ከኢትዮጵያየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር በአካባቢያዊናበኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፤ የሲቪል ማኅበረሰብተጠሪዎችንም አነጋግረዋል።
የአውሮፓ ፓርላማ ከትናንት በስተያ ሐሙስ በኢትዮጵያ ላይ ያሣለፈውን ውሣኔ ለማስቀረት የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ መሥመሮች ጥረት ሲያደርግ እንደነበረ የፓርላማው አባል አና ጎምሽ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡
ሰሞኑን ኦሮምያ ውስጥ ካለው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ መሪዎች እነ አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
ፓርላማው ውሣኔውን ያጸደቀው በ7ቱ ድጋፍ መሆኑን አና ጎሜሽ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል አመልክተዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ