በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማደሪያ ላይ ቃጠሎ ደርሷል።
ኦሮምያ ውስጥ በጉጂ ዞን እሥራት እየተካሄደ መሆኑ ተሰምቷል
ረዳት ሚኒስትር ማሊኖውስኪ ነገ ረቡዕና ሓሙስ ሩዋንዳን ይጎበኛሉ። በዚያ ከመንግስቱ ባለሥልጣናት እና ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ስለመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ስለመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ቁጥጥር ይነጋገራሉ። በአካባቢ ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይትም የሚያካሂዱ መሆኑ ታውቋል።
ኦሮምያ ክልል ውስጥ በሆሮ ጉዱሩ ዞን የታሠሩ ሰዎችን እንዲያቀርብ ዳኛ የሰጠውን ትዕዛዝ ፖሊስ አልቀበልም ማለቱ ተነግሯል።
በምዕራብ ትግራይ ዞን ወልቃይት አካባቢ ከተነሣው የማንነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ ማዋከብ እየደረሰብን ነው ያሉ የጠገዴ ቀራቅር ነዋሪዎች ዛሬ ሰላማዊ ሠልፍ ማደረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡
ኤርትራ ላለፉት ስምንት ዓመታት ይዛቸው የቆየቻቸውን አራት ጂቡቲያዊያን የጦር እሥረኞችን ለቅቃለች። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የጦር እሥረኞቹን መፈታት ዜና በአድናቆት መቀበላቸውን አስታውቀዋል። የቀሪዎቹ እሥረኞች ደኅንነት እንደሚያሰጋት ግን አሜሪካ ገልፃለች።
ከወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር የተያያዘ ሕዝባዊ ስብሰባ በቅርቡ ጎንደር ከተማ ውስጥ ተካሂዷል።
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኛ አንተኒ ስካሊያ ሞት ምክንያት የተፈረውን ባዶ ቦታ ለመሙላት ሕግ በሚያዝዛቸው መሠረት ትናንት ሜርሊክ ጋርላንድን መርጠው አሳውቀዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኛ እንዲሁኑ የፌደራሉን ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዳኛ ሜሬዲክ ጋርላንድን መርጠው አቀረቡ።
በሰሜን ሦሪያ ክፍል በተቆጣጠሩት ግዛት ላይ የራስ ገዝ ፌደራል ክልል እንሚያውጁ የግዙፉ የሶሪያ ኩርድ ፓርቲ አባላት አስታወቁ።
“ድርቅ የሚያስከትለው የበረታ ረሃብ እራሱ በሽታ ነው” ይላሉ የሥነ-ምግብ ጤና ባለሙያዎች፡፡ የአካልና የአዕምሮ ጤና ጉዳቶችን ያስከትላል። በሕፃናት ላይ በዕድሜ ዘመን ሙሉ የማይሽር የዕድገት መቀጨጭን ያመጣል።
የሶሪያ የሰላም ድርድር ዛሬ ጄኔቫ ላይ እንደገና ተጀምሯል፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት የመፍጠር ጥረት ክፋት አሣቢዎች ሊያደናቅፉት ውስጥ ውስጡን ጥረት ሊያደርጉ እንደሚችሉ ስቴፋን ዴ ሚስቱራ አስታውቀዋል፡፡
ሰልፈኞቹ የኢትዮጵያ መንግሥት ኦሮምያ ውስጥ የሚያካሂደውን ግድያ ያቁም፣ ኦሕዴድ ሥልጣን ይልቀቅ፣ ለተጎዱ ካሣ ይከፈል የሚሉና ሌሎችም ጥያቄዎችን የያዙ ነበሩ።
የዴሞክራቶቹን ሩጫ ክሊንተን፤ የሪፐብሊካኑን ትራምፕ እየመሩ ነው፡፡
ቱኒዝያ ከሊብያ ጋር ያላትን ወሰን መዝጋቷ ሁለቱ የሊብያ ተገዳዳሪ መንግሥታት ወደ ውኅደት እንዲገቡ ግፊቱን እንደሚያበዛባቸው እየተሰማ ነው፡፡
ባለፈው የአውሮፓ ዓመት ውስጥ ከኢትዮጵያና ከሶማሊያ በጦርነት ወደምትታመሰው የመን ከዘጠና ሁለት ሚሊየን በላይ ሰው መግባቱን ዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት - አይኦኤም አስታውቋል፡፡
በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከትናንት በስተያ ቅዳሜ ኢትዮጵያ ውስጥ በደረሰው ድርቅ ምክንያት ለተፈጠረው የምግብ እጥረት ድጋፍ ለመላክ የሚያስችል ገንዘብ ለማሰባሰብ ተገናኝተው ነበር።
ዶ/ር ማይገነት ሺፈራው በ69 ዓመት ዕድሜአቸው አልፈው አስከሬናቸው ባለፈው ሣምንት ሜሪላንድ ውስጥ አርፏል።
በምዕራብ ሐረርጌ መቻራ፣ በወለጋ ነቀምትና በሊበን ነጌሌ ከተሞች ውስጥ የተለያዩ የተቃውሞና የግጭት እንቅስቃሴዎች ትናንትናና ዛሬ እንደነበሩ የየአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
በወልቃይት የሕዝብ ፊርማ የተደገፈ ደብዳቤ ይዘው ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሄደው ከነበሩ መካከል የነበሩት አቶ ባየው ካሰኝ ዛሬ ከቀትር በኋላ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገልጿል።
ተጨማሪ ይጫኑ