በሰሜን አሜሪካ ሰላሣ ሦስተኛው የስፖርትና የባሕል ፌዴሬሽን ፌስቲቫል ካናዳዪቱ ከተማ ቶሮንቶ ላይ ቀጥሏል፡፡
የቅዱስ ሮማዳን ወር ማብቂያ የሆነው 1437ኛው ኢል አል ፍጥር ዛሬ በመላ ዓለም ሙስሊሞች ዘንድ እየተከበረ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ባለፈው ሣምንት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት መመረጧን ተከትሎ ከተለያዩ ወገኖች የተለያዩ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው፡፡ ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን ሂዩማን ራይትስ ዋች ድምፃቸውን ቀድመው ካሰሙት ወገኖች መካከል ሆኖ ይገኛል፡፡
በአሜሪካ የሚገኘው የመላ ኢትዮጵያ ስፖርት ማኅበር አምስተኛ ፌስቲቫሉን ዛሬ ጀመረ፡፡
የኤርትራ መንግሥት ቃል አቀባይ በመንግሥታቸው ላይ የተነገረውን ውንጀላ ውድቅ አድርገዋል፡፡
ሶማሊያ ክልል ውስጥ የመንግሥት ወታደሮችና የክልሉ ልዩ ፖሊስ ጥቃት አድርሰው ሃምሣ አንድ ሰው ገድለዋል ሲል የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ስሞታ አሰምቷል፡፡
የበረታ የምግብ እጥረት ሊደርስ የሚችለው ጤናማ የሆነ አመጋገብ ባለመኖሩ ብቻ አለመሆኑን አንድ ሰሞኑን የወጣ የጥናት ሪፖርት ጠቁሟል።
በምዕራባዊ ትግራይ ዞን ማይ ካድራ ከተማ ላለፉት ሃያ ዓመታት ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ቤቶቻቸው በአካባቢው ባለሥልጣናት እየፈረሱባቸው መሆናቸውን እየገለፁ ነው።
“ዩናይትድ ስቴትስ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የደቡብ አፍሪቃ መንግሥት ለማጣጣል ሙከራ ታደርጋለች” ሲሉ፣ የገዢው ፓርቲ ቃል አቀባይ ዚዚ ኮድዋስ ክስ አሰምተዋል። የመንግሥታቱ ቃል አቀባዮች አስተባብለዋል።
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች የድርጅቱ አመራር አባላት በጠቅላላው ሃያ ሁለት ተከሣሾች ዛሬ በተያዘላቸው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ሳይቀርቡ ቀርተዋል።
አልኑር በሽር ሲባል በቆየ በቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል በጉባ ወረዳ በኦሜድላ ቀበሌ ባለ እርሻ ልማት ላይ የሚሠሩ 22 ሠራተኞች በሱዳን ወታደሮች ተጠልፈው መወሰዳቸውን የእርሻ ልማቱ ባለቤት ነኝ ያሉት አቶ ይርሳው የሺወንድም ተናግረዋል።
አራት ተቃዋሚ የኦሮሞ ድርጅቶች በጋራ ለመታገል የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሰሞኑን ባወጡት የጋራ የፕሬስ መግለጫ አስታውቀዋል።
በአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ ውስጥ ሃይማኖት ሁልጊዜ ቁልፍ ቦታ እንደነበረው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃን ኬሪ አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ፤ ሁልጊዜ ተገቢው ግንዛቤ እንደማይሰጠው ተናግረዋል።
“እኔ ሪያክ ማቻር በተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንትነት የደቡብ ሱዳን ሪፑብሊክን በታማኝነትና በሃቅ ላገለግል በኃያል አምላክ እምላለሁ።”
የኢትዮጵያ መንግሥት በሲቪል ማኅበረሰብ ላይ እያካሄደ ነው ያሉትን አፈና እንደሚያወግዙ አሥራ ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት የሆኑ እንደራሴዎች ለምክር ቤቱ የውሣኔ ሃሣብ ረቂቅ አቅርበዋል።
በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ የኦሮምያን የወቅቱን ሁኔታ አስመልክቶ ትናንት ማብራሪያዎች በተሰሙበት ወቅት የተናገሩ የአሜሪካው ኮንግረስ አባላት ከኢትዮጵያ አምባሳደር ጋር ሰሞኑን እንደሚነጋገሩ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ጥቂት ወራት በኦሮምያ ክልል እየታየ ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ተጨባጭ እርምጃ እንዲወስድ የጠየቁ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚኖሩ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት ዛሬ በአሜሪካ ኮንግረስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በሦሪያ ሰላም ጉዳይ ከነገ፤ ረቡዕ ጀምሮ አዲስ የውይይት ዙር ጄኔቫ ላይ ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ባለበት ሁኔታ ሃገሪቱ ውስጥ ያለው ሁከት እየበረታ መጥቷል።
ሁለት ኤርትራዊያን ጋዜጠኞች ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በኢትዮጵያ ተይዘው እንደሚገኙና እስከአሁንም ክሥ እንዳልተመሠረተባቸው የዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮ አስታውቀዋል።
ሶማሊያ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ያለው ፅንፈኛ የሁከት ቡድን አል-ሻባብ እያደረሰ ያለው አደጋ እየበዛ መምጣቱ አሜሪካ በቡድኑ ይዞታዎች ላይ የምታካሂደውን የአየር ድብደባ እንድታጠናክርና እንድታሰፋ ያስገደዳት መሆኑን ዋሺንግተን እየተናገረች ነው።
ተጨማሪ ይጫኑ