የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር መታሠር “ኢትዮጵያ ያወጀችው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ምናልባት ተቃውሞን ዝም ለማሰኘትና በሕገመንግሥት የተረጋገጡ የኢትዮጵያን ዜጎች መብቶች ለመንፈግ ጉዳይ እየዋለ ለመሆኑ ያለንን ሃሣብ ይበልጥ ያጠናክረዋል” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ምክትል ቃል አቀባይ አስታውቀዋል፡፡
በኢትዮጵያ መንግሥት ትናንት የታሠሩት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና የተገኙበትን የአውሮፓ ፓርላማ የእማኝነት መስሚያ መርኃ ግብር ያዘጋጁትና ግብዣውንም ያደረጉት የፓርላማው አባል አና ጎምሽ የአውሮፓ ፓርላማ የዶ/ር መረራን እሥራት በብርቱ እንዲያወግዝ ጠይቀዋል፡፡
“የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር የሆኑት ዶክተር መረራ ጉዲና በኢትዮጵያ መንግሥት መታሠራቸውን ሰምተናል፡፡ ዘገባው አሳስቦናል፡፡ መንግሥቱ በዶክተር መረራ ላይ ያለውን ማንኛውንም ክሥ ለሕዝብ እንዲያሳውቅ በፅኑ እናበረታታለን፡፡ የመታሠራቸው ነገር እውነት ከሆነ አድራጎቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ነፃ ድምፆችን ለማፈን የሚጣሉት ገደቦች እየተጠናከሩ ለመምጣታቸው አንድ ተጨማሪ ማሳያ ነው የሚሆነው፤ በግልፅ ለመናገር ደግሞ ኢትዮጵያ ያወጀችው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ምናልባት ...
በዶ/ር መረራ ጉዲና መታሠር ላይ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ምክትል ቃል አቀባይ ማርክ ቶነር ለጋዜጠኞች ዛሬ የሰጡት መግለጫ በቪኦኤ የአፍሪካ ቀንድ አገልግሎት የአማርኛ ዝግጅት ክፍል እንደሚከተለው ተተርጉሟል፡፡
በኢንዱስትሪ የገፉት የቡድን ሃያዎቹ ሀገሮች ባለፈው ዓመት ፓሪስ ላይ የፈረሙት ስምምነት የሚያዝዘውን ግዴታ ለመወጣት የሚያስችሉ እርምጃዎችን ሳይወስዱ መቅረታቸውን የሚጠቅስ ሰሞኑን የወጣ ሪፖርት ውቅሷል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ሃሣብን ለመግለፅ ነፃነት መድረኩን ክፍት እስኪያደርግና ያሠራቸውን ጋዜጠኞች እስኪፈታ መጎትጎትና ጫና እንዲደረግበት መግፋቱን እንደማያቆም ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች ደኅነንት ተሟጋች ቡድን - ሲፒጄ አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት በመገናኛ ብዙኃን ላይ የሚያካሂደውን ማዋከብ እያባሰ መሄዱን የጠቀሰው ዓለምአቀፍ የጋዜጠኞች ደህንነት ተሟጋች ቡድን /ሲፒጄ/ መንግሥቱ ያሠራቸውን ጋዜጠኞች ባስቸኳይ እንዲለቅቅ ዛሬ ጥሪ አሰምቷል፡፡
ከተለያዩ የሕይወት መስኮች የተሰባሰቡ ከስድስት መቶ በላይ የሚሆኑ የኦሮሞ ተወላጆች በጆርጂያ ግዛት ዋና ከተማ አትላንታ ላይ ያደረጉት ጉባዔ ተጠናቅቆ የሥራ ሠነድ አውጥቷል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ በዚህ በያዝነው ሣምንት ሞሮኮ ውስጥ ይካሄዳል፡፡
በመሪ ሰቴት ዩኒቨርስቲ የምጣኔ ሀብት ፕሮፌሰር ዶ/ር ሰዒድ ሀሰን ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ
ነገ ለሚካሄደው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሚፎካከሩት ሪፐብሊካን ፓርቲው ዶናልድ ትራምፕ ቢመሩጡ ጥሩ ፕሬዚዳንት ይወጣቸዋል ብለው እንደሚያምኑ እና እንደሚደግፉዋቸው አንድ ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊው ፖለቲከኛ ገልፁ፡፡
ኤርትራዊው አትሌት ግርማይ ገብረሥላሴ የኒውዮርክ ማራቶን አሸነፈ፡፡
አሜሪካዊያን አዲስ ፕሬዚዳንት፣ አገረ ገዥዎቻቸውንና እንደራሴዎቻቸውን ሊመርጡ፤ የሕዝብ ውሣኔ ያስፈልጋቸዋል በሚባሉ የአካባቢና ብሔራዊ ጉዳዮቻቸው ላይ ድምፃቸውን ሊሰጡ የቀሩት ዛሬን ሳይጨምር አራት ቀናት ብቻ ናቸው፡፡
ኦሮሚያ ውስጥ ተቃዋሚዎች በውጭ ኩባኒያዎች ላይ ጥቃት ሲከፍቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠር መዋዕለ ነዋይ ወደ ጭስነትና አመድነት ወርዷል።
የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ በሚል ስም የሚጠራ የፖለቲካ ድርጅት ትናንት፤ ዕሁድ ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ላይ በተፈረመ ስምምነት መቋቋሙ ተገለፀ፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት ሰላሣ ሦስት ወራት የፖሊዮ አጋጣሚ አለማታየቱን አንድ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባለሙያ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ አርባ አምስተኛውን ፕሬዚዳንቷን ለመምረጥ ጥድፊያ ላይ ትገኛለች፡፡ የዴሞክራቲክ ፓርቲው ዕጩ ሂላሪ ክሊንተንና የሪፐብሊካን ፓርቲው ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ በየፊናቸው የሚያደርጉት የ“ምረጡኝ” “እኔ እሻላለሁ” ሩጫና ዘመቻ የመጨረሻው ጡዘት ላይ ደርሷል፡፡
በኢትዮጵያ ላይ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ “አላስፈላጊ እና ገዢው ፓርቲ የፈጠራቸው፤ በውስጡም የተፈጠሩበትን ችግሮች ለማስታወስ እንደ ዘዴ የተጠቀመበት ነው” እያሉ ነው።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የጣላቸውን ገደቦችና አፈፃፀሙን የሚመለከቱ ማብራሪያዎች ከመንግሥት እየወጡ ሲሆን በተለያዩ መድረኮች ላይም ውይይቶች እየተካሄዱ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አለመረጋጋት ያለውን አለመረጋጋት “ያቀናጃሉ፥ ይመራሉ፥ ከጀርባ ድጋፍ ይሰጣሉ” ሲሉ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የሚወነጅሏቸው የሃገር ውስጥና የውጭ ኃይሎች ምላሾችን እየሰጡ ነው፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ