በደርግ ዘመን የአውራጃ አስተዳዳሪ የነበሩት አቃቤ ሰላም ቆምጨ አምባው ዛሬ የሕግ ጠበቃና አማካሪ ናቸው።
በመንግሥትና በፓርቲ የተለያዩ ደረጃዎች ግምገማዎች እየተካሄዱና እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆናቸው እየተገለፀ ነው፡፡
በዩናይትድ ስቴትስ 43ኛ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዋከር ቡሽ የተጀመረው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የኤድስ አጣዳፊ ድጋፍ መርኃ ግብር(ፔፕፍር) ዓለመቅፉን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ግዙፍ የተባለለት አስተዋፅዖ አበርክቷል፡፡
ላለፉት ሦስት ዓመታት መረጋጋት ርቋት በቆየችው ደቡብ ሱዳን መንግሥቷ ሠላም ለማስፈን እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ላለፉት አጭር ዓመታት በዋና ፀሐፊነት ያገለገሉት ባን ኪ ሙን ዛሬ ታኅሣሥ 21/2009 ዓ.ም ተሰናብተዋል፡፡
የኦባማ አስተዳደር ወደ ፍፃሜው እየተቃረበ በመጣ መጠን የዋሺንግተንና የመስኮብ ግንኙነት ከድጡ ወደ ማጡ እየተንሸራተተ ይበልጥ እየሻከረ ሲሄድ እያየን ነው፡፡
የተሰናባቹ የኦባማ አስተዳደር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ አብዝተው የሚያሳስቧቸው የእሥራኤል ፍልስጥኤም ግጭት በዘላቂነት የሚቆምበት ጉዳይና የእሥራኤል ጥቅምና ደኅንነትም የሚጠበቅባቸው መላዎች መሆናቸውን እየተናገሩ ነው፡፡
የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ቁርሾ እየተዘጋ ይመስላል፡፡ ያኔ በተቃራኒ ጎራ ተሰልፈው የተናነቁት የዩናይትድ ስቴትስና ጃፓን ዛሬ ወዳጆች ናቸው፡፡ የእርቅን ጉዳይ ግን ሁለቱም ዝም ዝም ከማለት በስተቀር ጨርሶ አልዘነጉትም ነበር፡፡
የናይጀሪያ መንግሥት በሽብርና ሁከት ቡድኑ ቦኮ ሃራም ላይ ቁልፍ ነው ሊባል የሚችል ድል መቀዳጀቱን ገልጿል፡፡
"ተሃድሶ ወስደው ተለቀቁ" በተባሉ ሰዎች መፈታትና በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሣለኝ ንግግር ላይ የሦስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች አስተያየቶቻቸውን ሰጥተዋል፡፡
“ሁከት ውስጥ ተሣትፈዋል” ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት አሥሯቸው የነበሩ ሰዎች ትናንት በመለቀቃቸው ደስተኞች መሆናቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የገለፁ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀድሞም መታሠራቸው አግባብ እንዳልነበረ አመልክተዋል፡፡
ቲቢ በድፍን ዓለም በገዳይነታቸው ቀዳሚ ከሆኑ በሽታዎች መካከል የመሆኑ ነገር እንደቀጠለ ነው፡፡ ባለፈው የአውሮፓ ዓመትም በቲቢ ምክንያት ሁለት ሚሊየን ሰው አልቋል፡፡
በቱርክ የሩሲያ አምባሣደር የነበሩትን አንድሬ ካርሎቭን የገደለው ሲቪል የለበሰና ተረኛ ያልነበረ የፖሊስ አባል “አሌፖን አትርሱ! ሶርያን አትርሱ! የእኛ ሃገሮች ደኅና እስካልሆኑ እናንተም ደኅና አትሆኑም!” እያለ ይጮኽ እንደነበረ እማኞች ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡
ዘጠና ዘጠኝ ዓመቷ ነው “ተብሎ ይታመናል፤ ነገር ግን ከዚያም ሊበልጥ ይችላል” - የዣ ዣ ጋቦርን ዜና ዕረፍት ከሚናገሩት ዘገባዎች በአንዱ ነው እንዲህ የተባለው፡፡
እርስዎ የYahoo! አካውንት አለዎት? መረጃዎችም የግል ገመናዎ ተሰርቀው ሊሆን ይችላል፤ ችላ አይበሉ፡፡ ከአንጋፋዎቹና ከግዙፎቹ የነፃ ኢሜል አግልግሎት ሰጭዎች አንዱ የሆነው ‘ያሁ’ ውስጥ ከተያዙ ተገልጋዮች መካከል የአንድ ቢሊዮኑ የግል መረጃዎች ብዙው ተሰርቋል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢትዮጵያ አስተዳደርና ሰብዓዊ መብቶችን በሚመለከቱ ስፋት ያላቸው ጉዳዮች ላይ በግልፅነት ለመወያያት መስማማታቸውን አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ረቡዕ ታኅሣስ 5/2007 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የገባው በዴሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብቶችና የሥራ ረዳት ሚኒስትር ታም ማሊኖውስኪ የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቡድን ትናንት ረፋድ ላይ መግለጫ ሊሰጡ በዕቅድ ተይዞ እንደነበርና ሊሰጡት የነበረው መግለጫ መሰረዙን ጠቅሰን የዘገብነው ስህተት ስለሆነ "መግለጫ የመስጠት እቅድ አልነበረም" በሚል ይታረም።
ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቴክሣሱን የነዳጅ ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ ለአስተዳደራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት መርጠዋል፡፡
የእሥራት ፍርዱን እየፈፀመ ያለው የፍትሕ ጋዜጣና የፋክት መፅሔት አዘጋጅና አሣታሚ ተመስገን ደሣለኝ የት እንደሚገኝ ቤተሰቦቹ ማግኘት አለመቻላቸውን ገልፀዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ካቢኔአቸውን እያዋቀሩ ባሉበት በዚህ ወቅት አሜሪካዊያንም ዓለምም እነማንን እያነሱ ለየጉዳዩ አውራ እንደሚያደርጉ በንቃት እየተከታተሉ ነው፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ