"ጆን ብራውን በጣም የተበሳጨ አሜሪካዊ ነው፡፡ ባርነት የማስወገጃው ብቸኛ መንገድ ተቋሙን በአምፅ ማሰወገድ ነው ብሎ ያምን ነበር፡፡ በጦርነት መደምሰስ"የሀርፐርስ መሪ ብሔራዊ ፓርክ ዋና የታሪክ ተመራማሪው ዴኒስ ፍራይ የባርነት መሪና ተቃዋሚው ጆን ብራውንና ጓዶቹ ያንን የአሜሪካ የፅልመት ዕድሜ ለማብቃት የጀመሩትን ትግል ያስታውሳሉ፡፡
"ጆን ብራውን በጣም የተበሳጨ አሜሪካዊ ነው፡፡ ባርነት የማስወገጃው ብቸኛ መንገድ ተቋሙን በአምፅ ማሰወገድ ነው ብሎ ያምን ነበር፡፡ በጦርነት መደምሰስ" የሀርፐርስ መሪ ብሔራዊ ፓርክ ዋና የታሪክ ተመራማሪው ዴኒስ ፍራይ የባርነት መሪና ተቃዋሚው ጆን ብራውንና ጓዶቹ ያንን የአሜሪካ የፅልመት ዕድሜ ለማብቃት የጀመሩትን ትግል ያስታውሳሉ፡፡
የዓመቱ ምርጥ አልበም፤ የዓመቱ ምርጥ ቀረፃ፤ የዓመቱ ምርጥ ዘፈን! በእግር ኳስ ቋንቋ ቢሆን ኖሮ ‘ሃት ትሪክ’ ይባል ነበር - በአንድ ጨዋታ በአንድ አግቢ ለሚቆጠሩ ሦስት ተከታታይ ጎሎች! በታላቁ የሙዚቃ ዓለም ፍልሚያ መድረክ፣ በግራሚው ግጥሚያ ግን “ትራይፌክታ” ይባላል።
በአመዛኙ ሙስሊም ከሆኑ ሰባት ሀገሮች ፍልሰተኞችና ስደተኞች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገቡ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጥለውት የነበረውን የማስፈፀሚያ ትዕዛዝ ያስቆመው የሴአትል ዳኛ ውሣኔ በይግባኝ ሰሚ ችሎት ፀና፡፡
እንግሊዝ ከአውሮፓ ኅብረት የምትወጣበትን ሂደት የፊታችን መጋቢት አጋማሽ አካባቢ ልትጀምር ታቅዷል። በምኅፃር “ብሬግዚት” ተብሎ የሚጠራውን ይህንን ሂደት ማስፈፀሚያውን ሕግ የፓርላማው የሕግ መምሪያ ትናንት በድምፅ አፅድቆታል። ይህ በሕግ መምሪያው ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘ ሕግ አሁን ወደ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ ተመርቷል። የሕግ መምሪያው እንደራሴዎች ሕጉን ያሳለፉት 494 ለ 122 በሆነ ድምፅ ነው።
እንግሊዝ ከአውሮፓ ኅብረት የምትወጣበትን ሂደት የፊታችን መጋቢት አጋማሽ አካባቢ ልትጀምር ታቅዷል።
ዛሬ ጥር 29 በሴት የመራቢያ እና የፆታ አካላት ላይ የሚፈፀም ማንኛውም ጉዳት ይህም ማለት ግርዛት፣ መተልተል፣ መስፋት የመሳሰሉ ኢ - ሰብዓዊ አድራጎቶችን የመቃረኛ፣ የማውገዣ፣ ዓለም አቀፍ ቀን ነው፡፡
ኬንያ፣ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳንን አገናኝቶ ወደ ምዕራብ አፍሪካ የሚዘልቅ የትራንስፖርት መተላለፊያ መሥመር ግንባታ ተጀምሯል፡፡
ለአየር ንብረት እየተለወጠና ለምድራችን እየጋለች መምጣት ዋናው ምክንያት የሰው ልጅ ተግባር ነው ሲሉ የተፈጥሮ አካባቢ ተመራማሪዎች የሚያሰሙትን ድምዳሜ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጥርጣሬ ነው የሚያዩት፡፡
"ሕይወትን ለማትረፍ ተሰለፉ" ሕዝባዊ ትዕይንት በዋሺንግተን ዲሲ - January 27/2017 ተካሄደ
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዩናይትድ ስቴትስ ግዛት ውስጥ የሚዘረጉ የከርሰ-ምድር ዘይት ማስተላለፊያ ቦዮችና ቱቦዎች ግንባታ ሥራዎች እንዲጀመሩ ትናንት (ጥር 17/2009 ዓ.ም.) የማስፈፀሚያ ትዕዛዝ ፈርመዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ካቢኔ ዕጩዎች እየፈተሹ ባዶ ቦታዎችን በዚህም ሳምንት ውስጥ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ከበርቴው ነጋዴ ዶናልድ ትራምፕ ነገ፤ ዓርብ ጥር 12/2009 ዓ.ም. በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ደጅ ላይ ቃለ-መሃላ ሲፈፅሙ የሃገራቸው 45ኛ ፕሬዚዳንት ይሆናሉ።
ሶማሊያ ውስጥ ይከሰታል ተብሎ የተሰጋውን የበረታ ረሃብ ለማስወገድ ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።
ከነገ በስቲያ ዓርብ፣ ዶናልድ ትራምፕ ቃለ-መሃላ ፈፅመው 45ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ አሜሪካ ለውጭ ሀገሮች የምትሰጣቸው አንዳንድ ድጋፎች ከዚያ በኋላ ችግር ሊገጥማቸው እንደሚችል እየተሰማ ነው፡፡
ሶማሊያ ውስጥ ግዳጅ ላይ በነበሩ የኬንያ ወታደሮች ላይ አልሸባብ ድንገተኛ አደጋ ጥሎ ቁጥራቸው የበዛ ወታደሮችን ከገደለ ልክ አንድ ዓመት ሆነ፡፡
አሥር የተለያዩ ኢትዮጵያዊያን ድርጅቶች ዋሺንግተን ዲሲ ላይ ከትናንት በስተያ ዓርብ፣ ጥር 5 እና ቅዳሜ ጥር 6 ጉባዔ አካሂደዋል።
የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የስንብት ንግግርና የፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ ትንታኔ
የጋምቢያ ፕሬዚዳንት የሕያ ጃሜ መንበረ ሥልጣኑን ተቆጣጥረው ለመቆየት ያደረጉት ውሣኔ ላይሠምርላቸው እንደሚችል ተነግሯል።
የኢትያጵያ መንግሥትና ገዥው ኢህአዴግ በተኀድሶ እንቅስቃሴ ውስጥ መሆናቸውን እየገለፁ ነው፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ