ያለፈውን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሂደት ለማጣመም ሩሲያ አድርጋዋለች ከሚባለው ጣልቃ ገብነት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ መጠርጠሩ በእጅጉ እንዳሳዘናቸው የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ጄፍ ሴሽንስ በሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ የመረጃና የስለላ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ቀርበው ቃል በሰጡበት ወቅት ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ የአደጋ ጊዜ “ምግብ ክምችት እየተሟጠጠ ነው” ሲሉ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች እያስታወቁ ነው፡፡
ሙስሊም ምዕመናን መመገብ በሚችሉባቸው ሰዓታት ውኃና ፊሣሽነታቸው የበዛ ምግቦችን በብዛት እንዲወስዱ አንድ የሕክምና ባለሙያ መከሩ፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን፤ እንዲሁም የቡና፣ የመድንና የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለቦች ተሠላፊ የነበረው አሰግድ ተስፋዬ ዛሬ /ቅዳሜ ግንቦት 26/2009 ዓ.ም./ ረፋድ ላይ በድንገት አርፏል፡፡
"ብሔራዊ አንድነቷ የተጠበቀ፣ ሰላም የሠፈነባትትና የበለፀገች አንዲት ኢትዮጵያን ማየት!" ባለፈው ቅዳሜና ዕሁድ፤ ግንቦት 19 እና ግንቦት 20 / 2009 ዓ.ም የምዕራብ ዩናይትድ ስቴትሷ ዋሺንግተን ግዛት ውስጥ በሴአትል ከተማ ተጠርቶ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ጉባዔ ተሣታፊዎች ራዕይ ነው፡፡
ግንቦት ሃያ የራሱ የኢሕአዴግ እንጂ «የሕዝብ በዓል ሆኖ ሊከበር ይገባዋል ብዬ አላስብም» ብለዋል የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞራሲ ፓርቲ የቀድሞ ሥራ አባል ዶ/ር ኃይሉ አርአያ፡፡
ግንቦት 21 / 1909 ዓ.ም በዩናይትድ ስቴትስ ምሥራቃዊ ግዛት አንድ "ጃክ" እያሉ የሚጠሩት ኮከብ ተወለደ፡፡ በነፍስ ገዳይ ጥይት በ46 ዓመት ዕድሜው እስከተቀጨ ድረስም በዚህች ምድር ላይ ኖሮ እነሆ እስከዛሬ በዓለሙ ሁሉ እያስተጋባ የሚዘከር፣ የሚነገር ስም ሆነ - ጃን ፊትዠራልድ ኬኔዲ፡፡
የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የጤና ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉባዔ የኢትዮጵያውን ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን የድርጅቱ ስምንተኛ ዋና ዳይሬክተር እንዲሆኑ ዛሬ፤ ግንቦት 15/2009 ዓ.ም መርጧቸዋል፡፡
የኢትዮጵያን ፖለቲካና ምጣኔ ኃብት ሁኔታ የመቀየር ሃሣብ የዞ በ1983 ዓ.ም ወደ ሥልጣን የወጣው አማፂው ኢሕአዴግ መንግሥት ከሆነ በኋላ ባለፉ ሃያ ዓመታት ያሳየው ክፉ ወይም የጭቆና አካሄድ አካባቢያዊና የጎሣዎችን መከፋትን አስከትሏል ሲል - ካርኔጊ ኢንዶውመንት ፎር ኢንተርናሽናል ፒስ የሚባለው የዓለምአቀፍ ሰላም ቅኝት ተቋም ገልጿል፡፡
የሳዑዲ አረቢያ ንጉሥ ሳልማን ለሃገራቸው ሴቶች ተጨማሪ መብቶች እንዲከበሩ ሰሞኑን ያስተላለፉት ውሣኔ ከአንዳንዶች ብዙ ሙገሣ እያተረፈላቸው ነው፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ያለመደሰትና የወቀሣ ውርጅብኝም የሚያጎርፉባቸው አሉ፡፡
በፈረንሣይ ምርጫ አክራሪዋ ብሔረተኛ ማሪን ሎ ፔን በተቀናቃኛቸው ኢማኑኤል ማክሮን ድል መነሣታቸው በይፋ ከተገለፀ ገና ሁለት ቀን መሆኑ ነው፡፡
ዛሬ ሜይ ዴይ ነው - ሚያዝያ 23 /በአውሮፓ ደግሞ ሜይ አንድ/ ዓለምአቀፍ የሠራተኞች፣ የወዝአደሮች ወይም የላብአደሮች ቀን በዓለም ዙሪያ ይከበራል፡፡
ቅዳሜ፤ ሚያዝያ 14 / 2009 ዓ.ም. የዓለም ከተሞች ጎዳናዎችና አደባባዮች በግዙፍ የሣይንቲስቶችና ደጋፊዎቻቸው ሰልፎች ተሞልተው ውለዋል፡፡
የሱዳንን መንግሥት በሙስናና የሃገሪቱን ነዳጅ፣ ወርቅና መሬት በመዝረፍ የሚከስስ ሪፖርት ወጣ፡፡
በመላው ዓለም ክርስትያኖች ዕለተ ስቅለትን ዛሬ አክብረው ውለዋል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ ትናንት ሌሊት በአንድ የሶሪያ የአየር ኃይል መደብ ላይ ያደረሰችውን ጥቃት የአውሮፓ አጋሮቿ ሲደግፉ ሩሲያ የወረራ አድራጎት ነው ስትል አውግዛዋለች፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ