በአማራ ክልል ስድስት ወረዳዎች ውስጥ ካለፈው ግንቦት አንስቶ በተከሰተ የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ወረርሽኝ ቢያንስ የአራት ሰው ሕይወት ጠፍቷል።
ዓለም “ስለአፍሪካ የሚያደርገውን ንግግር ቃና መለወጥ አለበት” ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አሳሰቡ።
ከፀረ-ኤችአይቪ/ኤድስ መድኃኒቶች ጋር የተለማመደው የቫይረስ ዓይነት የኤድስን ሥጋት ይበልጥ እያባባሰው መምጣቱን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልል የተቀነባበረ የማፍረስ ዘመቻ እየተካሄደብኝ ነው ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ትናንት ያወጣውን መግለጫ የክልሉ መንግሥት አስተባብሏል።
- ሰማያዊ ፓርቲ የአማራ ክልላዊ መንግሥትን የፓርቲውን መዋቅሮች ለማፈራረስ እየተንቀሳቀሰ ነው ሲል ወነጀለ
ሰኞ፣ ሐምሌ 10/2009 ዓ.ም. ያረፉት የአንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ የአቶ ነጋሽ ገብረማርያም አስከሬን ሥርዓተ-ቀብር ዛሬ ተፈፀመ። አቶ ነጋሽ ገብረማርያም ያረፉት ባጋጠቸው የኩላሊት መታወክ ሕክምና እየተከታተሉ ሳሉ ነበር።
የአሜሪካ የጤና ጉዳይ ከሰሞኑ የዋሺንግተን የፖለቲካ ግለት አካባቢዎች ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡
ኬንያ፣ ላይቤርያና ኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ለምርጫ እየተዘጋጁ ባሉበት ጊዜ ዋሺንግተን ዲሲ ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ተንታኞች አፍሪካ ውስጥ ስላሉ ዴሞክራሲያዊ ምርጫዎች ቁልፍ ፈተናዎችና የምርጫ ሂደቶች ሊሻሻሉ የሚችሉባቸውን መንገዶች ለይተው ለማንጠር እየሞከሩ ናቸው፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የነፃነት ቀን ሲከበር በየዓመቱ የተለያዩ ዝግጅቶች ይሰናዳሉ ብሔራዊው ቤተ- መዛግብት የእነዚያ ዝግጅቶች ባለቤት ነው፡፡ ከዚህ ዓመት ክንዋኔዎች መካከል “አሜሪካን መጠገን” ተብሎ የተሰየመው ኤግዚቢሽን ጊዜውን የመጠነ ይመስላል፡፡ ይህ ኤግዚቢሽን አሜሪካ የምትገዛበትን፤ መሠረታዊ መርሆች እና የቀደሙ እውነታዎችን ያቀፈ እምቅ ሕገ መንግሥቷን ለመለወጥ የተደረጉ በሺሆች የሚቆጠሩ የከሸፉ ጥረቶችና ሙከራዎችን ያሳያል፡፡
ካታር ከጎረቤቶቿ ጋር ለገባችበት የዲፕሎማሲ ቀውስ መፍትኄ ለመፈለግ እየተንቀሳቀሱ ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ከካታርና ከቀሩት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ከትናንት በተስያ ማክሰኞ ተገናኝተው መክረዋል፡፡
የመኢአድና የሰማያዊ ፓርቲዎች ውይይት በአሜሪካ ድምፅ
በዩናይትድ ስቴትስ ሜን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የወጣ ሪፖርት እንደጠቆመው ወባ ወትሮ ሊተላለፍባቸው የማይችሉ የነበሩ በከፍተኛ ሥፍራዎች ላይ የሚኖሩ ሰዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለቢምቢ መራባትና ለወባ ሥርጭት እየተጋለጡ መሆናቸውን ተመራማሪዎቹ አመልክተዋል፡፡
ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ በ13ኛውና በፒባዲ መንገዶች መገናኛ ላይ በደረሰው የመኖሪያ ሕንፃ ቃጠሎ በሕይወትም ሆነ በአካል ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ አንድ የከተማዪቱ ባለሥልጣን ለቪኦኤ አስታውቀዋል፡፡
ዲጂታል ዴሞራክራሲ ደመወዛቸውን ሕዝብ የሚከፍላቸውን ሠራተኞችና ባለሥልጣናትን እንዲሁም መንግሥታትን የመፈተሻ፣ የመከታተያ፣ የመመርመሪያ አዲስ ዘዴ ሆኗል፡፡
በመጭዎቹ የሰማንያ ዓመታት የጊዜ ጉዞ ውስጥ የኢትዮጵያ ቡና ከሚመረትበት አካባቢ ወደ ስድሣ ከመቶ የሚሆነው ክልል ለቡና ምርት የማይስማማ ሊሆን እንደሚችል ከትናንት በስተያ የወጣ አንድ የጥናት ሪፖርት አስጠንቅቋል፡፡
በብልጥግና የናጠጡት ሃገሮች አፍሪካ ላይ የሚፈስሰውን እርዳታና መዋዕለ-ነዋይ በሚመለከት አዲስ ዓይነት አካሄድ እንዲከተሉ የጀርመን ቻንስለር አንጌላ መርከል አሳስበዋል፡፡
ሰኔ 7 እና ሰኔ 8 / 2009 ዓ.ም. (ትናንትናና ዛሬ መሆኑ ነው) እንዲያውም ሰሞኑንም ሁሉ ይቀጥላል፤ የሌሊቶቹ ሰማዮች ላይ ፕላኔት ሳተርን ከፀሐይ መውጫና መጥለቂያ አንፃር ጥርት ብላ ትታያለች፡፡
ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ውስጥ ተስተናጋጅ በሚበዛባቸው ሁለት ምግብ ቤቶች ላይ ትናንት ምሽት ላይ በተፈፀመ ጥቃት ቢያንስ የሃያ ዘጠኝ ሰው ሕይወት ጠፍቷል፡
ተጨማሪ ይጫኑ