ከሶማሌ ክልል ጋር አዋሣኝ በሆኑ የተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች ውስጥ ሰሞኑን እየታዩ ያሉ ጥቃቶችና ግጭቶች ተዛምተው ዛሬ ባሌ ውስጥ ራይቱ ወረዳ ላይ ቁጥሩ ከአሥር በላይ ሰው መገደሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀውልናል።
የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር - ኦብነግ አመራር አባል የሆኑን አብዲከሪም ሼክ ሙሴን በቅርቡ ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፎ የሰጠው "ከሃገሪቱ ውስጥ የፀጥታ ሥጋትን ለማስወገድ ባደረገው እንቅስቃሴ የተወሰደ ሕጋዊ እርምጃ ነው" ሲል የሶማሊያ መንግሥት አስታውቋል።
ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ለሚያሠራው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ካርታ ሥራ ያሰማራቸው ቡድኖች አባላት ላለፉት ሁለት ወራት ከስምምነታችን ውጭ በሆነ ሁኔታ ደመወዝም አበልም አልተከፈለንም ሲሉ ቅሬታ አሰሙ።
ቡሩንዲ ውስጥ ከሚያዝያ 2007 ዓ.ም. አንስቶ ባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ በመንግሥቱ ደጋፊዎች በሰብዕና ላይ ወንጀሎች ተፈፅመው ሊሆን እንደሚችል የጠቆሙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገለልተኛ ባለሙያዎች ዓለምአቀፍ ምርመራ እንዲከፈት ጥሪ አሰምተዋል።
የሶማሊያ መንግሥት የኦጋዴን ነፃነት ግንባር የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑትን ቀልቢ ዻጋ ተብለው የሚጠሩትን አብዲሃኪም ሼህ ሙሴን ለኢትዮጵያ አሳልፎ መስጠቱን አውግዞ ዓለምአቀፍ ጣልቃገብነት ጠይቋል።
የአል-ሻባብ ምክትል አዛዥ ሙክታር ሮቦው እጁን መስጠቱ የሶማሊያን መንግሥት በእጅጉ ማስፈንደቁ እየተሰማ ነው።
በኢትዮጵያ የውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር ከግማሽ ሚሊየን መብለጡት አይ.ዲ.ኤም.ሲ. በሚል ምኅፃር የሚጠራው ተቀማጭነቱ ጄኔቫ ስዊትዘርላንድ የሆነ የውስጥ ተፈናቃዮች ክትትል ማዕከል አስታውቋል።
ዩናይትድ ስቴትስ የቨርጂንያዪቱ ሻርለትስቪል ከተማ ውስጥ ባለፈው ቅዳሜ የተነሣውን የሕይወት መጥፋት ያስከተለ ሁከት የጫሩትን ኔኦ ናዚዎችና የነጭ የበላይነት አስተሳሰብ አራማጅ የሆኑትን ኩ ክለክስ ክላን የሚባል ቡድን አባላት “ወንጀለኞችና ወንበዴዎች” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አውግዘዋቸዋል።
ኬንያዊያን ባለፈው ሣምንት የተካሄደውን ምርጫ ውጤት እንዲቃወሙና ዛሬ - ሰኞ ከየቤታቸው ሳይወጡ እንዲውሉ ተቃዋሚው መሪ ራይላ ኦዲንጋ ጥሪ አስተላልፈው የነበረ ሲሆን አንዳንዶች ጥሪውን ተቀብለው ማደማቸውና ብዙዎች ደግሞ ወደ ሥራ መግባታቸው ታውቋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በሰሜን ኮሪያ ላይ የጀመሩትን የብርቱ ቃላት ድብደባ ዛሬ ይበልጥ አጠንክረው ቀጥለዋል።
ኦገስት 21 / 2017 ዓ.ም. [ከአሥር ቀን በኋላ የፊታችን ነኀሴ 15፤ በወዲያኛው ሰኞ] ዩናይትድ ስቴትስን ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ የሚያቋርጥ የፀሐይ ግርዶሽ ይኖራል።
ለኢትዮጵያ ቱሪዝም የመሠረት ድንጋይ ያኖሩት ልጅ ኃብተሥላሴ ታፈሰ በ91 ዓመት ዕድሜያቸው ዛሬ ነሐሴ 3/2009 ዓ.ም. አርፈዋል፡፡ ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም "ወዳጄ" ሲሉ ያስታውሷቸዋል፡፡
ኬንያውያን ትናንት ያካሄዱትን የምርጫ ውጤት እንዳይቀበሉ፣ ዋናው የተቃዋሚ መሪና ፕሬዚዳንት፣ ዕጩ ተወዳዳሪው ራይላ ኦዲንጋ ጥሪ አሰሙ፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ ቢ-767 አይሮፕላን ከ ኤ320 የሕንድ አይሮፕላን ጋር ዛሬ ክንፍ ለክንፍ ተጋጭቷል።
ለኢትዮጵያ ቱሪዝም የመሠረት ድንጋይ ያኖሩት ልጅ ኃብተሥላሴ ታፈሰ በ91 ዓመት ዕድሜያቸው ዛሬ አረፉ፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ ከፊሊፒንስ፣ ከታይላንድ እና ከማሌዥያ ጋር ባሏት የኢኮኖሚና የፀጥታ ትብብር ጉዳዮች ላይ ለመምከር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሬክስ ቲለርሰን ወደዚያው ተጉዘዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የአሁኑ ጉዞ ዋና አጀንዳ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል የሰሜን ኮሪያ የኒኩሌር ጦር መሣሪያ መርኃግብር ከዋና ዋናዎቹ የመነጋገሪያ ነጥቦች አንዱ ነው።
ዩናይትድ ስቴትስ ከፊሊፒንስ፣ ከታይላንድ እና ከማሌዥያ ጋር ባሏት የኢኮኖሚና የፀጥታ ትብብር ጉዳዮች ላይ ለመምከር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሬክስ ቲለርሰን ወደዚያው ተጉዘዋል።
በዓለም ዙሪያ ችግር ላይ ለሚወድቁ ኢትዮጵያዊያን ፈጥኖ ለመድረስና ለመብቶቻቸው መከበር እንደሚሠራ የሚናገረው “ዓለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት” የሚባል ስብስብ የፊታችን ነኀሴ 6 ወይም ኦገስት 12 ዋሺንግተን ዲሲና አካባቢዋ ለሚኖሩ ዝግጅት አሰናድቷል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ ሩሲያ ላይ የጣላቸውን አዳዲስ ማዕቀቦች የያዘ ሠነድ ዛሬ ፈርመው የሃገሪቱ ሕግ አድርገውታል።
የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የኢንዶኔዥያ አገልግሎት ዘጋቢ ክሪቲካ ቫራጋር በቅርቡ ወደ ዋና ከተማዪቱ ጃካርታ ለመስክ ሥራ ተጉዛ በነበረ ጊዜ በዚያ ድንገት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን አገኘች። አነጋገረቻቸው፤ ታሪካቸውንም ፃፈች።
ተጨማሪ ይጫኑ